“ዞራማውያን፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ዞራማውያን
በኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እምነታቸውን ማጠንከር
ዞራማውያን የሚባሉ የኔፋውያን ቡድኖች የእግዚአብሔርን ተዛዛት እየጠበቁ አልነበረም። ይህም ነቢዩ አልማን እንዲያዝን አደረገው። እነርሱን ለመርዳት በጣም ጥሩ የሆነው መንገድ የእግዚአብሔርን መንገድ ማስተማር እንደሆነ ያውቅ ነበር። እነርሱን ለማስተማር ከአሙሌቅ እና ከሌሎች ጋር ሄደ።
ዞራማውያን ስለ እግዚአብሔር ያውቁ ነበር ነገር ግን የእርሱን አስተምሮቶች ቀይረዋል። ጣኦታትንም አምልከዋል። እነርሱ ከሌሎች ሰዎች በላይ የተሻሉ እንደሆኑያስቡ ነበር። ገንዘብ ለሌላቸው ሰዎች እንዲሁ ስስታሞች ነበሩ።
ዞራማውያን በቤተክርስቲያኖቻቸው መካከል ለመቆም ከፍ ያለ ስፍራን ገነቡ። አንድ በአንድ በዚያ ላይ ቆሙ እና ጸለዩ። ዘወትር ተመሳሳይ ቃላትን በመጠቀም ይጸልያሉ። በጸሎታቸውም እግዚአብሔር አካል እንደሌለው እና ኢየሱስ ክርስቶስም ህያው እንዳልሆነ ይናገራሉ። እነርሱ እግዚአብሔር የሚያድናቸው ብቸኛ ህዝቦች እንደሆኑ ይናገራሉ።
አልማ ዞራማውያንን ወደዳቸው እና እግዜአብሔርን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲከተሉ ፈለገ። እርሱን እና ከእርሱ ጋር የመጡትን ዞራማውያንን ለማስተማር እንዲረዳቸው ጸለየ እና እግዚአብሔርን ጠየቀ። አልማ እና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። እነርሱም ሄዱ እና በእግዚአብሔር ሀይል አስተማሩ።
አንዳንድ ዞራማውያን አዝነው ነበር። በቤተክርስቲያኖች ውስጥ እንዲገቡ አልተፈቀደላቸውም ነበር እና ያማረ ልብስም አልነበራቸውም ነበር። እነርሱ እግዚአብሔርን ማምለክ ይፈልጉ ነበር ነገር ግን ወደ ቤተክርስቲያን ካልሄዱ በስተቀር እንዴት እንደሚያመልኩ አያውቁም ነበር። ምን ማድረግ እንዳለባቸው አልማን ጠየቁት። የትም ይሁኑ የት እግዚአብሔር ጸሎቶቻቸውን እንደሚሰማ አልማ አስተማራቸው።
እግዚአብሔር ሰዎች እምነት እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ አልማ ተናገረ። እርሱ የእግዚአብሔርን አስተምሮዎች ከአንድ ዘር ጋር አነጻጸረ። ሰዎች የእግዚአብሔርን አስተምሮዎች በልባቸው ቢተክሉ ያም ዘር ያድጋል እና የእግዚአብሔርም ትምህርቶች እውነት እንደሆኑ ያውቃሉ። እርሱም እምነታቸውን መለማመድን ለመጀመር ለማመን ፍላጎት እንዲያድርባቸው ብቻ እንደሚያስፈልግ ተናገረ።
አሙሌቅ እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለውን እቅድ አስተማረ። እርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሁሉም ሃጢአታቸው ይቅር ሊባልላቸው እንደሚችል ነገራቸው። እርሱ ወደ እግዚአብሔር መጸለይን እና እግዚአብሔር እንደሚረዳቸው እና እንደሚጠብቃቸው እንዲሁ አስተማረ።
አያሌ ድሆች የነበሩ ዞራማውያን አልማ እና አሙሌቅ ያስተማሩትን አመኑ። ነገር ግን የዞራማውያን መሪዎች ተበሳጩ። አማኞችን በሙሉ ከከተማው እንዲወጡ ግድ አሏቸው።
አማኖቹ ከአንቲ ኔፊ ሌሂዎች ጋር ለመኖር ሄዱ። አንቲ ኔፊ ሌሂዎች እነርሱን ምግብ፣ አልባሳት፣ እና መሬት በመስጠት አገለገሏቸው።