በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የንግስት እምነት


“የንግስት እምነት፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“የንግስት እምነት፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

አልማ 18–19

የንግስት እምነት

በኢየሱስ ክርስቶስ ደስታን ማግኘት

የንግስቲቱ ባለቤት በምድር ላይ ወድቆ

አንዲት የላማናውያን ንግሥት ከባለቤቷ ከንጉሥ ላሞኒ ጋር ገዛች። ንጉሱ አሞን የሚባል ኔፊያዊን ስለ ጌታ እንዲያስተምረው ጠየቀው። ንጉሡ አሞን የነገረውን አመነ። ንጉሱ ለመጸለይ ተንበርክኮ ጌታ ይቅር እንዲለው ጠየቀው። ሲጸልይ ንጉሡ በምድር ላይ ወደቀ። የሞተ መሰለ።

አልማ 18፥21፣ 24–42

ንግስቲቱ የወደቀውን ባለቤቷን እያየች

የንጉሱ አገልጋዮች ወደ ንግስቲቱ ወሰዱት። በመኝታውም ላይ አደረጉት። በዚያም ተኛ እንዲሁም ለሁለት ቀናት እና ለኁለት ምሽቶች ምንም አልተንቀሳቀሰም።

አልማ 18፥43

ንግስቲቱ ከአገልጋይ ጋር እየተነጋገረች

በዚያም ጊዜ፣ ንግስቲቱ እና ልጆቿ በጣም አዝነው ነበር። ከንጉሱ ጋር ቆዩ እንዲሁም ስለእርሱ አለቀሱ። አንዳንድ ሰዎች ንጉሱ መቀበር አለበት አሉ። ነገር ግን ንግስቲቱ በመጀመሪያ ከአሞን ጋር ለመነጋገር ፈለገች። እርሱ የእግዚአብሔር ሀይል እንዳለው ሰምታ ነበር። የንግስቲቱ አገልጋዮች አሞን ወደ ንግስቲቱ እንንዲመጣ ጠየቁት።

አልማ 18፥4319፥1–3፣ 5

ንግስቲቱ አሞንን እያነጋገረች

ንግስቲቱ እርሱ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ እንደሰማች ለአሞን ነገረችው። አሞን ንጉሱን ሄዶ እንዲያይ ጠየቀችው። አሞን ንጉሱ በህይወት እንዳለ ያውቅ ነበር። ንጉሲ እንዲያንቀላፋ ያደረገው የእግዚአብሔር ሀይል ነበር። አሞን ባለቤቷ በሚቀጥለው ቀን እንድሚነቃ ለንግስቲቱ ነገራት።

አልማ 19፥3–8

ንግስቲቱ ራሷን በባለቤቷ ላይ አሳርፋ

ንግስቲቱ አሞን ያለውን አመነች እንዲሁም በእግዚአብሔር ታላቅ እምነት ነበራት። ባለቤቷ በሚቀጥለው ቀን እንድሚነቃ አመነች። አሞንም እርሷ ታላቅ እምነት ስለነበራት እንደተባረከች ተናገረ። ከራሱ ህዝቦች በላይ ታላቅ እምነት እብደነበራትለንግስቲቱ ነገራት። ንግስቲቱ ከአጠገቡ በመሆን ሌሊቱን በሙሉ ባለቤቷን ጠበቀችው።

አልማ 19፥9–11

ንግስቲቱ ባለቤቷ ስለነቃ ተደስታ

በሚቀጥለው ቀን፣ ንጉሱ ነቃ። ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳየ ለንግስቲቱ ነገራት። ንግስቲቱ እና ንጉሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያህል እንደሚወዳቸው አወቁ፣ እናም በደስታ ተሞሉ።

አልማ 19፥12–13