በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢዩ ሞሮኒ


“ነቢዩ ሞሮኒ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሞርሞን 8ሞሮኒ 17፤ 10

ነቢዩ ሞሮኒ

የኢየሱስ ክርስቶስን ንፁህ ፍቅር ማግኘት

ሞሮኒ እየነደደች ያለችን አንዲት ከተማ ይመለከታል

ሞሮኒ የመጨረሻው የኔፋውያን ነቢይ ነበር። እርሱ በኔፋውያን እና በላማናውያን መካከል በተደረገው ትልቅ ጦርነት ውስጥ ተዋግቷል። ቤተሰቦቹ እና የሚያውቃቸው ሰዎች በሙሉ በጦርነቱ ሞተዋል። በምድሪቱ የነበሩት ሰዎች ሃጢአተኞች ነበሩ። በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑትን ማናቸውንም ሰዎች ገድለዋል። ሞሮኒ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን ሊክድ አልቻለም።

ሞርሞን 8፣ 2–10ሞሮኒ 1፣ 2–3

ሞሮኒ የብረት ሰሌዳዎቹን ተሸከመ እናም ከወታደሮችም ደበቃቸው።

የሞሮኒ አባት፣ ሞርሞን፣ በብረት ሰሌዳው ላይ የህዝባቸውን ታሪክ ይጽፍ ነበር። ሞርሞን ከመሞቱ በፊት ሰሌዳዎቹን ለሞሮኒ ሰጠ። ሞሮኒም የራሱን ህይወት እና ሰሌዳዎቹን ለማዳን ሲል መደበቅ ነበረበት።

ሞርሞን 6፣68፣1–5፣ 13ሞሮኒ1፣1–3

ሞሮኒ በዋሻ ውስጥ ተቀምጧል እናም በብረት ሰሌዳዎቹ ላይ ይጽፋል

ህይወት ለሞሮኒ አስቸጋሪ ነበር፣ ነገር ግን ታማኝ ሆኖ ቆይቷል። ሞርሞን ስለልግስና ፣ ስለንጹህ የክርስቶስ ፍቅር ያስተማረውን ጽፏል። ሰዎች ይህንን ፍቅር ለማግኘት በሙሉ ልባቸው ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እንዳለባቸው ሞርሞን ተናግሯል። እርሱም እንዳለው በእውነት ኢየሱስን ለሚወዱ እግዚአብሔር ልግስናን ይሰጣል።

ሞሮኒ 7፣32–33, 40–4810፣20–21, 23

አንድ ቤተሰብ ምግብ እየተሰጣቸው በነበረ ጊዜ ደስተኞች ሆኑ፣ እና ሞሮኒም ተደስቷል።

ምንም እንኳ እርሱ ያውቃቸው የነበሩትን ቢገድሉበት እና እርሱን እራሱን ሊገድሉት የፈለጉ ቢሆንም ሞሮኒ ላማናይቶችን ወዷቸዋል። ላማናይቶችን ለወደፊቱ ለመርዳት እርሱ ብዙ ነገሮችን በብረት ሰሌዳዎቹ ላይ ጽፏል። አንድ ቀን የተዘገበውን እንደሚያነቡ እና ዳግም በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያምኑ ተስፋ አድርጓል።

ሞርሞን 8፣1–3ሞሮኒ 1፣1–410፣1

ሞሮኒ በዋሻ ውስጥ ተቀምጧል እናም በብረት ሰሌዳዎቹ ላይ ይጽፋል

ሞሮኒ መዝገቡን የሚያነቡትን በሙሉ እግዚአብሔር ምን ያህል ልጆቹን በፍቅር የሚንከባከብ መሆኑን እንዲያስቡ ጋብዟል። እነርሱንም መዝገቡ እውነት ስለመሆኑ እንዲጸልዩ እና እግዚአብሔርን እንዲጠይቁ ጋብዟቸዋል። እርሱም እንዳለው በኢየሱስ እምነት ቢኖራቸው እና በእውነትም ለማወቅ የሚሹ ከሆነ፣ እግዚአብሔር እውነቱን እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል። በመንፈስ ቅዱስ ሃይልም ያውቃሉ።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያሞሮኒ 10፥1–5

ሞሮኒ የብረት ሰሌዳዎቹን ቀበራቸው እና በተደበቁበትም ስፍራ አንድ አለት አኖረበት።

ሞሮኒ መዝገቡን መጻፉን ጨረሰ። ከዚያም የብረት ሰሌዳዎቹን በመሬት ውስጥ ቀበራቸው። ኢየሱስ በሰሌዳዎቹ ላይ የተጻፈው ታሪክ በአለም ላይ አንድ ቀን የእግዚአብሔርን ልጆች ህይወት እንደሚባርክ ተናገረ።

ሞሮኒ 8፥ 4፣ 14–16

ወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ አለቱን አንቀሳቀሰው እና የብረት  ሰሌዳዎቹን እና ሊያሆናውን ተመለከተ።

ከብዙ ዓመት በኋላም፣ ጆሴፍ ስሚዝ ለተባለ ወጣት የብረት ሌዳዎቹ የተቀበሩበትን ስፍራ እንዲያሳየው እግዚአብሔር ሞሮኒን፣ እንደ መልዓክ ላከው። ጆሴፍ ነቢይ እንዲሆን በእግዚአብሔር ተጠርቷል። ሰዎች በውስጣቸው ያሉትን ያነቧቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጆሴፍን ሰሌዳዎቹን እንዲተረጉም ረዳው። መዝገቡ አሁን መፅሐፈ ሞርሞን ይባላል።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ