“ያሬድ እና ቤተሰቡ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ያሬድ እና ቤተሰቡ
በጌታ የተመራ ጉዞ
ያሬድ እና ወንድሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ ከሺህ ዓመታት በፊት በባቢሎን ይኖሩ ነበር። እነርሱ ለጌታን ታዘዙ። ነገር ግን አብዛኛው ህዝብ በባቢሎን ለጌታ የታዘዘ አልነበረም። እነዚያም ሰዎች ወደ ሰማይ ለመድረስ ግንብን መገንባት ጀመሩ። ጌታም ህዝቡ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን ደባለቀ።
ያሬድ ወንድም ነበረው። ጌታ የያሬድን ወንድም አምኖታል። ያሬድ ወንድሙን ጌታ እንዲረዳው እንዲጸልይ ጠየቀው። በጸሎቱም፣ የያሬድ ወንድም የቤተሰቦቹን እና የጓደኞቹን ቋንቋ እንዳይደባልቅበት ጌታን ጠየቀ። በዚያም መንገድ አሁንም እርስ በርሳቸው ሊግባቡ ቻሉ።
ጌታ አፍቃሪ እና ደግ ነው። የያሬድን ቤተሰብ እና የጓደኞቹን ቋንቋ አልደባለቀም። በኋላም፣ ጌታ ለያሬድ ወንድም ለእነርሱ የተለየ ምድር እንዳዘጋጀላቸው ነገረው። ጌታም ወደዚያ እንደሚመራቸው ተናገረ።
ያሬድና እና ወንድሙ ቤተሰባቸውን እና ጓደኞቻቸውን አሰባስበዋል። እንዲሁም ከብቶቻቸውን እና ሁሉንም ዓይነት ዘሮችን ሰበሰቡ፡፡ ከዚያም ቤቶቻቸውን ትተው ሄዱ እና በምድረበዳም ተጓዙ። ጌታም በደመና ውስጥ በመሆን እያናገራቸው መራቸው።
ረዥም ርቀት ከተጓዙ በኋላ፣ ወደ አንድ ባህርም መጡ። በባህሩ ዳርቻ ለአራት ዓመታት ኖሩ፡፡ ለረዥም ጊዜያት፣ የያሬድ ወንድም ወደ ጌታ አልጸለየም።
ጌታ ለያሬድ ወንድም እንደገና እንዲጸልይ ነገረው። የያሬድ ወንድም ንስሀ ገባ እና ወደጌታም ጸለየ፡፡ ጌታ ይቅር አለው።
ጌታም ለያሬድ ወንድም ጀልባዎች የተባሉ መርከቦችን መገንባት አስተማረው። ቤተሰቦቻቸውም በጀልባ ባህር አቋርጠው ወደ ተስፋይቱ ምድር መሄድ ቻሉ።
የያሬድ ወንድም እና ቤተሰቦቹ ጀልባዎቹን ገነቡ። በጀልባዎቹም ውስጥ ብርሃን እንደሌለ ተመለከተ። በጨለማም ውስጥ ባህር አቋርጠው መጓዝ እንዳለባቸው ጌታን ጠየቀ። ጌታ ለያሬድ ወንድም መርከቡ ብርሃን የሚያገኝበትን መንገድ ማሰብ እንዳለበት ነገረው።
የያሬድ ወንድም 16 አነስተኛ፣ የጠሩ ድንጋዮችን አዘጋጀ። እርሱም ጌታ እንዲነካቸው እና እንዲያንጸባርቁ እንዲያደርግለት ጠየቀው። ጌታም እጁን ዘረጋ እናም ድንጋዮቹን አንድ በአንድ በጣቶቹ ነካቸው። የያሬድ ወንድምም የጌታን ጣት ለማየት ቻለ። ጌታ ልክ እንደርሱ አካል ያለው መሆኑን ባየ ጊዜ ተደነቀ።
ጌታ የያሬድ ወንድም ታላቅ እምነት እንዳለው ተናገረ። ከዚያም ጌታ ለያሬድ ወንድም ተገለጠለት እና የመንፈስ አካሉን አሳየው። ጌታም ‘እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ’ አለ። እርሱም አዳኝ ለመሆን እንደተመረጠ ተናገረ። ለያሬድ ወንድም ሌሎች ብዙ ነገሮችን አስተማረው።
የያሬድ ወንድም ወደ ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ተመለሰ። እርሱም ከጌታ ጋር በነበረ ጊዜ የተማረውን ጻፈ። በተጨማሪም ድንጋዮቹን በጀልባዎቹ ውስጥ አደረጋቸው። አሁን ለጉዟቸው የሚሆን ብርሃን አላቸው።
ቤተሰቡም ባህሩን ለማቋረጥ በጀልባው ውስጥ ገብተዋል። እነርሱም ይጠነቀቅላቸው ዘንድ በጌታ ታምነዋል። ብዙ ማዕበሎች እና ማዕበሎች ነበሩ፡፡ አልፎ አልፎ፣ ውሃው ጀልባዎቹን ያጥለቀልቃቸዋል። ነገር ግን ይጸልዩ ነበር፣ እና ጌታም በውሃው አናት ላይ መልሶ ያመጣቸው ነበር። እነርሱም አያሌ የምስጋና መዝሙሮችን ዘምረዋል።
ከአንድ ዓመት ገደማም በኋላ፣ ጌታ ቃል ወደገባላቸው ምድር ደረሱ። በሃሴት ጮሁ እና አመሰገኑትም።