Scripture Stories
አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች


“አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 23–27

አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች

ጠላቶቻቸውን ሊወዱ የመረጡ ሰዎች

ምስል
አሞን በዛፍ ሥር ሰዎችን እያስተማረ

ብዙ ላማናውያን ከአሞን እና ከወንድሞቹ ስለ እግዚአብሔር ተማሩ። እነዚህ ላማናውያን በጌታ ላይ ጠንካራ እምነት ነበራቸው እንዲሁም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ይከተሉ ነበር። አዲስ ስም ፈልገው ስለነበር በላማናውያን ፈንታ ራሳቸውን አንቲ-ኔፊ-ሌሂ ብለው ጠሩ።

አልማ 23፥3–7፣ 16–17

ምስል
አሞንን ሲያስተምር እያዳመጡ ያሉ ቤተሰቦች

አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች በእግዚአብሔር ባላቸው እምነት ምክንያት ተለወጡ። ይሠሩት ከነበረው መጥፎ ነገር ንስሃ ገቡ። እግዚአብሔር እንደሚወዳቸውና ይቅር እንዳላቸው አወቁ።

አልማ 24፥8–14

ምስል
አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች መሣሪያዎችን ክፍት ጉድጓድ ውስጥ እየጣሉ

ላማናውያን ተቆጥተው አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎችን ለማጥቃት እየተዘጋጁ ነበር። ከመዋጋት ይልቅ፣ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ለእግዚአብሔር ቃል ገቡ። ሰዎችን ዳግመኛ እንደማይጎዱ ተናገሩ። ይህንን ለማሳየት መሳሪያቸውን ቀበሩ። ጠላቶቻቸውን ከመጉዳት ወይም ከመግደል ይልቅ መውደድን መረጡ።

አልማ 24፥1–1926፥31–34

ምስል
የተቆጣ ላማናዊ መሳሪያ ይዞ

በእግዚአብሔር የማያምኑ ላማናውያን አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎችን አጠቁ።

አልማ 24፥20

ምስል
ሁለት አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ለጸሎት ተንበርክከው

አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ከተገደሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚኖሩ እምነት ነበራቸው። ለእግዚአብሔር የገቡትን ቃል በመጠበቅ ላማናውያንን አልተዋጉም።

አልማ 24፥16፣ 21

ምስል
ላማናውያን ማጥቃት አቁመው

ከመዋጋት ይልቅ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ጸለዩ። ይህን ሲመለከቱ ብዙዎቹ ላማናውያን ማጥቃት አቆሙ። ሰዎችን በመግደላቸው መጥፎ ስሜት ተሰማቸው። እነዚያ ላማናውያን ዳግመኛ ሰዎችን ላለመጉዳት መረጡ። ከአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ጋር ተቀላቀሉ።

አልማ 24፥21–2725፥13–16

ምስል
አሞን እና አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች እየተጓዙ

ጊዜው ሲሄድ ብዙ ሰዎች ጥቃት አደረሱ። አሞን እና ወንድሞቹ፣ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች እየተሰቃዩ ስለነበር አዘኑ። ከኔፋውያን ጋር ይኖሩ ዘንድ ህዝቡን እንዲወስድ ንጉሱን ጠየቁ። ንጉሱም ጌታ እንድንሄድ ከፈለገ እንሄዳለን አለ። አሞን ጸለየ። ጌታ መሄድ እንዳለባቸው እና እንደሚጠብቃቸው ተናገረ።

አልማ 27፥2–15

ምስል
ኔፋውያን ለአንቲ-ኔፊ-ሌሂ ህዝብ ሰላምታ እያቀረቡ

ኔፋውያን ለአንቲ-ኔፊ-ሌሂስ እንዲኖሩበት መሬት ሰጧቸው እንዲሁም ጠበቋቸው። በምላሹም፣ አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ለኔፋውያን ምግብ ሰጡ። አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች በእግዚአብሔር ታላቅ እምነት ነበራቸው እንዲሁም ይወዱታል። ለሁሉም ሰው እውነተኞች ነበሩ እናም ፈጽሞ ላለመዋጋር የገቡትን ቃል ጠበቁ። ህይወታቸውን በሙሉ ታማኝ ነበሩ።

አልማ 27፥20–30

አትም