“የወጣት ሠራዊት እናቶች፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
የወጣት ሰራዊት እናቶች
ልጆች እግዚአብሔርን እንዲያምኑ ማስተማር
አንቲ- ኔፊ- ሌሂ ጌታን እና ሁሉንም ህዝቦች ወደዋል። እናቶች ልጆቻቸውን ዘወትር እግዚአብሔርን ማመን እንደሚችሉ አስተምረዋል። የእርሱን ተዛዛት እንዲጠብቁ አስተምረዋቸዋል።
አልማ 26፣31–34፤ 27፣12፣ 27–30፤ 56፣47–48፤ 57፣21፣ 26
ኔፋውያን እና ላማናውያን በታላቅ ጦርነት እርስ በርስ እየተዋጉ ነበር። ኔፋውያን የራሳቸውን ህዝቦች እና አንቲ- ኔፊ -ሌሂን ለመከላከል እየተዋጉ ነበር።
በቀደመው ሀጢአታቸው ምክንያት፣ አንቲ- ኔፊ- ሌሂዎች በፍጹም ከማንም ጋር ላለመዋጋት ቃልኪዳን ወይም ልዩ የሆነ ኪዳንን ከእግዚአብሔር ጋር አድርገዋል። ነገር ግን እነርሱ ኔፋውያንን ወደዋቸዋል እናም ሊረዷቸው ፈልገዋል።
አንቲ- ኔፊ- ሌሂዎች በጦርነቱ ለመዋጋት እየሄዱ ነበር። ነገር ግን ነቢዩ ሔለማን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ላለመዋጋት የገቡትን ኪዳን ይጠብቁ ዘንድ አሳመኗቸው። አንቲ ኔፊ ሌሂዎች ጓደኞቻቸው በብዙ ህመም እና ችግር ውስጥ ሲያልፉ ማየት ነበረባቸው ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃልኪዳን ጠብቀዋል።
የአንቲ ኒፊ- ሌሂ- ልጆች ወላጆቻቸው ያደረጉትን ኪዳን አላደረጉም። አሁን ለነጻነት እንደሚዋጉ የራሳቸውን ኪዳን አድርገዋል።
ታላቅ ብርታትን አግኝተዋል። አዎን፣ ጥርጣሬ ከሌለባቸው እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው በእናቶቻቸውም ተምረዋል።
ልጆቹ እናቶቻቸውን አምነዋል። ልጆቹ ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበሩ እና ትእዛዛቱንም ጠብቀዋል። እግዚአብሔርም ጠብቆ እንደሚያቆያቸው አምነዋል። እናቶች እግዚአብሔር ልጆቻቸውን እንደሚጠብቅ አውቀዋል።