“ነቢዩ ኤተር፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ነቢዩ ኤተር
ጌታ ለአንድ ህዝብ የሰጠው ማስጠንቀቂያ
ጌታ የያሬድን ወንድም እና ቤተሰቡን ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር አመጣ። ትሑት እና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ ነበሩ። ቡድናቸው ለብዙ ዓመታት አደገ እናም የሚመራቸውን ንጉስ ፈለጉ። የያሬድ ወንድም የንጉሥ መኖር ወደ ችግር ሊመራቸው እንደሚችል አስጠነቀቃቸው፣ ነገር ግን ንጉሥ እንዲመርጡ ፈቀደላቸው።
ለብዙ መቶ ዓመታት፣ ያሬዳውያን በቃል ኪዳኗ ምድር ውስጥ ኖሩ። አንዳንድ ጊዜ ንጉሦቻቸው መልካም ነገር እንዲያደርጉ ሲመሯቸው ሌላ ጊዜ ግን አላደረጉም። የእግዚአብሔር ነቢያት ህዝቡ ንስሐ እንዲገባ ያስጠነቅቁ ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሲሰሙ እና ሲጠብቁ፣ እርሱም ይባርካቸው ነበር። የመጨረሻው የያሬዳውያን ነቢይ ኤተር ይባል ነበር።
ኤተር 7፥23–27፤ 9፥26–30፤ 10፥16–17፣ 28፤ 11፥1–8፣ 12–13፣ 20–22፤ 12፥2
ህዝቡ እግዚአብሔርን እየታዘዘ አልነበረም። የጌታ መንፈስ ግን ከኤተር ጋር ነበር። ከጠዋት እስከ ማታ አስተማራቸው። በእግዚአብሔር እንዲያምኑ እና ንስሐ እንዲገቡ አለበለዚያ እንደሚጠፉ ተናገረ። እምነት ቢኖራቸው እንደገና ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ተስፋ እና መልካም ነገር ለማድረግ ጥንካሬ ይኖራቸው ነበር። ሰዎቹ አላመኑም።
ኤተር ሰዎቹ ያደርጉ የነበረውን ተመለከተ። ቀን ቀን ዋሻ ውስጥ እየተደበቀ ያየውን ይጽፍ ነበር። ህዝቡ ንስሃ አልገባም እንዲሁም እርስ በርስ መጣላት ጀምረው ነበረ።
ኤተር፣ የያሬዳዊውያን ንጉስ ቆሪያንተመር ንጉስ ለመሆን የሚፈልጉ ብዙ ሰዎችን መዋጋት እንደነበረበት ተመለከተ። ቆሪያንተመር ራሱን ለመከላከል ሠራዊቱን ተጠቀመ።
አንድ ቀን፣ ቆሪያንተመር እና ህዝቡ ንስሃ እንዲገቡ እንዲያስጠነቅቅ ጌታ ለኤተር ነገረው። ያንን ካደረጉ፣ ጌታ ህዝቡን ይረዳል እንዲሁም ቆሪያንተመር መንግስቱን ይዞ እንዲቀጥል ይፈቅዳል። ይህ ካልሆነ፣ ህዝቡ እርስ በርሱ ይጠፋፋል። ቆሪያንተመር የጌታን ቃል እውነት መሆኑን ለማየት ረጅም ዕድሜ ይኖረዋል። ከዚያም እሱም ይሞታል።
ቆሪያንተመር እና ህዝቡ ንስሃ አልገቡም። ህዝቡ ኤተርን ለመግደል ሞከሩ፣ ነገር ግን ኤተር ወደ ዋሻው አመለጠ። ሺዝ የሚባል ሰው ከቆሪያንተመር ጋር ተዋጋ። ህዝቡ ከሺዝ ወይም ከቆሪያንተመር ሠራዊት አንዱን ለመቀላቀል መረጡ። ሁለቱ ሠራዊቶች ብዙ ጦርነቶችን አደረጉ። ብዙ ሰዎች ሞቱ።
ቆሪያንተመር ኤተር የተናገረውን አስታወሰ። ብዙ የእርሱ ህዝቦች በመሞታቸው አዘነ። ይህ እንደሚሆን ሁሉም ነቢያት አስጠንቅቀው የነበረውን አስታወሰ። ንስሃ መግባት ጀመረ እንዲሁም ለሺዝ ደብዳቤ ላከ። ህዝቡ መዳን ከቻለ መንግስቱን አሳልፎ እንደሚሰጥ ተናገረ። ነገር ግን ሺዝ ለመዋጋት ፈለገ።
የቆሪያንተመር ህዝብ ተናድደው ነበር፣ እናም ለመዋጋት ፈለጉ። የሺዝ ህዝብም ተናድደው ነበር፣ እናም መዋጋት ፈለጉ። ማንም ንስሐ መግባት አልፈለገም። ኤተር እያንዳንዱ ሰው ወደ ጦርነት እንደሄደ ተመለከተ። ተጨማሪ ብዙ ሰዎች ሞቱ።
ቆሪያንተመር ጦርነቱን ለማቆም ፈለገ። እርሱም መንግስቱን እንዲወስድ እንዲሁም ህዝቡን እንዳይጎዳ ሺዝን ጠየቀ። ነገር ግን ሁሉም ሰው ተናድዶ ነበር። የጌታ መንፈስ አልነበራቸውም። ኤተር ከያሬዳዊያን መካከል በህይወት የተረፈው ቆሪያንተመር ብቻ እስኪሆን ድረስ ሁሉም ሲዋጋ አየ። ከዚያም ቆሪያንተመር ራሱን ስቶ ወደቀ።
ኤተር፣ ጌታ የተናገረው ሁሉ እውነት እንደሆነ አየ። ኤተር የተከሰተውን ነገር ጽፎ ጨረሰ። ከዚያም እሱ ካለፈ በኋላ ሰዎች ጽሑፎቹን ማግኘት እንዲችሉ አደረገ። ኤተር እግዚአብሔርን ያምን ነበር እንዲሁም አንድ ቀን ከእርሱ ጋር ለመሆን ይጓጓ ነበር።