“ኔፋዊዋ አገልጋይ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ኔፋዊዋ አገልጋይ
ህዝቦቿን ለመጠበቅ እየረዳች
አንዲት አገልጋይ ሞሪያንተን ለተባለ ኔፋዊ መሪ ትሠራ ነበር። ሞሪያንተን በህዝቡ መካከል ችግር እየፈጠረ ነበር። አንድ የኔፋውያንን ቡድን በማጥቃት መሬታቸውን ለመውሰድ ሞከረ። ከዚያም ከህዝቡ ጋር ወደ ሰሜን ለመጓዝና በዚያ ያለ ምድርን ለመውሰድ አቀደ።
አንድ ቀን፣ ሞሪያንተን በአገልጋይቱ ተናደደ። ክፉ ነገር አድርጎባት እንዲሁም ጎድቷት ነበር። አገልጋይዋ አምልጣ ወደ ሻምበል ሞሮኒ ካምፕ ሸሽታ ሄደች። ሞሪያንተን ስላደረገው ክፉ ነገር ለሞሮኒ ነገረችው። ሞሮኒም አመናት።
አገልጋይዋ፣ ሞሪያንተን ሄዶ በሰሜን ያለውን መሬት ለመውሰድ እንደሚፈልግ ተናገረች። ሞሮኒ ተጨነቀ። ሞሪያንተን በሰሜን በኩል ያለውን መሬት ከተቆጣጠረ ኔፋውያን አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። ህዝቡም ነፃነቱን እንዲያጣ ሊያደርግ ይችላል።
ሞሪያንተንን ለማስቆም ሞሮኒ ሠራዊትን ላከ። የሞሪያንተን ህዝብ ከሠራዊቱን ጋር ተዋጉ ሆኖም ተሸነፉ። ሰላማዊ ለመሆን ቃል በመግባት ወደ አገራቸው ተመለሱ። አገልጋይዋ ሞሮኒን ስላስጠነቀቀች፣ የኔፋውያን ከተሞች ደህንነት ተጠበቀ።