“እስማኤል እና ቤተሰቡ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
እስማኤል እና ቤተሰቡ
ወደ ቃል ኪዳን ምድር እየተደረገ ያለውን ጉዞ መቀላቀል
የሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ በምድረበዳ ውስጥ ብቻቸውን ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን፣ ጌታ ሌሂ ልጆቹን ላማንን፣ ልሙኤልን፣ ሳምን እና ኔፊን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲልክ ነገረው። እስማኤልንና ቤተሰቡ ከእነርሱ ጋር ይቀላቀሉ ዘንድ እንዲጠይቋቸው ተልከው ነበር። በጋራ ቤተሰቦቻቸው በቃል ኪዳን ምድር ልጆችን ማሳደግ ይችላሉ።
እስማኤል እና ቤተሰቡ ጌታን መከተል ፈለጉ። ጌታ ከሌሂ እና ሳርያ ቤተሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ እንደሚፈልግ አመኑ። ኢየሩሳሌምን ለመልቀቅ እና ሌሂን በምድረበዳ ውስጥ ለመገናኘት መረጡ።
በመንገዳቸው ላይ፣ አንዳንድ ሰዎች ታዛዥ ለመሆን አልፈለጉም። ወደ ቤታቸው ለመመለስ ፈለጉ። በጌታ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ኔፊ ጠየቃቸው።
እምነት ካላቸው ጌታ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደሚችል ኔፊ ነገራቸው። ነገር ግን ላማን እና ልሙኤል ተናደዱ። ኔፊን አስረው በምድረበዳ ሊተውት ፈለጉ።
ኔፊ እርዳታ ለማግኘት ጸለየ። ገመዱ ተፈታ፣ እና ኔፊ ተነስቶ ቆመ። ነገር ግን ላማን እና ልሙኤል አሁንም ሊጎዱት ፈለጉ። ከእስማኤል ሴት ልጆች አንዷ ኔፊን ተከላከለችው። በተጨማሪም እናቷ እና ከወንድሞቿ አንዱ እርሱን ተከላከሉት። ላማን እና ልሙኤል እነርሱን ያሉትን ሰሙ እንዲሁም ኔፊን ለመጉዳት መሞከራቸውን አቆሙ።
ላማን እና ልሙኤል ስላደረጉት ነገር አዘኑ። ኔፊን ይቅር እንዲላቸው ጠየቁት። ኔፊ ወንድሞቹን ይቅር አለ። ከዚያም ላማን እና ልሙኤል ጸለዩ እና ጌታ ይቅር እንዲላቸው ጠየቁት።
ሁሉም ጉዟቸውን ቀጥለው ወደ ሌሂ እና የሳርያ ድንኳን ደረሱ። በመጨረሻም ሁለቱ ቤተሰቦች አብረው ነበሩ። እግዚአብሔርን አመሰገኑት እንዲሁም አመለኩት።