“ነቢዩ ሳሙኤል፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ነቢዩ ሳሙኤል
ስለኢየሱስ መወለድ እና ሞት አስተምሮ
ሳሙኤል የተባለው ላማናዊው ነቢይ ኒፋውያንን በዛራሄምላ ለማስተማር ሄደ። እርሱ ስለንሰሃ አስተማረ። ኔፋውያን ሊሰሙት አልቻሉም እና ከከተማው ውጪ ወረወሩት።
ሳሙኤል ወደ ህዝቡ ሊመለስ ተቃርቦ ነበር። ነገር ግን ጌታ እንዲመለስ እና ኔፋውያንን እንዲያስተምር ነገረው።
ጌታ ለሳሙኤል ምን መናገር እንዳለበት ነግሮታል። ሳሙእል ጌታን ታዘዘ። እርሱ ወደ ዛራሄምላ ተመለሰ። ነገር ግን ኔፋውያን ወደ ከተማው አላስገቡትም።
ሳሙኤል ወደ ከተማው ግንብ ወጣ። እርሱ ጌታ በልቡ ያስቀመጠውን ተናገረ። ህዝቡ መጥፎ የሆኑ ነገሮችን እያደረጉ በመሆናቸው ምክንያት እንደሚጠፉ አስጠነቀቃቸው። ንሰሃ እና በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ብቻ ሊያድናቸው እንደሚችል ተናገረ። እርሱም ኢየሱስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደሚወለድ ተናገረ።
ሳሙኤልም የኢየሱስ መወለድ ምልክቶች እንደሚኖሩ ተናገረ። ህዝቡም እነኚህን ምልክቶች እንዲፈልጋቸው ተናገረ። አንዱም ምልክት የሚሆነው ጨለማ የሌለበት ሌሊት ነው። ሌላው ምልክት አዲስ ኮከብ እና ሌሎች አስደናቂ ነገሮች በሰማይ እንደሚገለጡ ነው።
ሳሙኤል ሰዎች በኢየሱስ እምነት እንዲኖራቸው ይፈልግ ነበር። እርሱም ኢየሱስ እንደሚሞት እና ከሞት እንደሚነሳ በመሆኑም ሰዎች ሁሉ ንሰሃ የሚገቡ ከሆነ እንደሚድኑ ተናግሯል።
ሳሙኤልም የኢየሱስ መሞት ምልክቶች እንደሚኖሩ ተናገረ። ህዝቡ ፀሐይን፣ ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ማየት አልቻሉም፡፡ ሰሶስት ቀናት ምንም አይነት ብርሃን አይኖርም።
ነጎድጓድ እና መብረቅ ይከሰታል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል እንዲሁም ብዙ ከተሞች ይደመሰሳሉ።
አንዳንድ ሰዎች ሳሙኤልን አምነዋል፣ ነገር ግን አብዛኞቹ ኔፋውያን በእርሱ ተበሳጭተው ነበር። ድንጋዮችን ወረወሩ፣ ቀስቶችንም በእርሱ ላይ አስወነጨ ፉበት፡፡ ሳሙኤል በግንቡ ላይ እንዳለ ጌታ ጠብቆታል ድንጋዩም ሆነ ቀስቱ የትኛውም አላገኘውም።
ማንም ሳሙኤልን ለመምታት ባለመቻሉ፣ ብዙ ሰዎች በቃሉ አምነዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ ሰዎች አሁንም ተበሳጭተዋል። ሳሙኤልን ወስደው ሊያስሩት ሞክረዋል። ሳሙኤል ሸሸ እናም ወደ ቤቱ ሄደ። እርሱ ሰዎችን ማስተማሩን ቀጠለ።
በሳሙኤል ያመኑ ኔፋውያን ንሰሃ ገቡ በነቢዩ ኔፊም ተጠመቁ። በኢየሱስ አመኑ እና ሳሙኤል ስለ ኢየሱስ መወለድ የነገራቸውን ምልክት አዩ።