“ኢኖስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
“ኢኖስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች
ኢኖስ
ወደ ጌታ የቀረበ ታላቅ ጸሎት
ያዕቆብ ሰሌዳዎችን ለልጁ ኢኖስ ሰጠ። ኢኖስ ያዕቆብ እንዳደረገው ጻፈባቸው። አንድ ቀን ኢኖስ በጫካ ውስጥ ለማደን ሄደ። አባቱ ስለጌታ ያስተማረውን አስታወሰ። ያዕቆብ ጌታን መከተል ደስታ እንደሚያመጣ ኢኖስን አስተምሮት ነበር።
ኢኖስ አባቱ የተናገረው ደስታ እንዲሰማው ፈለገ። ወደ ጌታ ለመጸለይ ወሰነ። ቀኑን በሙሉ እስከ ለሊት ድረስ ጸለየ።
ጌታ ለኢኖስ ኃጢያቱ ይቅር እንደተባለለት ነገረው። ኢኖስ በጣም ደስ አለው። ኢኖስ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው እምነት ተባረከ።
ኢኖስ ኔፋውያንም ይህ ደስታ እንዲሰማቸው ፈለገ። መፀለዩን ቀጠለ። ኔፋውያንም ተመሳሳይ ደስታ ሊሰማቸው ይችል ዘንድ ጌታን ጠየቀ።
ጌታ ኔፋውያን ትእዛዛቱን ከጠበቁ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ለኢኖስ ነገረው። ኢኖስም ይህን በሰማ ጊዜ በጌታ ላይ ያለው እምነት ይበልጥ እየጠነከረ መጣ።
ኢኖስ እንደገና ጸለየ። ጌታን ላማናውያንን እንዲባርክ እና በሰሌዳዎቹ ላይ ያሉትን ጽሁፍ እንዲጠብቅ ጠየቀ። ላማናውያን ሰሌዳዎቹን እንዲያነቡ እና በጌታ እንዲያምኑ ፈልጎ ነበር። ጌታ ላማናውያን ጽሁፎቹን አንድ ቀን እንደሚያነቡ ለኢኖስ ቃል ገባለት።