በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኔፊ ወንድሞቹ እና ሌሂ


“ኔፊ ወንድሞቹ እና ሌሂ” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሔለማን 3–6

ኔፊ፣ ወንድሞቹ እና ሌሂ

ከሰማይ ድምፅን መስማት

ኔፊ፣ ወንድሞቹ  እና ሌሂ ሰዎችን እያስተማሩ፣ የላማናውያን ሠራዊት በአቅራቢያቸው እንደሠፈረ

ኔፊ እና ሌሂ ሁሉም ሰው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዲያውቅ የሚፈልጉ ወንድማማቾች ነበሩ። ኔፋውያን እና ላማናውያን ጦርነት ላይ ነበሩ፣ ነገር ግን ወንድማማቾቹ ከሁለቱም ቡድኖች የመጡ ሰዎችን ያስተምሩ ነበር። አንድ ቀን ሰዎችን ለማስተማር ሲጓዙ፣ የላማናውያን ሰራዊት ወደ እስር ቤት አስገቧቸው።

ሔለማን 3፥20–21፣ 374፥4–5፤ 145፥4–21

የላማናውያን ሠራዊት፣ ኔፊ እና ሌሂ ወዳሉበት እስር ቤት ሄዱ።

ከብዙ ቀናት በኋላ፣ ሠራዊቱ ኔፊን እና ሌሂን ለመግደል ወደ እስር ቤቱ መጣ።

ሔለማን 5፥22

ኔፊን እና ሌሂን በዙሪያቸው እሳት እና ብርሃን ከቧቸው እየጠበቃቸው፣ ወታደሮች ወድቀው እንዲሁም የደመና ጭጋግ እየታየ

ማንም ሰው ኔፊን እና ሌሂን ከመጉዳቱ በፊት፣ ዙሪያቸውን እሳት ከቧቸው ታየ። እሳቱ አላቃጠላቸውም። ይልቁንም እግዚአብሔር ጠበቃቸው። ከዚያም መሬቱ ተንቀጠቀጠ። የእስር ቤቱ ግንቦች ሊወድቁ ያሉ ይመስል ነበር። ብዙም ሳይቆይ፣ በእስር ቤቱ ውስጥ ያሉትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ የደመና ጭጋግ ሸፈነ። ሰዎቹ በጣም ፈሩ።

ሔለማን 5፥23–28

የደመና ጭጋግ ውስጥ የቆሙ ሰዎች ወደ ብርሃን ጨረር እየተመለከቱ

ከደመናው ጭጋግ በላይ ድምፅ መጣ። ልክ እንደ ሹክሹክታ ጸጥ ያለ ነበር፣ ነገር ግን ሰዎቹ በልባቸው ተሰማቸው። የእግዚአብሔር ድምፅ ነበር። እግዚአብሔር ንስሐ እንዲገቡ ነገራቸው።

ሔለማን 5፥29–30፣ 46–47

ወንዶች እና ሴቶች በደመናው ጭጋግ ውስጥ ቀና ብለው እየተመለከቱ

መሬቱ እና እስር ቤቱ ይበልጥ ተናወጡ። ድምፁ ዳግም መጥቶ ህዝቡ ንስሐ እንዲገባ ነገራቸው። ሰዎቹ ከደመናው እና ከፍርሃታቸው የተነሳ መንቀሳቀስ አቃታቸው።

ሔለማን 5፥31–34

አሚናዳብ ወደሚያበሩት እና ቀና ብለው ወደሚያዩት ኔፊ እና ሌሂ እየጠቆመ

ከህዝቡ መካከል አንዱ አሚናዳብ ይባላል። በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል ነበር። የኔፊ እና የሌሂ ፊት በደመቀ ሁኔታ ማብራት እንደጀመረ አየ። መላዕክትን ይመስሉ ነበር። ሰማይ ላይ ካለ ሰው ጋር እየተነጋገሩ ያሉ ይመስል ነበር። አሚናዳብ ሁሉም ሰዎች ኔፊን እና ሌሂን እንዲመለከቱ ነገራቸው።

ሔለማን 5፥35–39

ብዙ ወንዶች እና ሴቶች በደመና ጭጋግ ቀና ብለው እየጸለዩ

ሰዎቹ የጨለማውን ጭጋግ ለማስወገድ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አሚናዳብን ጠየቁት። አሚናዳብ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኢየሱስ የሚያውቀውን አካፈለ። ሰዎቹ ንስሐ እንዲገቡ፣ በኢየሱስ እምነት እንዲኖራቸው እና ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልዩ ነገራቸው። ሰዎቹ አሚናዳብን አዳመጡት። ጨለማው እስኪጠፋ ድረስ ጸለዩ።

ሔለማን 5፥40–42

ሰዎች በብርሃን እና በእሳት ተከበው እየጸለዩ

ከእግዚአብሔር የመጣው እሳት ህዝቡን ሁሉ ቢከባቸውም አላቃጣቸውም። ሰዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ እንዲሁም በጣም ደስተኞች ሆኑ። አስደናቂ ነገሮችን ተናገሩ። ድምፁ እንደገና መጣ። በኢየሱስ ባላቸው እምነት ምክንያት ሰላም እንዲኖራቸው ተናገራቸው። መላዕክት መጥተው ህዝቡን ጎበኙ።

ሔለማን 5፥43–49

ኔፊ እና ሌሂ እስር ቤቱን ለቀው እየወጡ፣ ህዝቡ እየተመለከተ

ኔፊ፣ ሌሂ እና ሁሉም ሰዎች እስር ቤቱን ለቀው ወጡ። በዕለቱ ያዩትንና የሰሙትን በመላ አገሪቱ ለብዙ ሰዎች ተናገሩ። አብዛኞቹ ላማናውያን አምነው ኢየሱስን ለመከተል መረጡ። በጦርነቱ መዋጋት አቆሙ። ከዚያ ይልቅ ሰዎች በኢየሱስ እንዲያምኑና ንስሐ እንዲገቡ ረዱ።

ሔለማን 5፥50–526፥1–6