በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢዩ ኔፊ


“ነቢዩ ኔፊ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሔለማን 6–11

ነቢዩ ኔፊ

ከጌታ ታላቅ ሀይልን መቀበል

ኔፋውያን ከሰዎች የሰረቋቸውን ያሽበረቁ ልብሶችን ለብሰዋል እና በእነርሱም ላይ ይስቃሉ

የጋዲያንተን ዘራፊዎች የተባሉ ቡድኖች የዛራሄምላን ከተማ አስተዳድረዋል። መጥፎ ነገሮችን በማድረግም እርስ በርሳቸው ሊረዳዱ ወሰኑ። ገንዘብን እና ስልጣንን ለማግኘት ሰዎችን ዘርፈዋል እና ጎድተዋል። አብዛኞቹ ሰዎች ዘራፊዎቹን ተቀላቀሉ። እነርሱ ባለጠጋ መሆንን ይሹ ነበር።

ሔለማን 6፣15–24፣ 38–39; 7፣4–5

ኔፊ በግንቡ ውስጥ ይንበረከካል እና ይጸልያል፣ እና ኔፋውያን ወደ እርሱ ይመለከታሉ

ነቢዩ ኔፊ በዛራሄምላ ውስጥ ኖረ። ህዝቡ የእግዚአብሔርን ተዛዛት ባለመከተላቸው ስለተበሳጨ ኔፊ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ህዝቡ እግዚአብሔር ያደረገለቸውን ሁሉ እንዲያስታውሱ ኔፊ ጠየቀ። ነገር ግን ከህዝቡ ብዙዎች አላደመጡም ። እነርሱ እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ይልቅ ይበልጥ ስለ ገንዘብ እና ስለ ስልጣን ይጨነቁ

ሔለማን 7፥1–22

ኔፊ በግንቡ ላይ ሆኖ ለህዝቡ ይናገራል፣ እና ህዝቡም በእርሱ ላይ ይጮሃሉ።

ኒፊ ለህዝቡ ስለዘራፊዎቹ አስጠነቀቃቸው። ንሰሃ መግባት እንዳለባቸው ተናገረ። አንዳንድ የኔፋውያን ዳኞች ከዘራፊዎቹ ጋር ተባበሩ። እነርሱ በኔፊ ተበሳጭተው ነበር እና እየዋሸ እንደሆነም ተናገሩ። ህዝቡም እንዲሁ በኔፊ ላይ እንዲበሳጩ ፈልገዋል።

ሔለማን 7፥22–298፥1–7

ኒፊ ይናገራል እና እጁንም ያንቀሳቅሳል።

ኔፊ እግዚአብሔር ለህዝቡ ብዙ ነገሮችን ይናገራል አለ። ኔፊ ሁሉም ነቢያት ስለኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት እንዳስተማሩ ተናገረ። ንሰሃ የማይገቡ ከሆነ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ነቢያት ህዝቡን ያስጠነቀቁ መሆኑን ተናገረ። ኢየሩሳሌም የጠፋች መሆኗን እንዲያስታውሱ ረድቷቸዋል።

ሔለማን 8፥11–25

ኔፊ ለህዝቡ ይናገራል፣ እና ህዝቡም ያደምጣሉ።

በቀጣዩ ቀን፣ ዳኞች ሊያታልሉት ኔፊን ጥያቄ ጠየቁት። ኔፊ በመካከላቸው ስላለው ክፋት ነገራቸው። አንዳንድ ሰዎች ኒፊን አመኑ እና ነቢይ መሆኑንም አወቁ።

ሔለማን 9፥19–41

ኔፊ ብቻውን ነው እና የተበሳጨም ይመስላል

ሌሎች አላመኑም። እያንዳንዳቸው ተነታረኩ እና ትተው ሄዱ። ኒፊ እግዚአብሔር ስላስተማረው ነገር አሰበ። በሰዎቹ ክፉ ስራ ምክንያት እርሱ አዝኖ ነበር፡፡

ሔለማን 10፥1-3

ኔፊ በግንቡ ውስጥ ይንበረከካል እና ይጸልያል፣ እና ብርሃንም በእርሱ ላይ ያበራ ነበር።

ጌታ ለኔፊ ተናገረ። ኔፊ ህዝቡን ስላስተማረ እርሱ ደስተኛ ነበር። ኔፊ እንዴት ታዛዥ የነበረ በመሆኑ ምክንያት፣ ጌታ በምድር እና በሰማይ ባሉ ነገሮች ሁሉ ላይ ልዩ ስልጣንን ሰጠው። ኔፊ ስልጣኑንም ሰዎች ንሰሃ እንዲገቡ ለመርዳት ብቻ እንደሚጠቀም ጌታ ያውቅ ነበር።

ሔለማን 10፥3–12

ኔፊ ለኔፋውያን ህዝብ ንግግር ያደርጋል፣ እና ህዝቡም ችላ ይሉት  ወይም በግልምጫ ይመለከቱት ነበር።

ኔፊ ወደ ህዝቡ እንዲመለስ እና ንሰሀ እንዲገቡ እንዲነግራቸው ጌታ ተናገረው። ኔፊም ወዲያውኑ ሄደ። ነገር ግን ህዝቡ በእርሱ ተበሳጩ እና አላደመጡትም።

ሔለማን 10፥11–15

ጠባቂዎች ኔፊን ይፈልጋሉ፣ እና ኔፊም ከእነርሱ ይኮበልላል

እነርሱም ኔፊን ወደእስር ቤት ለማስገባት ሞከሩ። ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ኔፊን እንዲሸሽ ረዳው።

ሔለማን 10፥15–17

ኔፊ እየነደደ ያለን ከተማ ይመለከታል

ኔፊ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማሩን ቀጠለ። ህዝቡ አሁንም አልሰሙትም። እርስ በርሳቸው መከራከር እና መፋለም ጀመሩ። ዘራፊዎቹ ፍልሚያውን አባባሱት። ወዲያውኑ፣ በየከተማው ጦርነት ሆነ። አያሌ ሰዎችም ተጎዱ ወይም ተገደሉ። ኔፊ አዝኖ ነበር። እርሱ ህዝቡ በጦርነት እንዲጠፋ አልፈለገም።

ሔለማን 10፥17–1811፥1–4

መሬቱ ደረቅ ነው፣ ምንም ነገር አይበቅልም፣ እና ውሃ አልነበረም፣ ኒፋውያን አዝነዋል እናም እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ

ህዝቡ እግዚአብሔርን ያስታውሱና ንሰሃ ይገቡ ዘንድ ኔፊ ታላቅ ረሃብ እንዲመጣ እግዚአብሔርን ጠየቀ። ለአያሌ አመታት ዝናብ አልነበረም። መሪቱ ደረቅ ነበር፣ እና እህልም ሊበቅል አልቻለም። ሰዎቹ ተርበው ነበር። በጦርነቱ መዋጋት አቆሙ እና እግዚአብሔርንም ማስታወስ ጀመሩ። ህዝቡ ንሰሃ ገቡ እና ዘራፊዎቹንም ማስወገድ ጀመሩ።

ሔለማን 11፥3–7፣ 9–10

ኔፊ ይጸልያል፣ ዝናብ ይዘንባል፣ እና ኔፋውያን ፈገግ አሉ እና እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

ህዝቡ ኔፊን ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ጠየቁት። ኔፊ ንሰሀ እንደገቡ ተመለከተ እና ዘራፊዎቹም አልነበሩም። እርሱ ጌታን ዝናብ እንዲልክ ጠየቀ። ጌታ የኔፊን ጸሎት መለሰ። ዝናብም መጣ፣ እህል ማብቀል ጀመረ። ህዝቡም እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ኔፊ ነቢይ እንደነበር አወቁ እና ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ሀይል ነበራቸው።

ሔለማን 11፥8–18