በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ አዲስ ቤት


“በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ አዲስ ቤት፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ አዲስ ቤት፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

2 ኔፊ 4–5

በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ አዲስ ቤት

ኔፋውያን እና ላማናውያን

በሌሂ ዙሪያ የተሰበሰቡ ቤተሰቦች

የሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ በቃል ኪዳን ምድር በቁጥር ማደግን ቀጠሉ። ልጆቻቸው የራሳቸው ልጆች ነበሯቸው። ሌሂ እያረጀ ነበር። ከመሞቱ በፊት፣ በቤተሰቡ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ባረካ። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሲጠብቁ፣ ጌታ እንደሚረዳቸው ነገራቸው።

2 ኔፊ 4፥3–12

ላማን እና ልሙኤል ኔፊን እየተመለከቱ

ሌሂ ከሞተ በኋላ፣ ኔፊ ህዝቡን መራ። ጌታን እንዲታዘዙ ነገራቸው። ላማን እና ልሙኤል ተናደዱ። በምትኩ እንዲመሩ ኔፊን ለመግደል ፈለጉ።

2 ኔፊ 4፥135፥1–4

የሚጓዙ ሰዎች ቡድን

ጌታ፣ ኔፊ ከቤተሰቡ እና ጌታን ሊከተሉ ይፈልጉ ከነበሩ ከማናቸውም ከሌሎች ጋር ከዚያ እንዲሄድ ነገረው። ለብዙ ቀናት ተጓዙ እና አዲስ የመኖሪያ ቦታ አገኙ።

2 ኔፊ 5፥1፣ 5–8

ሰዎች እያረሱ

ከኔፊ ጋር የሄዱት ኔፋውያን ተባሉ፣ እናም የቀሩት ላማናውያን ተባሉ። ኔፋውያን፣ ኔፊ እንዲመራቸው ጠየቁት። በትጋት ሰሩ። አረሱ፣ እንስሳትን አረቡ፣ እንዲሁም ቤተመቅደስ እና ሌሎች ህንፃዎችን ገነቡ። ካህናትና አስተማሪዎች ስለ ጌታ አስተማሯቸው፣ ህዝቡም ደስተኞች ነበሩ።

2 ኔፊ 5፥9–11፣ 13–17፣ 26–27