በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሳርያ


“ሳርያ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

“ሳርያ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

1 ኔፊ 2–35

ሳርያ

የሴት የእምነት ጉዞ

ሳርያ እና ሌሂ

ሳርያ ከቤተሰቧ ጋር በኢየሩሳሌም ኖረች። ባለቤቷ ሌሂ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር። አንድ ቀን፣ ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲሄድ ጌታ ነገረው።

1 ኔፊ 2፥1–3

ሳርያ ስትጸልይ

ሳርያ በእግዚአብሔር እምነት ነበራት። እሷና ቤተሰቧ ቤታቸውን ለቀው ወጡ። ከሌሂ ጋር ወደ ምድረ በዳ ለመሄድ ሲሉ ወርቃቸውን እና ብራቸውን ተው።

1 ኔፊ 2፥4–5

ሳርያ በምድረበዳ ውስጥ

ሳርያ እና ሌሂ ምግብ እና ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ወሰዱ። ለብዙ ቀናት ከተጓዙ በኋላ በምድረበዳ ለመኖር ድንኳን ተከሉ። ከዚያም መሠዊያ ሠሩ እንዲሁም ለሠጣቸው እርዳታ ጌታን አመሰገኑ።

1 ኔፊ 2፥4፣ 6–7፣ 15

ሳርያ ተጨንቃ፣  ሌሂ በሩቅ እያለ

አንድ ቀን ጌታ የሳርያን እና የሌሂን ወንድ ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው የነሐስ ሰሌዳዎችን እንዲያመጡ ጠየቃቸው። ሳርያ ልጆቿ ባልተመለሱ ጊዜ ፈራች። የሞቱ መስሏት ነበር። ሌሂ ሳርያን አፅናናት። ጌታ ወንድ ልጆቻቸውን እንደሚጠብቃቸው ማመንን መረጡ።

1 ኔፊ 3፥1–2፣ 4–65፥1–6

ሳርያ እና ሌሂ ልጆቻቸውን ሲቀበሉ።

ሳርያ ልጆቿ ከኢየሩሳሌም በተመለሱ ጊዜ በደስታ ተሞላች። አሁን ጌታ እንደጠበቃቸው አወቀች። ጌታ የጠየቀውን እንዲያደርጉ ኃይል እንደሚሰጣቸው አመነች። የሳርያ ቤተሰብ በሙሉ ተደስተው ነበር፣ እናም ጌታን አመሰገኑ።

1 ኔፊ 5፥7–9