በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
አልማ እና ህዝቡ


“አልማ እና ህዝቡ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሞዛያ 23–25

አልማ እና ህዝቡ

በአስቸጋሪ ጊዜያት ከእግዚአብሔር የሚመጣ ኃይል

አልማ እና ሌሎች ሰዎች ቤታቸውን እየተመለከቱ

አልማ እና ህዝቦቹ ውብ በሆነች ምድር ይኖሩ ነበር። ዘር ዘሩ እንዲሁም ቤት ሠሩ። አልማ የእግዚአብሔር ካህን ነበር። ህዝቡ እርስ በርስ እንዲዋደድ አስተማረ። ሰዎቹ አልማን ሰሙ፣ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ጠበቁ። ቤተሰቦቻቸው ትልቅ ሆኑ፣ ከተማም ሠሩ።

ሞዛያ 23፥4–5፣ 15–20

አልማ ላማናውያንን እያናገረ

አንድ ቀን፣ የላማናውያን ሰራዊት መጣ። የት እንዳሉ አያውቁም ነበር። ላማናውያን፣ አልማ ወደ ቤታቸው የሚወስዳቸውን መንገድ እንዲያገኙ ከረዳቸው የአልማን ህዝቦች እንደሚተው ቃል ገቡ። አልማ ላማናውያን እንዴት ወደ ምድራቸው መመለስ እንደሚችሉ አሳያቸው።

ሞዛያ 23፥25፣ 30፣ 36–37

አሙሎን እና ጠባቂዎች አልማን እና ህዝቡን እየጠበቁ

ላማናውያን የገቡትን ቃል ሳይጠብቁ ቀሩ። ይልቁንም፣ መሬቱን በመቆጣጠር ጠባቂዎች የአልማን ሰዎች እንዲጠብቁ አደረጉ። እንዲሁም አሙሎን የሚባል ኔፋዊ በአልማ ህዝብ ላይ እንዲነግስ አደረጉ። አሙሎን የሐሰተኛ ካህናት መሪ ነበር። እሱና ካህናቱ የእግዚአብሔርን ነቢይ ገደሉ፣ እንዲሁም ሌሎች ብዙ መጥፎ ድርጊቶችን ፈጸሙ።

ሞዛያ 17፥12–1323፥31–32፣ 37–3924፥9

አሙሎን ተናድዶ

አሙሎን በአልማ ተናደደ። የአልማን ህዝቦች በጣም ከባድ ስራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፣ ለእነርሱም ክፉ ነበር። ይህ ለአልማ ህዝቦች አስቸጋሪ ነበር።

ሞዛያ 24፥8–9

አልማ እየጸለየ፣ ከጀርባው አሙሎን ተቆጥቶ

እነርሱም እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ጸለዩ። አሙሎን ጸሎታቸውን እንዲያቆሙ ነገራቸው። የሚጸልይ ሁሉ ይገደላል አለ።

ሞዛያ 24፥10–11

አልማ እና አንዲት ሴት ሽማግሌን እንዲቆም እየረዱ

አልማ እና ህዝቡ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መጸለይን አቆሙ። ይልቁንም በልባቸው ጸለዩ። እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰማ። አጽናናቸው እንዲሁም እንዲያመልጡ እንደሚረዳቸው ቃል ገባላቸው። እግዚአብሔር ከባዱ ስራቸው ቀላል ሆኖ እንዲሰማቸው አደረገ። ሰዎቹ እግዚአብሔርን ሲሰሙ ታጋሾች እና ደስተኞች ሆኑ። እርሱ እየረዳቸው እንደሆነም አወቁ።

ሞዛያ 24፥12–15

አልማ ህዝቡን በምሽት እየመራ

የአልማ ሰዎች በእግዚአብሔር ታመኑ እንዲሁም በእርሱ ላይ ታላቅ እምነት ኖራቸው። አንድ ቀን እግዚአብሔር የመሄጃ ጊዜያቸው እንደደረሰ ነገራቸው። በዚያ ምሽት፣ አልማ እና ህዝቡ ተዘጋጁ። እንስሶቻቸውንና ምግባቸውን ሁሉ ሰበሰቡ። በማለዳ፣ እግዚአብሔር ላማናውያን ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለባቸው። ከዚያም አልማ እና ህዝቡ አመለጡ፤ ቀኑን ሙሉም ተጓዙ።

ሞዛያ 24፥16–20

አልማ እና ህዝቡ ዛራሔምላን እየተመለከቱ

በዚያ ምሽት ሁሉም ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ። እግዚአብሔር ብቻ ሊረዳቸው እንደሚችል ያውቁ ነበር። ለብዙ ቀናት ከተጓዙ በኋላ ወደ ዛራሔምላ ምድር መጡ። ኔፋውያን ተቀበሏቸው፣ አልማም በኢየሱስ ክርስቶስ ስለማመን ሁሉንም ሰው አስተማረ። ብዙ ሰዎች አምነው ተጠመቁ።

ሞዛያ 24፥20–2525፥14–24