በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የላማናውያን ሁሉ ንጉስ


“የላማናውያን ሁሉ ንጉስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“የላማናውያን ሁሉ ንጉስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

አልማ 2022–23

የላማናውያን ሁሉ ንጉስ

ስለጌታ ለመማር መፈለግ

ንጉሱ በላሞኒ እና አሞን ተናድዷል

ላማናውያን በሌሎች ንጉሶቻቸው ሁሉ ላይ የሚገዛ ንጉስ ነበራቸው። እርሱም የንጉሥ ላሞኒ አባት ነበር። ኔፋውያን ጠላቶች እንደሆኑ ያስብ ነበር። አንድ ቀን፣ ላሞኒን ከአሞን ጋር አየው። ንጉሡ፣ ከኔፊያዊ ጋር ምን እንደሚያደርግ ላሞኒን ጠየቀው። የአሞንን ወንድሞች ከእስር ቤት ለማስወጣት እየሄዱ እንደሆኑ ላሞኒ ለንጉሱ ነገረው።

ሞዛያ 10፥11–17አልማ 20፥1–12

ንጉሱ እየተናገረ

ንጉሱ ተናድዶ ነበር። ኒፋውያን ከላማናውያን ለለመስረቅ ሲሉ እየዋሹ ናቸው ብሉ አስቦ ነበር። አሞንን እንዲገድል እና ከእርሱ ጋር እንዲሄድ ለላሞኒ ነገረው።

አልማ 20፥13–14

ላሞኒ እየተናገረ

ላሞኒ አሞንን አይገድልም። አሞን እና ወንድሞቹ የእግዚአብሔር ነቢያት እንደሆኑ ለንጉሱ ነገረው። የአሞንን ወንድሞች እንደሚረዳም ተናገረ።

አልማ 20፥15

ንጉሱ እና አሞን እየተጣሉ

ንጉሱ ላሞኒን ለመውጋት ሰይፉን አወጣ፣ ነገር ግን አሞን አስቆመው። ንጉሱ በምትኩ አሞንን አጠቃው። አሞን እራሱን ተከላከለ። ንጉሱ መዋጋት እንዳይችል የንጉሱን ክንድ ጎዳው። አሞን በጣም ጠንካራ ስለነበረ ንጉሱ ፈራ። በህይወት እንዲኖር ከፈቀደለት የግዛቱን ግማሹን እንደሚሰጠው ለአሞን ቃል ገባለት።

አልማ 20፥16–23

አሞን ንጉሱን ሲያነጋግረው

አሞን መንግሥቱን አልፈለገም። ይልቁንም ንጉሡ ወንድሞቹን ከእስር እንዲፈታቸው ጠየቀው። በላሞኒ ላይ መቆጣቱን እንዲያቆምም ንጉሱን ጠየቀው። አሞንም ላሞኒ የተሻለ ነው ብሎ በሚያስብበት መንገድ እንዲገዛ ንጉሱ መፍቀድ እንደሚገባው ተናገረ።

አልማ 20፥24

ንጉሱ እያሰበ

ንጉሱ፣ አሞን ላሞኒን ምን ያህል እንደሚወደው ሲያይ ተደነቀ። አሞን የጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ተስማማ።

አልማ 20፥25–27

ንጉሱ በመደሰት ከላሞኒና ከአሞን ጋር እየተነጋገረ

ንጉሱ አሞን እና ላሞኒ ስለእግዚአብሔር ስለነገሩት ይበልጥ ለመማር ፈለገ። አሞን እና ወንድሞቹ እንዲመጡና እንዲያስተምሩት ጠየቀ።

አልማ 20፥27

አሞን እና ላሞኒ የአሞን ወንድሞችን እየረዱ

አሞንና ላሞኒ ወደ ሚዶኒ ምድር ሄዱ። የአሞን ወንድሞች በዚያ በእስር ላይ ነበሩ። በገመድ ታስረው ነበር እንዲሁም ምግብና ውሃ አልተሰጣቸውም ነበር። ላሞኒ፣ የሚዶኒ ገዥ የአሞንን ወንድሞች በነጻ እንዲለቃቸው አሳመነው።

አልማ 20፥28–30

አሮን በንጉሱ በፊት ተንበርክኮ

እነርሱ ነጻ ከሆኑ በኋላ፣ የአሞን ወንድሞች ወደ ላሞኒ አባት ሄዱ። ለንጉሱ ሰገዱ እንዲሁም የእርሱ አገልጋዮች ለመሆን ጠየቁ። ንጉሱም እምቢ አለ። ይልቁንም እነርሱ ስለወንጌል እንዲያስተምሩት ፈለገ። ከወንድሞቹ አንዱ አሮን ይባል ነበረ። ቅዱሳት መጻህፍትን ለንጉሱ አነበበለት እንዲሁም ስለእግዚአብሔር እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተማረው።

አልማ 22፥1–14

አሮን እና ንጉሱ እየጸለዩ

ንጉሱ አሮንን አመነው። እግዚአብሔርን ለማወቅ መንግስቱን ሁሉ እንደሚተው ተናገረ። ምን ማድረግ እንዳለበት አሮንን ጠየቀው። ንስሀ እንዲገባ እና በእምነት ወደእግዚአብሔር እንዲጸልይ አሮን ለንጉሱነገረው። ንጉሱ ለኃጢያቶቹ በሙሉ ንስሀ ገባ እንዲሁም ጸለየ።

አልማ 22፥15–18

ንጉሱ መሬት ላይ ወድቆ

ንጉሱም መሬት ላይ ወደቀ። የንጉሱ አገልጋዮች ለንግስቲቱ ለመንገር ሮጠው ሄዱ።

አልማ 22፥18–19

ንግስቲቱ ተናደደች

ንግስቲቱ መጣች እናም ንጉሡን መሬት ላይ አየችው። አሮን እና ወንድሞቹ ንጉሱን እንደገደሉት አሰበች። ንግስቲሱ ተናድዳ ነበር።

አልማ 22፥19

ንግስቲቱ ወደአሮን እየጠቆመች

ንግስቲቱ፣ ሠራተኞቿአሮንን እና ወንድሞቹን እንዲገድሉ ነገረቻችው። ነገር ግን ሰራተኞቹ ፈርተው ነበር። አሮን እና ወንድሞቹ በጣም ጠንካራ ናቸው አሉ። አሁን ንግስቲቱ ፈራች። በከተማ ውስጥ ላለው ህዝብ ምን እንደተከሰተ እንዲነግሩ አገልጋዮቹን ላከቻቸው። ህዝቡ አሮንን እና ወንድሞቹን እንደሚገድሉ ተስፋ አደረገች።

አልማ 22፥19–21

አሮን ንጉሱ እንዲቆም ሲረዳ

አሮን ህዝቡ እንደሚናደዱ አውቆ ነበር። ንጉሱ እንዳልሞተም ያውቅ ነበር። እርሱም ንጉሱ እንዲቆም ረዳው። ንጉሱ ጥንካሬውን አገኘና ቆመ። ንግስቲቱ እና አገልጋዮቹ ተደነቁ።

አልማ 22፥22–23

ንጉሱ ንግስቲቱን እና አገልጋዮችን እያስተማረ

ንጉሱ ንግስቲቱን እና አገልጋዮቹን ስለኢየሱስ አስተማረ። ሁሉም በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ንጉሱ ህዝቦቹ ሁሉ ስለኢየሱስ እንዲማሩ ፈለገ። አሮንና ወንድሞቹ በመንግሥቱ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ወንጌልን እንዲያስተምሩ ህግ አወጣ። ህዝቡንም አስተማሩ እንዲሁም በምድሪቱ ለካህናትና ለመምህራን የአገልግሎትጥሪ ሠጡ።

አልማ 22፥23–2723፥1–4