በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ


“ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

1 ኔፊ 3

ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ

የነሐስ ሰሌዳዎች ሰኢዳዎችን የማግኘት ጉዞ

ቤተሰብ ድንኳንን ሲተክሉ

ሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ በምድረበዳ ተጓዘ። በነሐስ ሰሌዳዎች ላይ ስለተጻፉት ቅዱሳት መጻህፍት ጌታ ለሌሂ በህልም ነገረው። ላባን በሚባል ሰው ሰው እጅ ነበሩ። ቤተሰቡ የነሐስ ሰሌዳዎቹን በጉዞአቸው ይዘው መሄድ እንዳለባቸው ጌታ ለሌሂ ነገረው።

1 ኔፊ 3፥1–3፣ 19–20

ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር ሲነጋገር

ሌሂ የነሐስ ሰሌዳዎቹን ለማምጣ ልጆቹን መልሶ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲልክ ጌታ ነገረው። የኔፊ ወንድሞች አጉረመረሙ። ያንን ማድረግ ከባድ እንደነበረ ለሌሂ ነገሩት። ለመሄድ አልፈለጉም ነበር።

1 ኔፊ 3፥4–5

ሳርያ፣ ሌሂ፣ እና ኔፊ ሲነጋገሩ

ይህም በጣም ከባድ ነገር ነበር፣ ነገር ግን ኔፊ ታዛዥ ለመሆን ፈለገ። ጌታ እርሱን እና ወንድሞቹን እንደሚረዳ አወቀ። ኔፊ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለስና የነሐስ ሰሌዳዎቹን እንደሚያመጣ ለሌሂ ነገረው።

1 ኔፊ 3፥6–8

ወንድማማቾች በኢየሩሳሌም አጠገብ

ላማን፣ ልሙኤል፣ ሳም እና ኔፊ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። በዚያም ሲደርሱ፣ ላማን ወደ ላባን ቤት እንዲሄድ እና ነሐስ ሰሌዳው እንዲሰጠው እንዲጠይቅ ወሰኑ።

1 ኔፊ 3፥9–11

ላባን እና ላማን

ላማን ነሐስ ሰሌዳዎች እንዲሰጡት ሲጠይቅ፣ ላባን ወንበዴ ነህ አለው። ላባንም ላማንን እገድላለሁ አለ።

1 ኔፊ 3፥11–13

ላማን ከጠባቂዎች እየሸሸ

ላማን ሸሸና ለወንድሞቹ ምን እንደተከሰተ ነገራቸው።

1 ኔፊ 3፥14

ኔፊ ወንድሞቹን ሲያናግር

አራቱ ወንድማማቾች አዘኑ። ላማን፣ ልሙኤል፣ እና ሳም በምድረበዳ ውስጥ ወዳሉት ወላጆቻቸው ለመመለስ ፈለጉ፣ነገር ግን ኔፊ አንድ ሀሳብ ነበረው። የነሐስ ሰሌዳዎቹን ለማግኘት ከላባን ጋር ልውውጥ ማድረግ እንደሚችሉ ተናገረ። በከተማ ውስጥ ወደነበረው ቤታቸው ተመልሱና ወርቃቸውን እና ብራቸውን ለመለዋወጥ ሰበሰቡ።

1 ኔፊ 3፥14–16፣ 22–24

ወንድሞቹ ከጠባቂዎች ሲሸሹ

ወርቁን እና ብሩን ለላባን ሲያሳዩት፣ ሁሉንም ፈለገ። ነገር ግን የነሐስ ሰሌዳዎችን ለእነርሱ ለመስጠት አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ፣ የእነርሱን ወርቅ እና ብር ለመውሰድ ይችል ዘንድ አገልጋዮቹ ወንድማማቾቹን እንዲገድሉ ነገራቸው።

1 ኔፊ 3፥16፣ 23–25

ወንድማማቾች ከጠባቂዎች እየተደበቁ

አራቱ ወንድማማቾች ወርቃቸውን እና ብራቸው ትተው ህይወታቸውን ለማዳን ሸሹ። የላባን አገልጋዮች ሊይዟቸው አልቻሉም። ወንድማማቾቹ ዋሻ ውስጥ ተደበቁ።

1 ኔፊ 3፥26–27

ላማን እና ልሙኤል በኔፊና ሳም ተናደዱ።

ከእነዚህ ብዙ ከባድ ነገሮች በኋላ፣ ላማን እና ልሙኤል በበኔፊ በጣም ተናድደው ነበር። እነርሱ ኔፊን እና ሳምን በበትር መቷቸው።

1 ኔፊ 3፥28

መልአክ ላማን እና ልሙኤልን ሲያነጋግር

በድንገትም፣ መልአክ መጣና ኔፊን ለምን እንደሚመቱት ጠየቃቸው። መልአኩም ኔፊ፣ እነርሱን እንዲመራ እንደተመረጠ ነገራቸው። ከዚያም፣ መልዓኩ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ነገራቸው። ጌታ የነሐስ ሰሌዳዎቹን ማምጣት እንዲችሉ መንገድ ያዘጋጅላቸዋል።

1 ኔፊ 3፥29