በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ሕዝቡን ጎበኘ


“ኢየሱስ ህዝቡን ይጎበኛል፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3 ኔፊ 7–11

ኢየሱስ ሕዝቡን ጎበኘ

እያንዳንዱን ሰው በእርሱ እንዲያምን መርዳት

አንድ ቤተሰብ ወደ ሰማይ ይመለከታል፣ እና ሌሎች ሰዎች በከተማው ይነታረካሉ

ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ነቢያት ሊሰሙ አልቻሉም። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ነቢያት ያስተማሯቸውን አምነዋል። እነዚህ አማኖች የኢየሱስ ክርስቶስን የሞቱን ምልክቶች ጠብቀው ነበር።

3 Nephi 7፣16–26; 8፣1–4

መብረቅ፣ ማእበል፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እና እሳት አንዲትን ከተማ ያቃጥላታል

በኢየሩሳሌም ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ፣ ምልክቶቹ ጀምረዋል። በአሜሪካ ማእበል፣ የምድር መንቀጥቀጥ፣ እና ለሶስት ሰአታት እሳት ነበር። ከተሞች ጠፍተዋል፣ እና አያሌ ሰዎችም ሞተዋል። ከዚያም ለሶስት ቀናት ሙሉ ጨለማ ነበር።

3 ኔፊ 8፥5–19፣ 19፣23

አንዳንዶች እሳትን ለማንደድ ይሞክራሉ፣ ነገር ግን አይበራም እና ሁሉም ነገር ጨለማ ነው

ጨለማው ጥቅጥቅ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች ፀሀይን፣ ጨረቃን፣ ወይም ክዋክብትን መመልከት አልቻሉም። እሳትን ማንደድም ሆነ ሻማን መለኮስ አልቻሉም።

3 ኔፊ 8፥20–23

አሁንም ጨለማ ነው፣ ሰዎች በፍርስራሽ ውስጥ ይረዳዳሉ፣ እና አንድ ሰው ይጮሃል እና ይጸልያል

በህይወት ያሉ አብዛኖቹ ሰዎች አዝነዋል እና ፈርተዋል። በወቅቱ ንሰሃ ባለመግባታቸው ይጮሃሉ እና አዝነዋል።

3 ኔፊ 8፥24–25

አሁንም ጨለማ ነው፣ ሰዎች ወደ ሰማይ ይመለከታሉ፣ የሚጸልየው ሰውም ማልቀሱን አቁሟል

በድንገትም፣ አንድ ድምጽ ሰሙ። የሚያናግራቸው ኢየሱስ ነበር። ንሰሃ የገባውን ሁሉንም ለመፈወስ ቃል ገባ። ኢየሱስም ሞቶ እንደነበር እና ሰዎችን ሁሉ ለመርዳት ዳግም ተመልሶ በህይወት እንደመጣ ነገራቸው። ሰዎቹ በጣም ስለተደነቁ ማልቀስ አቆሙ፡፡ በምድሪቱም ላይ ለብዙ ሰዓታት ፀጥታ ነበር።

3 ኔፊ 910፥1–2

ቤተሰቦች ክብ ሰርተው በፈገግታ ተቀምጠዋል፣ እና ከዚህ ወዲያ ጨለማ አይኖርም

ኢየሱስ እንደገና ተናገረ። ሰዎች እርሱን ለመከተል ከመረጡ እንደሚረዳቸው ተናገረ። ጨለማው ራቀ፣ ምድርም መናወጧን አቆመች። ህዝቡ ደስተኛ ነበር እና ኢየሱስን አወደሱ።

3 ኔፊ 10፥3–10

ብዛት ያለው ህዝብ በቤተመቅደስ ዙሪያ ተሰብስቧል፣ እና የጨለመው ደመና ብርሃን ማሳየት ሲጀምር ወደ ሰማይ ያማትራሉ

ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በለጋስ ምድር ባለች ቤተመቅደስ አያሌ ሰዎች መጥተዋል። ስለኢየሱስ እና ስለሞቱ ምልክቶች ማውራት ጀምረዋል። ሲነጋገሩም፣ ከሰማይ ረጋ ያለ ድምጽ ሰሙ፡፡ በመጀመሪያ ሊገባቸው አልቻለም ነበር፡፡ በድጋሚም ድምጹን ሰሙ።

3 Nephi 8፣5; 10፣18; 11፣1–4

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ይወርዳል፣ እና ህዝቡም ደስተኛ ናቸው እና ተቀብለውታል

ድምጹን ለሶስተኛ ጊዜ ሲሰሙ፣ ወደ ሰማይ መመልከት ጀመሩ። ያም የሚናገረው የሰማይ አባት ነበር። ለህዝቡም ልጁን እንዲያዩት እና እንዲሰሙት ነገራቸው። ከዚያም ህዝቡ ነጭ መጎናጸፊያ ያደረገ ሰው ከሰማይ ሲወርድ ተመለከቱ።

3 ኔፊ 11፥5–8

ኢየሱስ ክርስቶስ ከህዝቡ መሃል ቆሟል፣ እና ህዝቡም ወደ እርሱ እየመጡ በመዳፉ ላይ ያሉትን የችንካር ምልክቶች ይዳስሳሉ።

ከህዝቡም መካከል የቆመው ሰው እንዲህ አለ፣ “እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ።” ህዝቡም ወደ መሬት ወደቁ። ኢየሱስም እርሱ ለሁሉም ሰው እንደተሰቃየ እና እንደሞተም ነገራቸው። እርሱም ለህዝቡ በእጁ፣ በእግሩ እና በጎኑ ላይ ያሉትን ምልክቶች እንዲዳስሱ ስለዚህም እርሱ የዓለም ሁሉ አዳኝ መሆኑን ማወቅ እንዲችሉ ጋበዛቸው።

3 ኔፊ 11፥8–14

ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተመቅደስ ደረጃ ተቀምጧል፣ እና ህዝቡም ወደ እርሱ መጥተዋል እና በመዳፉ ላይ ያሉትን የምስማር ምልክቶች ይዳስሳሉ።

ህዝቡም አንድ በአንድ ወደ ኢየሱስ መጥተዋል። በገዛ ዐይኖቻቸው እና በእጆቻቸው በእጆቹ፣ በእግሮቹ፣ እና በጎኑ ያሉትን ምልክቶች ዳስሰዋል። ነቢያት ይመጣል ብለው የተናገሩለት እርሱ እንደሆነ ሁሉም አውቀዋል። እርሱ የዓለም አዳኝ እንደሆነ አውቀዋል። ህዝቡም በኢየሱስ እግር ስር ወደቁ እና አመለኩት።

3 ኔፊ 11፥15–17