“ጌዴዎን፣ አልማ እና ኔሆር፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
“ጌዴዎን፣ አልማ እና ኔሆር፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች
ጌዴዎን፣ አልማ እና ኔሆር
በእግዚአብሔር ቃል እውነትን መከላከል
ኔፋውያን ወጣቱ አልማ ዋና ዳኛቸው እንዲሆን መረጡት። ደግሞም አልማ የቤተክርስቲያኗ ሊቀ ካህን ነበር።
ኔሆር የሚባል አንድ ሰው፣ ህዝብን እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ብሎ የሚጠራውን ማስተማር ጀመረ። ነገር ግን ሕዝቡን ያስተማረው እግዚአብሔርን መታዘዝ እና ንስሀ መግባት እንደማያስፈልጋቸው ነበር።
ብዙ ሰዎች ኔሆር ይናገር የነበረውንወደዱት እንዲሁም አመኑት። ሰዎች ገንዘብ እንዲሰጡት እና እንዲያሞግሱት ይፈልግ ነበር። እርሱ ከሌሎች በላይ የተሻለ እንደሆነ ያስብ ነበር። የራሱን ቤተክርስቲያን መሠረተ፣ እንዲሁም ብዙ ሰዎች እርሱን አዳመጡ።
አንድ ቀን፣ ኔሆር ጌዴዎን ከሚባል አንድ ሽማግሌ ሰው ጋር ተገናኘ። ጌዴዎን በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪ ነበር እንዲሁም ብዙ መልካም ነገሮችን አድርጎ ነበር። ኔሆር ሰዎች ቤተክርስቲያኗን እንዲክዱ ይፈልግ ነበር፣ ስለዚህ ከጌዴዎን ጋር ተከራከረ። ጌዴዎን ኔሆር የሚያስተምረው ውሸት እንደሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በመጠቀም አሳየ። ኔሆር ተናደደ! ጌዴዎንን በጎራዴ ገደለው።
ህዝቡ፣ ኔሆር ይፈረድበት ዘንድ ወደ አልማ ወሰዱት ኔሆር ያደረገውን ለመከላከል ሞከረ። መቀጣት አልፈለገም ነበር።
አልማ የኔሆር ትምህርቶች ትክክል እንዳልሆኑ እና ሕዝብን ሊጎዱ እንደሚችሉ ተናገረ። አልማ ሕጉን ተከተለ። ኔሆር ጌዴዎንን ስለገድለ፣ ኔሆርም ተገደለ።
ከመሞቱ በፊት፣ ኔሆር ዋሽቶ እንደነበረ ለህዝቡ ነገራቸው። የእግዚአብሔርን ቃል አላስተማረም። ምንም እንኳን ኔሆር እንደተሳሳተ ቢናገርም፣ ብዙ ሰዎች የእርሱን ምሳሌ ተከተሉ። ውዳሴና ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ሰዎችን ዋሹ። ሌሎች ሰዎች ግን አልማን አዳመጡት። ድሆችን ይንከባከቡ እና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ይጠብቁ ነበር።