በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሻምበል ሞሮኒ እና ፓሆራን


“ሻምበል ሞሮኒ እና ፓሆራን፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 59–62

ሻምበል ሞሮኒ እና ፓሆራን

ከእግዚአብሔር ጥንካሬ

ካፕቴን ሞሮኒ በትኩረት ይመለከታል፣ እና ደክሞታል እና ቁስለኛ ወታደሮችም ያርፋሉ

ኔፋውያን እና ላማናውያን በጦርነት ውስጥ ነበሩ። ካፒቴን ሞሮኒ የኔፋውያን ጦር መሪ ነበር። የኔፋውያን መሪዎች በቂ ወታደሮችን ወይም ምግብ አልላኩም። ሞሮኒ ተበሳጭቷል እና ለኔፋውያን መሪ ለፓሆራን ደብዳቤ ጻፈ።

አልማ 59፧3–1360፟፣1፧3–5

ሻምበል ሞሮኒ ደብዳቤ ይጽፋል።

በደብዳቤውም ሞሮናይ ፓሆራንን እርዳታን ለምን እንዳልላከ ጠየቀው። ሞሮኒ ፓሆራን ስለህዝቡ ግድ የሌለው እና ስልጣንን ብቻ የሚፈልግ መሰለው። ሞሮኒ ህዝቡ ነጻ እንዲሆኑ ፈልጓል።

አልማ 60

ፓሆራን የሻምበል ሞሮኒን ደብዳቤ ያነባል እና ያዘነም ይመስላል

ፓሆራን ሰራዊቱ እርዳታ ስላልነበረው አዝኗል። ሞሮኒንን ሊረዳ ፈልጓል፣ ነገር ግን አልቻለም። አንዳንድ ኔፋውያን ከእርሱ ጋር ይዋጉ ነበር።

አልማ 61፥1–4

ኔፋውያን ያሸበረቁ ልብሶችን ለብሰው በከተማው ግንብ ላይ ቆመዋል እና ይጮሃሉ

እነዚያ ኔፋውያን የንጉስ-ሰዎች ይባሉ ነበር። ስልጣንን ለራሳቸው ይፈልጉ ነበር እና በህዝቡም ላይ ሊሰለጥኑ ይፈልጉ ነበር። መንግስትንም ከፓሆራን ተቀብለዋል።

አልማ 51፥561፥ 3–5፣ 8

ፓሆራን ደብዳቤን ይጽፋል እና ካምፑንም ይጠብቃል።

ፓሆራን ሊረዳቸው ስለሚፈልግ ኔፋውያንን በመምራት መቀጠልን ፈልጓል። እንደ ሞሮኒ፣ ኔፋውያን እግዚአብሔርን እንዲከተሉ እና ነጻነታቸውን እንዲጠብቁ ፈልጓል። ከማንም ጋር መዋጋት እንዳልነበረባቸው ተመኝቷል። ነገር ግን ህዝቡን በነጻነት ለማቆየት የሚረዳ ከሆነ ለመዋጋት ፈቃደኛ ነበር።

አልማ 61፥9–14፣ 19–20

ፓሆራን ከኔፊ ህዝብ ጋር ይነጋገራል።

ፓሆራን ኔፋውያን ቤተሰቦቻቸውን፣ እና እግዚአብሄርን የማምለክ ነጻነታቸውን ለመከላከል በውጊያው እንዲረዱት ኔፋውያንን ጠይቋል። ትክክል ለሆነው ነገር ለመዋጋት በሚመርጡበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን አውቋል። አያሌ ኔፋውያን ሀገራቸውን ለመከላከል ፓሆራንን ለመርዳት መጥተዋል።

አልማ 61፥5–7፣ 1–15

ፓሆራን ደብዳቤ እየጻፈ

ፓሆራን ለሞሮኒ ደብዳቤ ጽፋል። እርሱ በሞሮኒ አልተበሳጨም። ሲካሄድ የነበረውን በሙሉ ለሞሮኒ ተናግሯል። እርሱ ሞሮኒ እንዲመጣ እና የንጉስ-ሰዎችን እንዲወጋለት ጠይቋል። እነርሱ እግዚአብሔርን ቢከተሉ፣ መፍራት እንደማይገባቸው ፓሆራን ያውቅ ነበር። እግዚአብሔር ይጠብቃቸው እና ይረዳቸው ነበር።

አልማ 61፥9፣ 14-21

ሻምበል ሞሮኒ የነጻነት አርማውን ያነሳል እና በኔፋውያን መካከል በሰልፍ ይጓዛል።

ሞሮኒ በፓሆራን እምነት ምክንያት በተስፋ ተሞልቷል። ነገር ግን አንዳንድ ኔፋውያን የራሳቸውን ህዝብ በመውጋታቸው እና እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸው አዝኗል። ሞሮኒ ሰራዊትን ያዘ እናም ፓሆራንን ለመርዳት ሄደ። እርሱ በሄደበት በየትኛውም ስፍራ የነጻነት አርማውን ያነሳ ነበር። በሺህዎች የሚቆጠሩ ኔፋውያን ነጻነታቸውን ለመከላከል ለመዋጋት ወስነዋል።

አልማ 62፥1–5

ሻምበል ሞሮኒ እና ፓሆራን ፈገግ ይላሉ እና ወደ አንድ ካርታ ይመለከታሉ።

ሞሮኒ እና ፓሆራን በሰራዊቶቻቸው የንጉሱን ሰዎች ድል ነሱ። ፓሆራን እንደገና የኔፋውያን ጦር መሪ ሆነ። ሞሮኒ የኔፋውያንን ሰራዊት እንዲረዱ አያሌ ሰዎችን ላከ። በተጨማሪም እርሱ ለሰራዊቱ ምግብን ላከ። አሁን በብዙ ውጊያ በማሸነፋቸው፣ ኔፋውያን አንድ ሆነዋል። እነርሱ ከሌማናውያን አያሌ የኔፋውያንን ከተሞች ተረክበዋል።

አልማ 62፥6–32