“አልማ፣ አሙሌቅ እና ዚኤዝሮም፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
አልማ፣ አሙሌቅ እና ዚኤዝሮም
በእግዚአብሔር ለማመን እና ለመታዘዝ መምረጥ
አልማ ብዙ የቤተክርስቲያን አባላት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እየታዘዙ እንዳልሆኑ ተመለከተ። ስለዚህ አልማ የእግዚአብሔርን ቃል ከከተማ ወደ ከተማ እያስተማረ ሄደ። ብዙ ሰዎች ንስሃ ገቡ። ከዚያም አልማ አሞኒሀ ወደምትባል ከተማ መጣ። በዚያ ያሉት ሰዎች የሚለውን አላዳመጡም። በእርሱ ላይ ተፉበትም ከከተማም አባረሩት።
አልማ ከተማዋን ለቆ ሲወጣ አዘነ። ለህዝቡ ተጨንቆ ነበር። ከዚያም አንድ መልአክ ወደ እርሱ መጣ። መልአኩ እግዚአብሔርን ስለታዘዘ ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል ለአልማ ነገረው። መልአኩም አልማ ወደ ከተማው ተመልሶ ህዝቡን እንዲያስጠነቅቅ ነገረው። እነርሱ ንስሐ ካልገቡ ይጠፋሉ። አልማ በፍጥነት ተመለሰ።
አልማ ወደ ከተማው ሲመጣ፣ በጣም እርቦት ነበር። ለብዙ ቀናት ጾሞ ነበር። አልማ አሙሌቅ የሚባልን ሰው ምግብ እንዲሰጠው ጠየቀው።
አሙሌቅ ስላየው ራዕይ ለአልማ ነገረው። በዚህም ራዕይ፣ አንድ መልአክ፣ አልማ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ ለአሙሌቅ ነገረው። አሙሌቅ አልማን ለመርዳት ፈለገ።
አሙሌቅ አልማን ወደ ቤቱ ወሰደው እና የሚበላውን ምግብ ሰጠው። አልማ በአሙሌቅ ቤት ለብዙ ቀናት ቆየ። እግዚአብሔር አሙሌቅንና ቤተሰቡን ባረካቸው። በኋላም፣ እግዚአብሔር አልማ እና አሙሌቅ በከተማው ውስጥ ላሉ ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ ጥሪ እንዲያደርጉላቸው ነገራቸው። አልማ እና አሙሌቅ ታዘዙ። እግዚአብሔር ማስተማር እንዲችሉ እንዲረዳቸው ኃይሉን ሰጣቸው።
ሲያስተምሩ ከሰሟቸው ሰዎች አንዱ ዚኤዝሮም ይባል ነበር። እሱ በጣም ብልህ ነበር እናም አልማን እና አሙሌቅን ለማታለል ፈለገ። አሙሌቅ እግዚአብሔር የለም ካለ ዚኤዝሮም ብዙ ገንዘብ እንደሚሰጠው ነገረው። ህዝቡ አሙሌቅ እና አልማ ያስተማሩትን እንዳያምኑ አሙሌቅ እንዲዋሽ ፈለገ።
አልማ 10፥29–32፤ 11፥21–25፤ 12፥4–6
አሙሌቅ ግን ስለእግዚአብሔር አይዋሸም። እግዚአብሔር እውን እንደሆነ ተናገረ። አሙሌቅ እና አልማ የዚኤዝሮምን ሃሳቦች ያውቁ ነበር። ዚኤዝሮምም ተገርሞ ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቃቸው። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እቅድ እንዳለው ዚኤዝሮምን አስተማሩት። ዚኤዝሮም፣ አልማ እና አሙሌቅ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማሩትን አመነ።
አልማ 11፥23–46፤ 12፥1–18፣ 24–34፤ 14፥6–7፤ 15፥6–7
ዚኤዝሮም ስላደረጋቸው መጥፎ ነገሮች በጣም አዝኖ ነበር። ታመመ። አልማ እና አሙሌቅ ጎበኙት። አልማ፣ ዚኤዝሮም በኢየሱስ ባለው እምነት ምክንያት ለመፈወስ እንደሚችል ለዚኤዝሮም ነገረው። አልማ፣ እግዚአብሔር እርሱን እንዲፈውሰው ጠየቀ። ዚኤዝሮም ዘልሎ ተነሳ። ተፈውሶ ነበር! ተጠመቀ እንዲሁም በህይወቱ በሙሉ ህዝቡን አስተማረ።