በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ አስራ ሁለት ደቀመዛሙርትን መረጠ


“ኢየሱስ አስራ ሁለት ደቀመዛሙርትን መረጠ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3 Nephi 11; 13; 18

ኢየሱስ አስራ ሁለት ሐዋሪያትን መረጠ

የማስተማር እና የማጥመቅ ሃይል

ኢየሱስ ክርስቶስ እጁን በአንድ ደቀ መዝሙር ላይ ያደርጋል እናም ይባርከዋል፣ እና ሰዎች በዙሪያቸው ቆመዋል እና ይጸልያሉ

ኢየሱስ ወደ ለጋስ ምድር በመጣ ጊዜ፣ አስራ ሁለት ሰዎችን መረጠ እና ለማስተማር እና ለማጥመቅ ሃይልን ሰጣቸው። መንፈስ ቅዱስንም ይሰጡ ዘንድ ሃይልንም ደግሞ ሰጣቸው። የእርሱ ደቀመዛሙርት ብሎም ጠራቸው። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዲያደርጉ ያስተማራቸውን ነገሮች አደረጉ።

3 ኔፊ 1፣1፣ 18–22, 41; 12፣1; 15፣11–12; 18፣36–37

ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራል፣ አንድ ደቀመዝሙር አንድን ሌላ ሰው ያጠምቃል፣ እና ሌሎች ደቀመዛሙርት ይሰማሉ እና ይመለከታሉ

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዴት እንደሚያጠምቁ አስተማራቸው። እርሱ መናገር ያለባቸውን ቃላት ነገራቸው። እርሱም ተጠማቂውን ሰው በውሃ ውስጥ እንዲያስገቡት እና እንዲወጣ እንዲረዱት አስተማራቸው። ኢየሱስም ዘወትር ሲያጠምቁ እርሱ ባስተማራቸው መንገድ እንዲሆን ነገራቸው። እርሱም ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ አስተማራቸው።

3 ኔፊ 11፥22–28፣ 35

ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱን ያናግራል።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ እርስ በርሳቸው እንዲግባቡ እና እንዳይነታረኩ ፈለገ። በሚነታረኩ ጊዜ፣ የእርሱን አስተምሮዎች እየተከተሉ እንዳልሆነ ተናገረ።

3 ኔፊ 11፥28–30።

ኢየሱስ ክርስቶስ እጁን ወደ ህዝቡ ይዘረጋል፣ እና ህዝቡም በፈገግታ ይሰማሉ

ከሰማዩ አባታቸው ጋር ዳግም መኖር ይችሉ ዘንድ ኢየሱስ ህዝቡን በእርሱ እንዲያምኑ፣ ንሰሃ እንዲገቡ፣ እና እንዲጠመቁ አስተማረ።

3 ኔፊ 11፥31–33

ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ይራመዳል እና ያስተምራቸዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በእርሱ ካመኑ፣ በሰማይ አባትም እንዲሁ ያምናሉ በማለት ተናገረ። ኢየሱስ እና የሰማይ አባት ህያው መሆናቸውን እንዲያውቁ መንፈስ ቅዱስ ይረዳቸዋል።

3 ኔፊ 11፥35–36

ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ እና ከህዝቡ ጋር ይቀመጣል እናም ያስተምራቸዋል።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ማስተማር በጨረሰ ጊዜ፣ እነርሱም ሄደው ሰዎችን ሁሉ እንዲያስተምሩ ነገራቸው። ስለሚበሉት፣ ስለሚጠጡት፣ እና ስለሚለብሱት እንዳይጨነቁ ነገራቸው። የሰማይ አባትን የሚያገለግሉ ከሆነ፣ የሰማይ አባት እንደሚጠነቀቅላቸው ነገራቸው።

3 Nephi 11፣41; 13፣25–34