በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ያዕቆብ እና ሼረም


“ያዕቆብ እና ሼረም፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ያዕቆብ 7

ያዕቆብ እና ሼረም

ስለኢየሱስ ክርስቶስ የነቢይ ምስክርነት

ያዕቆብ ልጆችን ሲያስተምር

ያዕቆብ ኢየሱስ ክርስቶስን ያየ ነቢይ ነበር። ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ ፈለገ። ያዕቆብ፣ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዲያከብሩ አስተማረ። ሰዎችን ስለኢየሱስ ለማስተማር በትጋት ሰራ።

2 ኔፊ 11፥2–3ያዕቆብ 1፥1–8፣ 17–19

ሼረም ሰዎችን ሲያነጋግር

አንድ ቀን ሼረም የሚባል ሰው ህዝብን ማስተማር ጀመረ። ሼረም ግን ኢየሱስ እውን አይደለም ብሎ አስተማረ። ሼረም ጥሩ ተነጋሪ ነበር፣ እናም ብዙ ኔፋውያን የተናገረውን አመኑ። በእርሱ ምክንያት፣ ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ማመን አቆሙ። ሼረም፣ ያዕቆብ በኢየሱስ ማመኑን እንዲያቆም ፈልጎ ነበር።

ያዕቆብ 7፥1–5

ሼረም ወደ ያዕቆብ በመጠቆም እየተናገረ

ሼረምም ወደፊት የሚሆነውን ማንም ሊያውቅ አይችልም አለ። ይህ ማለት ኢየሱስ ገና ወደ ምድር ያልመጣ ስለነበረ፣ ኢየሱስ እውን መሆኑን ማንም ሊያውቅ ይችል እንዳልነበረ ተናገረ። ያዕቆብ ግን ቅዱሳት መጻህፍትና ነቢያት ሁሉ ስለ ኢየሱስ እንዳስተማሩ ተናገረ። እግዚአብሔር ኢየሱስ ወደ ምድር እንደሚመጣ ለያዕቆብ አሳይቶት ነበር።

ያዕቆብ 7፥6–12

ሼረም እየተናገረ እና እየሳቀ

ሼረም አሁንም አላመነም ነበር። ኢየሱስ እውን ስለመሆኑ ስለመሆኑ ምልክት እንዲያሳየው ፈልጎ ነበር።

ያዕቆብ 7፥13

ያዕቆብ እጁን ሲያነሳ

ያዕቆብም ሼረም ኢየሱስ እንደሚመጣ እንደሚያውቅ እና ምልክት እንደማያስፈገው ተናገረ። ነገር ግን ያዕቆብ እግዚአብሔር ኃይል እንዳለው እና ኢየሱስም እውን መሆኑን ለማሳየት እግዚአብሔር፣ ሼረምን ነፍሱን እንዲስት እንደሚያደርገው ተናገረ።

ያዕቆብ 7፥14

ሼረም በአቅራቢያው ሰዎች እያሉ በጉልበቱ ሲወድቅ

በድንገት ሼረም ታመመ እና መሬት ላይ ወደቀ። ከብዙ ቀናት በኋላ እንደሚሞት አወቀ። በሰይጣን እንደተታለለ ለሰዎች ነገረ። እግዚአብሔርን ዋሽቶ እንደነበር ተናገረ። በዚያ ሁሉ ጊዜ ኢየሱስ እውን መሆኑን ያውቅ ነበር። ከዚያም ሼረም ሞተ። ሰዎቹ ቅዱሳት መጻህፍትን አነበቡ እናም በኢየሱስ አመኑ።

ያዕቆብ 7፥15–23