በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ልጆችን ባረከ


“ኢየሱስ ልጆችን ባረከ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3ኔፊ 17

ኢየሱስ ልጆችን ባረከ

ለእነርሱ ያለውን ፍቅር ማሳየት

ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተመቅደስ ደረጃ ላይ ቆሟል እናም ለተሰበሰበው ህዝብ ይናገራል

ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡን ብዙ ነገር አስተማረ። እነርሱ ስለተማሩት ነገር ለማሰብ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አየ። ኢየሱስ እርሱ ያስተማራቸውን ይረዱ ዘንድ ህዝቡ ወደ ቤታቸው ሄደው እናም ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልዩ ነገራቸው። ከዚያም ኢየሱስ በቀጣዩ ቀን መጥቶ እንደሚጎበኛቸው ቃል ገባላቸው።

3 ኔፊ 17፥1–4

ኢየሱስ ክርስቶስ ፈገግ አለ እናም እጆቹን ወደላይ አነሳ

ህዝቡም አለቀሱ ምክንያቱም ኢየሱስ አብሯቸው እንዲቆይ ይፈልጉ ስለነበር ነው። ኢየሱስ ህዝቡን ወደዳቸው። እምነታቸው ጠንካራ እንደነበር ማየት ችሎ ነበር። ከመካከላቸው ህመምተኛ የሆነ ወይም ማንኛውም ጉዳት ያለበትን ሰው ወደ እርሱ እንዲያመጡ ጠየቃቸው። እያንዳንዳቸውን መፈወስ ፈለገ።

3 ኔፊ 17፥5–8

 ኢየሱስ ክርስቶስ ህመምተኛን ልጅ ይረዳል፣ እና በአጠገቡ ሌሎች ልጆች አሉ እናም ተደስተዋል

ህዝቡም ከበሽተኞች ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው ጋር ወደ እርሱ መጥተዋል። ኢየሱስ እያንዳንዳቸውን ፈውሷል። በጣም ተደስተዋል። ተንበርክከው እግሩን ሳሙ።

3 ኔፊ 17፥9-10

ኢየሱስ አንድን ልጅ ያናግራል፣ እና ህዝቡም ከልጆቻቸው ጋር  በዙሪያው ተሰብስበዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ህጻናት ልጆቻቸውን ወደ እርሱ እንዲያመጡ ጠየቃቸው። ህዝቡም ልጆቻቸውን አመጡ እና ኢየሱስ ባለበት ወለል ላይ አስቀመጧቸው።

3 ኔፊ 17፥11–12

ኢየሱስ ክርስቶስ ተንበርክኳል እናም ይጸልያል፣ እና በዙሪያው ያሉ ልጆች እና ጎልማሶችም  እንዲሁ ይጸልያሉ

ከእርሱ ጋር ልጆች ከተሰበሰቡ በኋላ፣ ኢየሱስ ህዝቡን በመሬት እንዲንበረከኩ ጠየቀ። እርሱም ደግሞ ተንበረከከ። ከዚያም ወደ ሰማይ አባት ጸለየ። ቃላቶቹ ሊመዘገቡ በማይቻል ደረጃ አስገራሚ ነገሮችን ተናገረ። ህዝቡም በሃሴት ተሞሉ።

3 ኔፊ 17፥13–18

ኢየሱስ ክርስቶስ ፈገግ አለ፣ እናም እንባ ከዓይኖቹ ፈሰሰ

ኢየሱስም ህዝቡ ለእርሱ ባላቸው እምነት ምክንያት የተባረኩ እንደሆኑ ነገራቸው። ኢየሱስ እጅግ ሀሴት ስለተሰማው ማልቀስ ጀመረ።

3 ኔፊ 17፥19–21

ኢየሱስ ክርስቶስ አንድን ብላቴና አቀፈ፣ እና በአጠገቡ ሌሎች ልጆች አሉ እናም ተደስተዋል

ከዚያም ኢየሱስ እያንዳንዱን ልጅ አንድ በአንድ ባረከ። እርሱ ለእያንዳንዳቸው ወደ ሰማይ አባት ጸለየ። ከዚያም እርሱ ለህዝቡ ልጆቻቸውን እንዲመለከቱ ነገራቸው፡፡

3 ኔፊ 17፥21–23

ኢየሱስ ክርስቶስ ለልጆች ተናገረ፣ እና መላእክትም ከሰማይ ወረዱ እና በልጆቹ ዙሪያ ተሰበሰቡ

መላእክት ከሰማይ ወረዱ እና በልጆችም ዙሪያ ተሰበሰቡ፡፡ መላእክቱ ልጆችን በባረኩበት ጊዜ፣ ሰማያዊ ብርሃን ከበባቸው። በሌላም ቀን፣ ኢየሱስ ልጆችን አገኘ እና ባረካቸው። እርሱ በተጨማሪ ልጆችን መናገር ይችሉ ዘንድ ባረካቸው። ህጻናትም እንኳ ተናገሩ። ልጆች ለወላጆቻቸው አስገራሚ ነገሮችን አስተማሩ።

3 ኔፊ 17፥23–2526፥14፣16