በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የነፃነት አርማ


“የነፃነት አርማ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 46–50

የነፃነት አርማ

በእግዚአብሔር የማመን መብትን ማስከበር

አማሊቅያ በተደሰተ ህዝቡ ፊት እጆቹን ዘርግቶ

አማሊቅያ ትልቅ፣ ጠንካራ ኔፋዊ ነበር። ንጉሥ መሆን ይፈልግ ነበር። ለሚረዱት ሰዎች ስልጣን እንደሚሰጥ ቃል ገባ። ብዙ ሰዎች ይወዱት ስለነበር ሌሎች እንዲከተሉት ለማድረግ ሞከረ። አማሊቅያ ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ አደረገ። እሱና ተከታዮቹ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምሩ ሰዎችን መግደል ፈለጉ።

አልማ 45፥23–2446፥1–10

ሻምበል ሞሮኒ ከአማሊቅያ እና ከህዝቡ ዞር ብሎ እየሄደ

የኔፋውያን ሰራዊት መሪ ሻምበል ሞሮኒ በኢየሱስ አመነ። ኔፋውያን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጠበቃቸው ምክንያት እንደተባረኩ ያውቅ ነበር። አማሊቅያ ንጉሥ ለመሆን እና ሰዎችን ለመጉዳት እየሞከረ ስለሆነ እንዲሁም ሰዎች ከእግዚአብሔር እንዲርቁ እያደረገ በመሆኑ በጣም ተናድዶ ነበር።

አልማ 46፥9–11፣ 13–15፣ 18

ሻምበል ሞሮኒ የነፃነት አርማ ይዞ

ሞሮኒ ኮቱን ቀደደ። በሱም ላይ፣ሰዎች አምላካቸውን፣ ነፃነታቸውን እና ቤተሰባቸውን እንዲያስታውሱ በማለት ጻፈ። ከዚያም ዘንግ ላይ አስሮት የነጻነት አርማ ብሎ ጠራው። ሞሮኒ የእግዚአብሔርን በረከት ለማግኘት ጸለየ። ለኔፋውያን የነጻነት አርማውን አሳያቸው እና አማሊቅያን ለመዋጋት ከእሱ ጋር እንዲተባበሩ ጠየቃቸው።

አልማ 46፥12–20፣ 23–24፣ 28

ሽምበል ሞሮኒ በሰራዊቱ እና በቤተሰቦች ፊት ቆሞ

ሰዎቹ ጥሩራቸውን ለብሰው ወደ ሞሮኒ ሮጡ። ለእግዚአብሔር እና ለቤታቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለነጻነታቸው ለመዋጋት ዝግጁ ነበሩ። ከእግዚአብሔር ጋር እርሱን ሁል ጊዜ ለመከተል ቃል ኪዳን ወይም ልዩ ኪዳን ገቡ። ከዚያም አማሊቅያን ለመውጋት ተዘጋጁ።

አልማ 46፥21–22፣ 28

አማሊቅያ እና አንዳንድ ወታደሮቹ እየሸሹ

የሞሮኒ ሠራዊት ትልቅ ነበር። አማሊቅያ ፈራ። ከተከታዮቹ ጋር ለማምለጥ ሞከረ። ነገር ግን ብዙዎቹ አማሊቅያ እየተዋጋ ያለው ትክክለኛ ላልሆነ ምክንያት ነው በማለት ተጨነቁ። ብዙዎች እሱን መከተል አቆሙ። የሞሮኒ ሠራዊት አማሊቅያን ይከተሉ የነበሩትን አስቆመ፣ ነገር ግን አማሊቅያ እና ሌሎች ጥቂት ሰዎች አመለጡ።

አልማ 46፥29–33

አማሊቅያ ላማናውያንን እያናገረ

አማሊቅያ ወደ ላማናውያን ምድር ሄደ። ከኔፋውያን ጋር በሚያደርገው ጦርነት ላማናውያን እንዲረዱት ፈለገ። ከዚያም ትልቅና ጠንካራ ሠራዊት ይኖረዋል። ብዙ ላማናውያን በኔፋውያን ላይ እንዲቆጡ አደረገ። የላማናውያን ንጉስ ኔፋውያንን ለመውጋት እንዲዘጋጁ ለሁሉም ላማናውያን ነገራቸው።

አልማ 47፥1

አማሊቅያ ዘውድ እንዲደረግለት በላማናውያን ንጉሥ ፊት ተንበርክኮ

ንጉሡ አማሊቅያን ወደደው። አማሊቅያን ከላማናውያን ሠራዊት መሪዎች መካከል አንዱ አደረገው። ነገር ግን አማሊቅያ ተጨማሪ ኃይል ፈለገ።

አልማ 47፥1–3

አማሊቅያ ዘውድ ደፍቶ

አማሊቅያ ላማናውያንን ለመግዛት እቅድ አወጣ። መላውን የላማናውያንን ሠራዊት ተቆጣጠረ። ከዚያም አገልጋዮቹ ንጉሡን እንዲገድሉትና ማን እንዳደረገው እንዲዋሹ አደረገ።

አልማ 47፥4–26

አሚሊቅያ በሚጮሁ የላማናውያን ወታደሮች ፊት እጁን ጨብጦ

አማሊቅያ ንጉሡ በመገደሉ የተናደደ መስሎ ለመታየት ሞከረ። ላማናውያን አማሊቅያን ወደዱት። ንግሥቲቱን አግብቶ አዲስ ንጉሥ ሆነ። በኔፋውያንም ላይ መንገስ ፈለገ። ላማናውያን እንዲቆጡባቸውም ስለ ኔፋውያን ክፉ ተናገረ። ብዙም ሳይቆይ ብዙ ላማናውያን ሊዋጓቸው ፈለጉ።

አልማ 47፥25–3548፥1–4

ሻምበል ሞሮኒ እና ወታደሮቹ ግንብ ገነቡ

አማሊቅያ በውሸት ስልጣን ሲያገኝ፣ ሞሮኒ፣ ኔፋውያን በእግዚአብሔር እንዲታመኑ አዘጋጃቸው። የገቡትን ቃል ኪዳን እንዲያስታውሱ በምድሪቱ ውስጥ ባሉ ማማዎች ሁሉ ላይ የነፃነት አርማን ሠቀለ። የሞሮኒ ወታደሮችም የኔፋውያንን ከተሞች ለጦርነት አዘጋጁ። ከተሞቹን አስተማማኝ እና ጠንካራ ለማድረግ ግንቦችን ገነቡ፣ ጉድጓዶችንም ቆፈሩ።

አልማ 46፥3648፥7–18

የአማሊቅያ ወታደሮች በኔፋውያን ከተማ ላይ ቀስቶችን ወረወሩ

ላማናውያን ለመዋጋት በመጡ ጊዜ፣ ወደ ኔፋውያን ከተሞች መግባት አቃታቸው። የሞሮኒ ወታደሮች በገነቧቸው ግንቦች እና ጉድጓዶች ተከለከሉ። ብዙ ላማናውያን ኔፋውያንን ሲያጠቁ ሞቱ። አማሊቅያ በጣም ተናደደ። ሞሮኒን ለመግደል ቃል ገባ።

አልማ 49፥1–27

ሻምበል ሞሮኒ ከጦርነቱ በኋላ ኔፋውያንን እያናገረ

ኔፋውያን እግዚአብሔር ስለረዳቸው እና ስለጠበቃቸው አመሰገኑት። ከተሞቻቸውን የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ አደረጉ፣ እንዲሁም ተጨማሪ ከተሞችን ገነቡ። ከላማናውያን ጋር የነበረው ጦርነት ቀጠለ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ሞሮኒንና ሰራዊቱ ኔፋውያንን በመጠበቅ ረዳቸው። ኔፋውያን ደስተኞች ነበሩ። እግዚአብሔርን ታዘዙት፣ ለእርሱም ታማኝ ሆነው ቆዩ።

አልማ 49፥28–3050፥1–24