በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ነቢዩ ሞርሞን


“ነቢዩ ሞርሞን፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

የሞርሞን ቃላት 1ሞርሞን 1–8

ነቢዩ ሞርሞን

መፅሐፈ ሞርሞንን መጻፍ

ብዙ ሰዎች የጦር መሳሪያ ይሰራሉ፣ እና ሞርሞን በህጻንነቱ እና እናቱ ሰይፍ በተሞላ ጠረቤዛ አጠገብ ይቆሙ ነበር

ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ ያምን የነበረ ኔፋዊ ነበር። እርሱ ያደገው ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ይከተሉ ባልነበረበት ጊዜ ነበር። ሰዎች ለገንዘብ እና ለስልጣን እርስ በርሳቸው ይዘራረፉ እና ይገዳደሉ ነበር። አያሌ ጦርነቶች ነበሩ።

3 ኔፊ 5፥12–134 ኔፊ 1፥27-49ሞርሞን 1፣1–3፥15፣18-19

አማሮን ሞርሞንን ያናግራል እና አዝመራ እየሰበሰቡ እያለ እናቱ፣ እና ብዙ ሰዎች በአቅራቢያው ባለ የእርሻ ቦታ ይሰራሉ።

ሞርሞን የ 10 ዓመት ልጅ እያለ፣ አማሮን የተባለ ሰው ወደ እርሱ መጣ። አማሮን የኔፋውያንን ታሪክ መዝገብ ይንከባከብ ነበር። አማሮን ሞርሞንን ያምን ነበር እና መዛግብቱም በአንድ ተራራ ስር ተደብቀው እንደነበር ነገረው። አማሮንም ሞርሞን 24 ዓመት በሆነው ጊዜ፣ ሞርሞን ስለህዝባቸው ያየውን መጻፍ እንዳለበት እና በመዝገብም ውስጥ እንዲያካትተው ተናገረ።

4 ኔፊ 1፣47–49 ሞርሞን 1፥2–4

ታዳጊ የነበረው ሞርሞንም በዛፎች ቁጥቋጦ ውስጥ ይጸልያል፣ እና በዙሪያውም ብርሃን አለ።

ሞርሞን ማደግ በጀመረ ጊዜም፣ አማሮን እንዲያደርገው የጠየቀውን አስታወሰ። ሞርሞን የ 15 ዓመት ልጅ እያለ፣ በጌታ ተጎበኘ። ሞርሞን ስለኢየሱስ መልካምነት ተማረ።

ሞርሞን 1፥5፣ 15

ታዳጊው ሞርሞን መሳሪያ ይታጠቃል እና የኔፋውያንንም ሰራዊት ይመለከታል።

ምንም እንኳ ሞርሞን ወጣት ቢሆንም፣ እርሱ ብርቱ ነበር። ኔፋውያን ሰራዊታቸውን እንዲመራላቸው መረጡት። ሞርሞን በሙሉ ልቡ ህዝቡን ወደዳቸው። እነርሱ ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ እና ደስተኛ እንዲሆኑ ፈለገ፡፡

ሞርሞን 2፣1–2፣ 12፣ 15፣ 193፣12

ጎልማሳው ሞርሞን አዝኗል እናም ይጸልያል፣ እና ከበስተኋላውም የሚነድ መሬት አለ።

ሞርሞን ህዝቡን ሊረዳ ሞክሯል። ቀን በቀንም ስለእነርሱ ይጽልያል። ህዝቡም ክፉን ነገር እያደረጉ እንደሆነ አውቀዋል፣ ነገር ግን ንሰሃ ሊገቡ አልቻሉም። ከዚህም በኋላ የሚረዳቸው የእግዚአብሔር ሀይል አልነበራቸውም፡፡ እምነት ስላልነበራቸው ተአምራት ቆመዋል። መዋጋትን ቀጥለዋል፣ እና ከእነርሱም ብዙዎች ሞተዋል። ሞርሞን አዝኖ ነበር።

ሞርሞን 1፣13-14፣ 16–192፣23–273፣1-124፣5፣ 9–125፣1–7

ሞርሞን የሚጽፍባቸውን የብረት ሰሌዳዎች አሰናዳ።

ሞርሞን 24 ገደማ ሲሆነው፣ መዛግብቱ ወደ ተደበቁበት ኮረብታ ሄደ። እርሱም የህዝቡን ታሪክ እና አስተምሮዎችን በብረት ሰሌዳው ላይ መጻፍ ጀመረ። ምን መጻፍ እንደነበረበትም ጌታ ረድቶታል። ሞርሞንም በመዛግብቱ ላይ ለብዙ ዓመታት ሰርቷል። ዛሬ፣ መዝገቡ መጽሐፈ ሞርሞን ይባላል።

የሞርሞን ቃላት 1፣3–9ሞርሞን 1፣3–42፣17–18

ሞርሞን፣ ባለቤቱ፣ እና ልጆቹ ይጓዛሉ።

ከብዙ ጦርነት በኋላ፣ ላማናውያን ምናልባትም ሁሉንም ኔፋውያን ገድለዋቸዋል። ሞርሞንም ህዝቡ በቅርብ ጊዜ እንደሚጠፉ አወቀ። እነርሱ ንሰሃ ስላልገቡ እና የእግዚአብሔርንም እርዳታ ስላልጠየቁ አዝኗል። ነገር ግን ሰሌዳዎቹ ይጠበቁ ዘንድ ጸለየ እና እግዚአብሔርንም ጠየቀ። ሰሌዳዎቹ የተጠበቁ እንደሚሆኑ ያውቅ ነበር ምክንያቱም በላያቸው ላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለነበረ ነው።

የሞርሞን ቃላት 1፣11ሞርሞን 5፣116፣6፣ 16–22

ሞርሞን በሸመገለ ጌዜ የነሃስ ሰሌዳዎቹን ለልጁ ሞሮኒ ሰጠው።

ሞርሞን ሰዎች በኢየሱስ እንዲያምኑ ይፈልግ ነበር። ለወደፊቱም ብዙ ሰዎች መጽሐፉን ያነቡ ዘንድ ተስፋ ነበረው። በተለይም የሌማናውያን ቤተሰቦች አንድ ቀን እንዲያነቡ ይመኝ ነበር። ይህን ቢያደርጉ፣ ስለኢየሱስ መማር ይችላሉ። ሞርሞን ከመሞቱ በፊት፣ መዝገቡን ለልጁ ሞሮኒ ሰጠው ይህም የሆነው ይጠበቅ ዘንድ ነበር።

የሞርሞን ቃላት 1፣1–2ሞርሞን 3፣17–225፣8–246፣678፣1