“ሊሄ እና ሳርያ ከኢየሩሳሌም ወጡ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
“ሊሄ እና ሳርያ ከኢየሩሳሌም ወጡ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች
ሊሄ እና ሳርያ ከኢየሩሳሌም ወጡ
ጌታ ለአንድ ቤተሰብ የሰጠው ማስጠንቀቂያ
ሊሄ እና ሳርያ ከልጆቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ሌሂ ከጌታ የመጣ ራዕይ አየ። አዳኝ ወደምድር አንድ ቀን እንደሚመጣ ተመለከተ። ደግሞም ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ጌታ አሳየው።
ሌሂ ሰዎችን ስለራዕዩ ነገራቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን አለምን ለማዳን እንደሚመአ ነገራቸው።
ሌሂ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ ለሰዎች ነገረ። ንስሃ እንዲገቡ ጋበዛቸው።
ሰዎቹ ተናድደው ነበር። ጌታ ሌሂን እንደገና በህልም አነጋገረው። እርሱ እና ቤተሰቡ በኢየሩሳሌም ውስጥ ደህንነታቸው እንደማይጠበቅ ሌሂ ተረዳ። ከዚያ መውጣት ነበረባቸው።
ሌሂ እና ሳርያ የጌታን ትእዛዝ አከበሩ። ከቤተሰባቸው ጋር ከከተማው ወጡ። ሌሂ እና ሳርያ ላማን፣ ልሙኤል፥ ሳም፣ እና ኔፊ ተብለው የሚጠሩ አራት ወንድ ልጆች ነበሯቸው። ቤታቸውን እና ጥሩ እቃዎቻቸውን ትተው መሄድ ነበረባቸው።
ቤተሰቡ በቀይ ባህር አጠገብ ባለው ምድረ በዳ ተጓዙ። ቤተሰቡን ስለባረከለት ሌሂ ጌታን አመሰገነ። ቤተሰቡ ጌታን እንዲከተሉ እና ትእዛዛቱን እንዲያከብሩ አስተማረ።
ላማን እና ልሙኤልም አጉረመረሙ። ቤታቸው እና ትተዋቸው የሄዱት ነገሮች ሁሉ ናፈቋቸው። ጌታ ለምን እንዲወጡ እንደጠየቃቸው አልገባቸውም ነበር። እንደኢየሩሳሌም አይነት ትልቅ ከተማ ሊደመሰስ ይችላል ብለው አላመኑም ነበር።
ላማን እና ልሙኤል የሌሂ ራዕዮች የቅዠት እንደሆነ አሰቡ። ቤተሰቦቻቸው በምድረበዳ ለዘለአለም ቢጠፉስ?
ኔፊ፣ ሌሂ ያየው እውነት እንደሆነ በራሱ ለማወቅ ፈለገ። ጸለየ እእንዲሁም ጌታን ጠየቀ።
ጌታም፣ ኔፊ የአባቱን ቃላት እንዲያምን ለመርዳት መንፈስ ቅዱስን ላከ። ኔፊ ጌታን አመነ እናም የተማረውን ለወንድሞቹ አካፈለ። ሳም ኔፊን አዳማጠ እንዲሁም አመነ፣ ነገር ግን ላማን እና ላሙኤል አላዳመጡም።