“ቆሪያንተን፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ቆሪያንተን
እንደገና ወደ ጌታ መመለስ
ቆሪያንተን ከአልማ ልጆች አንዱ ነበር። ከአባቱ፣ ከወንድሙ ሺብሎን እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ዞራማውያን የተባሉ ሰዎችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለማስተማር ሄደ።
ቆሪያንተን ከሰዎች ጋር ሳለ፣ ኃጢአት ለመስራት ተፈተነ። ጌታን ከመታዘዝ ይልቅ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚቃረኑ ነገሮችን ለማድረግ መረጠ። ባደረገው ነገር ምክንያት፣ አንዳንድ ዞራማውያን አልማ እና ልጆቹ ያስተማሩትን አላመኑም።
አልማ ቆሪያንተን ንስሃ እንዲገባ እና ይቅርታን ያገኝ ዘንድ ወደ ጌታ እንዲመለስ ጋበዘው። ቆሪያንተን ስለ ጌታ እቅድ ክፍሎች ተጨንቆ ነበር። አልማ፣ ልጁ የጌታን የደስታ እቅድ፣ የክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ፣ ትንሳኤን እና ከሞት በኋላ ያለውን ህይወት እንዲገነዘብ ረድቶታል። ጌታ፣ እርሱ እንዲሠራው የሚፈልገው ሥራ እንዳለው አልማ አስታወሰው።
ቆሪያንተን አባቱን አዳመጠ። በኢየሱስ ላይ እምነት ነበረው እና ለኃጢያቱ ንስሀ ገባ። ጌታ ፍትሃዊ ደግሞም አፍቃሪ እና ደግ መሆኑን ተማረ። ቆሪያንተ ከአባቱ እና ከወንድሙ ጋር በድጋሚ አስተማረ። እነርሱም ንስሀ በመግባት፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመኖር ስለሚመጣው ደስታና ሰላም ለብዙ ሰዎች አስተማሩ።