በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሻምበል ሞሮኒ እና ዛራሔምና


“ሻምበል ሞሮኒ እና ዛራሔምና፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

አልማ 43–44

ሻምበል ሞሮኒ እና ዛራሔምና

ጦርነት እና በሰላም ለመኖር ቃል ኪዳን

ዛራሔምና ሠራዊቱን እየመራ

ዛራሔምና የላማናውያን ሠራዊት መሪ ነበር። በኔፋውያን ላይ መግዛት እና ህዝቡን እንዲያገለግሉ ለማድረግ ፈለገ። ዛራሔምና ሰራዊቱ ኔፋውያንን እንዲያጠቃ መራ።

አልማ 43፥3–8

የኔፋውያን ሰራዊት የላማናውያንን ሰራዊት እየተመለከተ

ኔፋውያን ቤታቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና ሃይማኖታቸውን ለመጠበቅ ፈለጉ። ላማናውያን የሚገዟቸው ከሆነ ጌታን ማምለክ እንደማይችሉ ያውቁ ነበር። ኔፋውያን ጠላቶቻቸውን ለመዋጋት መረጡ።

አልማ 43፥9–10፣ 14–15

ሞሮኒ ከዳመና ፊት ሆኖ ወደፊት እየተመለከተ

የኔፋውያን ሠራዊት ሻምበል የሆነ ሞሮኒ የሚባል ሰው ነበር። ሞሮኒ ሠራዊቱ ለውጊያ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጠ።

አልማ 43፥16–17

ሻምበል ሞሮኒ እና የኔፋውያን ወታደሮች ለመዋጋት ዝግጁ ሆነው

የሞሮኒ ወታደሮች መሳሪያ አመጡ፣ እንዲሁም ሞሮኒ እነሱን ለመጠበቅ ጠንካራ ጥሩር እና ጋሻ ሰጣቸው።

አልማ 43፥18–19

ላማናውያን የኔፋውያንን ሠራዊት በፍርሃት እየተመለከቱ

ሞሮኒ ላማናውያንን ለመውጋት ሠራዊቱን ይዞ ሄደ። ነገር ግን ላማናውያን ኔፋውያን ጥሩር እና ጋሻ እንዳላቸው ባዩ ጊዜ ለመዋጋት ፈሩ። ላማናውያን ሥሥ ልብስ ብቻ ነበራቸው እንዲሁም የሚከላከላቸው ትጥቅ አልነበራቸውም።

አልማ 43፥19–21

የላማናውያን ወታደሮች ጫካ ውስጥ እየሮጡ

ላማናውያን ሸሹ። ወደ ሌላ የኔፋውያን ምድር በድብቅ ለመግባት ሞከሩ። ሞሮኒ የት እንደሄዱ የማያውቅ መስሏቸው ነበር።

አልማ 43፥22

የኔፋውያን ሰላዮች የላማናውያን ወታደሮች ሲሮጡ እየተመለከቱ

ነገር ግን ላማናውያን እንደሸሹ፣ ሞሮኒ እንዲከተሏቸው ሰላዮችን ላከ።

አልማ 43፥23

የኔፋዊ ወታደር አልማን እያደመጠ

ከዚያም ሞሮኒ ለነቢዩ አልማ መልእክት ላከ። አልማ ላማናውያን ምን ለማድረግ እንዳሰቡ ጌታን እንዲጠይቅ ፈለገ። ጌታ፣ ላማናውያን ማንቲ የተባለ ደካማ ምድርን ለማጥቃት እንዳቀዱ ለአልማ ነገረው። ሞሮኒ አልማን አዳመጠ። ከላማናውያን ጋር ለመዋጋት ሠራዊቱን መራ።

አልማ 43፥23–33

የላማናውያን እና የኔፋውያን ወታደሮች አንዳቸው ሌላውን እየተዋጉ

ሠራዊቱ ተዋጋ። ላማናውያን በጣም ጠንካሮች እና ቁጡዎች ነበሩ። ኔፋውያን ላማናውያንን ፈርተው ስለነበር ሊሸሹ ፈለጉ። ነገር ግን ሞሮኒ ቤተሰቦቻቸውን እና እምነታቸውን አስታወሳቸው፣ ስለዚህ መዋጋታቸውን ቀጠሉ።

አልማ 43፥34–37፣ 43–48

ሞሮኒ ጦርነቱን ለማቆም እጁን ዘርግቶ

ኔፋውያን ለእርዳታ ወደ ጌታ ጸለዩ። ጌታ ጸሎታቸውን ሰማ፣ ታላቅም ኃይል ሰጣቸው። አሁን ላማናውያን ፈሩ። እነርሱም ወጥመድ ውስጥ ገቡ፣ ማምለጥም አልቻሉም። ሞሮኒ ላማናውያን እንደፈሩ ባየ ጊዜ፣ ወታደሮቹ ውጊያ እንዲያቆሙ ነገራቸው። ሞሮኒ ላማናውያንን መግደል አልፈለገም።

አልማ 43፥49–5344፥1–2

ሞሮኒ ለላማናውያን እየተናገረ

ሞሮኒ፣ ላማናውያን ኔፋውያንን ዳግም ላለመዋጋት ቃል የሚገቡ ከሆነ መሄድ እንደሚችሉ ለዛራሔምና ነገረው። ዜራሔምና ተቆጣ፣ ውጊያውን ለመቀጠል ሞከረ፣ ነገር ግን የሞሮኒ ወታደሮችን ማሸነፍ አልቻለም። ከዚያም ዛራሔምና እና ሠራዊቱ በሰላም ለመኖር ቃል ገቡ፣ ሞሮኒም እንዲሄዱ ለቀቃቸው።

አልማ 44፥1–20