Scripture Stories
የህይወት ዛፍ


“የህይወት ዛፍ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“የህይወት ዛፍ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

1 ኔፊ 8

የህይወት ዛፍ

በመንፈስ የተነሳሳ የሌሒ ህልም

ምስል
ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር ሲነጋገር

አንድ ምሽት፣ ሌሂ ከጌታ የመጣ ህልም አየ። ስለህልሙ ለቤተሰቡ ነገራቸው።

1 ኔፊ 8፥2–4

ምስል
መልአክ ሌሂን ሲያነጋግረው

በሕልሙ ውስጥ፣ ሌሂ ነጭ ልብስ የለበሰ ነው አየ። ሰውየውም ሌሂ እንዲከተለው ነገረው።

1 ኔፊ 8፥5–6

ምስል
ሌሂ በጭለማ ውስጥ

ሌሂ በጭለማ እና ባድማ ውስጥ እንደነበር ተመለከተ። ለብዙ ሰዓታት ተጓዘ። ጭለማው ግል አልጠፋም። በመጨረሻም፣ ሌሂ እርዳታ ለማግኘት ጸለየ።

1 ኔፊ 8፥7–8

ምስል
ሌሂ ፍሬ የያዘ ዛፍን ሲመለከት

ሌሂ ጸሎቱን ሲጨርስ፣ ትልቅ ሜዳ ተመለከተ። በሜዳውም ውስጥ ነጭ ፍሬ ያለው ዛፍ ነበር። ሌሂ ፍሬው ደስ ያሰኘኛል ሲል አሰበ፣ እናም በላው። ነፍሱ በደስታ ተሞላች።

1 ኔፊ 8፥9–12

ምስል
ስርያ፣ ሳም እና ኔፊ በወንዝ አጠገብ ቆመው ሳሉ ሌሂ ፍሬን ሲበላ

ፍሬው ከሌላ ፍሬ በላይ የሚጥም ነበር። ጣፋጭ እና አስደሳች ነበር። ሌሂ ይህን ከቤተሰቡ ጋር ለመካፈል ፈለገ። እነርሱንም እንደሚያስደስታቸው ያውቅ ነበር። ሌሂ ሳርያ፣ ሳም እና ሴፊ በወንዝ አጠገብ ቆመው አያቸው። የጠፉ ይመስሉ ነበር። ሌሂ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጠራቸው። እንዲመጡና ፍሬውን እንዲበሉ ጠየቃቸው።

1 ኔፊ 8፥11–15

ምስል
ላማን እና ልሙኤል ዞረው ሲሄዱ

ሳርያ፣ ሳም እና ኔፊ ወደ ዛፉ መጥተው ፍሬውን በሉ። ሌሂ ላማን እና ልሙኤልን ፈለገ። እነርሱም በፍሬው እንዲደሰቱ ፈልጎ ነበር። ሆኖም ፍሬውን ለመብላት አልመጡም።

1 ኔፊ 8፥16–18

ምስል
ሰዎች ወደ ዛፍ እየመጡ

ከዚያም ሌሂ የብረት በትር ያለውን ወደ ዛፉ የሚመራ መንገድ ተመለከተ። ብዙ ሰዎች በመንገዱ ላይ ሲጓዙ አየ። በድንገት፣ የጨለማ ጭጋግ ተነሳ። ጨለማው ለማየት አስቸጋሪ አደረገው። ወደ ዛፉ ለመድረስ የሚቻለው የብረት በትሩን በመያዝ ብቻ ነበር።

1 ኔፊ 8፥19–24

ምስል
እጅ በትርን ይዞ

አንዳንድ ሰዎች ከመንገዱ ወጡና ጠፉ። ሌሎችም የብረት በትሩን ያዙ እና ወደፊት ገፉ።

1 ኔፊ 8፥23–24

ምስል
ሴት ፍሬውን እየበላች

ዛፉ ጋር ሲደርሱ፣ ፍሬውን በሉ።

1 ኔፊ 8፥24

ምስል
ዛፍ፣ ወንዝ እና ትልቅ ህንጻ

ሌሂ ቀና ብሎ ተመለከተ ዘዚያም በብዙ ሰዎች የተሞላ አንድ ትልቅ ህንፃ አየ። ፍሬውን በበሉ ሰዎች ላይ ተሳለቁ። ፍሬውን የበሉ አንዳንዶች ሌሎች ሲስቁባቸው መጥፎ ሥሜት ተሰማቸው፣ ስለዚህ ከዛፉ ዞር ብለው ሄዱ። ተቅበዘበዙና ጠፉ።

1 ኔፊ 8፥25–28፣ 31–32

ምስል
ሰዎች ከዛፍ አጠገብ

ሌሂ የብረት በትርን አጥብቀው የያዙ ብዙ ሰዎችን በህልሙ አየ። ወደ ዛፉ እስኪመጡ ድረስ ደረጃ በደረጃ ወደፊት ተጓዙ። ከዚያም በዛፉ አጠገብ ተንበረከኩና ፍሬውን በሉ። በህንፃው ውስጥ ያሉትን ሰዎች አላዳመጡም። በዛፉ አጠገብ ለመቆየት መርጠዋል።

1 ኔፊ 8፥30፣ 33

ምስል
ሌሂ ከቤተሰቡ ጋር ሲነጋገር

ሌሂ ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ ስለ ላማን እና ስለ ልሙኤል ተጨነቀ። በህልሙ ውስጥ ፍሬውን አልበሉም ነበር። ሌሂ ላማንን እና ልሙኤልን ይወዳቸዋል። ወደ ጌታ እንደሚቀርቡ ተስፋ አድርጎ ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዲጠብቁ ጋበዛቸው።

1 ኔፊ 8፥36–38

አትም