“ኔፊ እና የነሐስ ሰሌዳዎች፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ኔፊ እና የነሐስ ሰሌዳዎች
መንፈስን መከተልን መማር
ላማን፣ ልሙኤል፣ ሳም እና ኔፊ በሌሊት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ወንድሞቹ ከከተማው ውጭ ተደብቀው ሳለ ኔፊ ወደ ላባን ቤት ሄደ።
ኔፊ መንፈሱ እንዲመራው ፈቀደ። ምን ማድረግ እንደሚገባው አላወቀም ነበር፣ ነገር ግን ጌታ የነሐስ ሰሌዳዎቹን ማምጣት እንዲችል እንደሚረዳው ያውቅ ነበር።
ኔፊ ወደ ላባን ቤ ሲቀርብ፣ ላባንን መሬት ላይ ወድቆ አገኘው። ላባን ሰክሮ ነበር። ኔፊ የላባንን ጎራዴ አየና አነሳው።
ኔፊ ሰይፉን ሲመለከት፣ መንፈስ ላባንን እንዲገድለው ነገረው። ኔፊ ግን ሊገድለው አልፈለገም። የኔፊ ቤተሰብ ያለቅዱሳት መጻህፍት ከሚቀሩ ላባን ቢሞት የተሻለ እንደሚሆን መንፈስ ለኔፊ ነገረው። እነርሱ በነሐስ ሰሌዳዎቹ ላይ የተጻፉት የእግዚአብሔር ትእዛዛት ያስፈልጓቸው ነበር።
ኔፊ ላባን ሊገድለው እንደሞከረ ያውቃል። በተጨማሪምላባን ንብረታቸውን ሰርቋል እንዲሁም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አያከብርም።
መንፈስ፣ ላባንን እንዲገድል እንደገና ለኔፊ ነገረው። ጌታ የነሐስ ሰሌዳዎችን ለማምጣት እንዲችል መንገድ እንዳዘጋጀለት ኔፊ አወቀ። መንፈሱን ለመታዘዝ መረጠ። ኔፉ ላባንን ገደለው እንዲሁም የላባንን ልብስ ለበሰ።
ኔፊ ከዚያም ወደ ላባን ግምጃ ቤት ሄደ እና ከላባን አገልጋይ ዞራም ጋር ተገናኘ። ኔፊ በሚያደርገው እና በሚናገረው እንደ ላባን አስመሰለ።
ኔፊ የነሐስ ሰሌዳዎቹን እንደሚፈልግ ለዞራም ነገረው። ከዚያም ኔፊ ዞራም ከእርሱ ጋር እንዲመጣ ነገረው። ዞራም፣ ኔፊ ላባን መሰለው፣ ስለዚህ ኔፊ እንደጠየቀው አደረገ።
ኔፊ እና ዞራም ከከተማው ሲወጡ፣ ኔፊ ለላማን፣ ለልሙኤል እና ለሳም ላባን መሰላቸው። ፈርተው ስለነበር መሸሽ ጀመሩ።
ኔፊ ወንድሞቹን ጠራቸው። ኔፊ መሆኑን ሲያውቁ መሮጥ አቆሙ። ከዚያም ግን ዞራም ፈራ እና ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ሞከረ።
ኔፊ ዞራምን አስቆመው። ጌታ ሰሌዳዎቹን እንዲያመጡ እንዳዘዛቸው ለዞራም ነገረው። ዞራም ከእነርሱ ጋር ወደ ቃል ኪዳን ምድር እንዲሄድ ጋበዘው። ዞራም ሰራተኛ ሳይሆን ነጻ ሰው ለመሆን እንደሚችል አወቀ፣ እናም ከኔፊ እና ቤተሰቦቹ ጋር አብሮ ለመሄድ ቃል ገባ።
ወደ ሌሂ እና ሳርያ ተመለሱ። ሌሂ እና ሳርያ ልጆቻቸውን በማየታቸው በጣም ተደስተው ነበር። ሳርያ ልጆቿ እንደሞቱ አስባ ነበር። ጌታ የልጆቿን ደህንነት ስለጠበቀ፣ አሁን ቤተሰቦቻቸው ከኢየሩሳሌም እንዲወጡ እንደታዘዙ አመነች። ሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ ጌታን ለማመስገን መስዋዕቶችን አቀረቡ።
ሌሂ የነሐስ ሰሌዳዎቹን አነበበ። ሰሌዳዎቹ የነቢያት ትምህርቶችን እንደያዙ አየ። በተጨማሪም ከቅድመ አያቶቹ አንዱ ወንድሞቹ ከረጅም ጊዜ በፊት በግብፅ ሸጠውት የነበረው ዮሴፍ እንደሆነ ተረዳ። ሌሂ የንሐስ ሰሌዳዎቹ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ያውቅ ነበር። ጌታ ቤተሰቡ ተእዛዛቱ እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ ያውቅ ነበር።