Scripture Stories
ንጉስ ቢንያም


“ንጉስ ቢንያም፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሞዛያ 1–5

ንጉስ ቢንያም

የእግዚአብሔር ህዝብን ማገልገል

ምስል
ሞሮኒ በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ እየፃፈ

ንጉስ ቢንያም የዛራሔምላ ምድርን የሚገዛ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር። ህዝቡን ለማገልገል እና ስለእግዚአብሔር ለማስተማር በትጋት ሰርቷል። በሌሎች የእግዚአብሔር ነቢያት እርዳታ፣ ቢንያም ዛራሔምላን ሰላማዊ እና በደህንነት የሚኖርበት ቦታ አደረጋት።

የሞርሞን ቃላት 1፥17–18ሞዛያ 1፥1–7

ምስል
ቢንያም ከሞዛያ ጋር እየተነጋገረ

ቢንያም አረጀ። ወንድ ልጁ ሞዛያ ህዝቡን እንዲሰበስብ ጠየቀው። ቢንያም፣ ሞዛያ አዲሱ ንጉሳቸው እንደሚሆን ሊነግራቸው ፈልጎ ነበር።

ሞዛያ 1፥9–10

ምስል
ቤተሰብ በድንኳን ውስጥ

ብዙ ሰዎች ከመላ አገሪቱ መጡ። ቢንያምን ለመስማት በቤተመቅደሱ አጠገብ ድንኳኖቻቸውን ተከሉ።

ሞዛያ 2፥1፣ 5–6

ምስል
ሰዎች በግንብ አጠገብ

ቢንያም፣ ብዙ ሰዎች እርሱን ለመስማት ይችሉ ዘንድ በግንብ ላይ ሆኖ ተናገረ። ቢንያም እነርሱን መምራት ይችል ዘንድ እግዚአብሔር እንደረዳው ተናገረ። እንደ ንጉሥ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዲያከብሩ አስተምሯቸዋል። ገንዘባቸውን አልወሰደም ወይም እንዲያገለግሉት አላደረገም። ይልቁንም ህዝቡንና እግዚአብሔርን ለማገልገል ሠርቷል።

ሞዛያ 2፥7–16

ምስል
ሰዎች አንዳቸው ለሌላው አገልግሎት ሲሰጡ

ሰዎቹ አንዳቸው ለሌላውን ሲያገለግሉ እግዚአብሔርንም እንደሚያገለግሉ ቢንያም ነገራቸው። ከዚያም የነበሯቸው ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር የመጡ እንደሆኑ ነገራቸው። በምላሹም፣ እግዚአብሔር ትእዛዛቱን እንዲያከብሩ ይፈልጋል። ታዛዥ ሲሆኑም፣ እግዚአብሔር ብዙ በረከቶችን ይሰጣቸው ነበር።

ሞዛያ 2፥17–24፣ 41

ምስል
ቢንያም ሞዛያ አጠገቡ ሆኖ እየተነገረ

ቢንያም ከዚህ በኋላ ንጉሳቸው ወይም አስተማሪያቸውለመሆን እንደማይችል ነገራቸው። ወንድ ልጁ ሞዛያ አዲሱ ንጉሳቸው ይሆናል።

ሞዛያ 2፥29–31

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ አንድን ሰው እየፈወሰ

ከዚያም ቢንያም መልአክ እንደጎበኝው ለህዝቡ ነገረ። መልአኩ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ወደ ምድር እንደሚመጣ ተናገረ። ተአምራትን ያደርጋል እንዲሁም ሰዎችን ይፈውሳል። በሕመም ይሰቃያል እንዲሁም ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ይሞታል። ኢየሱስ በእርሱ ላይ እምነት ያለውን እና ንስሀ የሚገባውን ሁሉ ይቅር እንደሚል ቢንያም አስተማረ።

ሞዛያ 3፥1–12፣ 17–18

ምስል
ደስተኛ ሰዎች

ህዝቡም ቢንያም ስለኢየሱስ ያስተማራቸውን አመኑ። ንስሀ መግባት እንደሚያስፈልጋቸው አወቁ። ሁሉም ሰዎች ፀለዩ እንዲሁም እግዚብሔር ይቅር እንዲላቸው ጠየቁ። ከጸለዩ በኋላ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእነርሱ ጋር ነበር። ደስታ ተሰማቸው እንዲሁም በኢየሱስ ላይ ባላቸው እምነት ምክንያት እግዚአብሔር ይቅር እንዳላቸው አወቁ።

ሞዛያ 4፥1–3፣ 6–8

ምስል
ሰዎች ከቢንያም እና ሞዛያ ጋር

ሠዎቹ በኢየሱስ እምነት ስለነበራቸው የተለየ ሥሜት እና ውስጣዊ መታደስ ተሰማቸው። አሁን ሁልጊዜም መልካም ነገሮችን ለማድረግ ፈለጉ። በቀሪው ህይወታቸው በሙሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመከተል ቃል ኪዳን ገቡ። በኢየሱስ ስላመኑ እና ይህንን ቃል ኪዳን ስለገቡ፣ የኢየሱስ ህዝቦች ተብለው ተጠሩ።

ሞዛያ 5፥2–9፣ 156፥1–2

አትም