በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን አካፈለ


“ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን አካፈለ ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3 Nephi 18; 20

ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን አካፈለ

ዘወትር እርሱን ማስታወስ

ኢየሱስ ክርስቶስ ብዛት ላለው ህዝብ ይናገራል፣ እና ደቀመዛሙርቱም ዳቦ እና በማሰሮ ወይንን አመጡለት

ኢየሱስ ህሙማንን ከባረከ እና ህጻናት ልጆችን ከባረከ በኋላ፣ እርሱን ሊሰሙ ለተሰበሰቡት ሁሉ የቅዱስ ቁርባንን አስተዋወቀ። እርሱ ጥቂት ዳቦና የወይን ጠጅ እንዲያመጡ ደቀመዛሙርቱን ጠየቃቸው፡፡

3 ኔፊ 1718፥1–2

ኢየሱስ ክርስቶስ ዳቦውን ለሁለት ቆረሰ እናም ዳቦውን ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ።

ኢየሱስ ዳቦውን ቆረሰ እና ባረከው። ይበሉትም ዘንድ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው። ደቀመዛሙርቱም ዳቦውን ለህዝቡ ሁሉ እንዲሰጡ ጠየቀ።

3 ኔፊ 18፥3–4፣ 6

ኢየሱስ ክርስቶስ ቁራሽ ዳቦን አነሳ፣ እና የመስቀሉ እና የባዶ መቃብር ምስል ከበስተጀርባው አለ።

ኢየሱስም በእርሱ ያመነ እና የተጠመቀ ዳቦውን መብላት እንዳለበት ተናገረ። ይህንንም ካደረጉ፣ ስጋውን ማስታወስ አለባቸው። ለህዝቡም በእጁ እና በእግሩ እንዲሁም በጎኑ የዳሰሱትን የችንካር ምልክቶች የዳሰሱበትን አስታወሳቸው።

3 Nephi 11፣14–15; 18፣3–7

ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ለአንዱ ኩባያን ከወይን ጋር ሰጠው።

ይጠጡትም ዘንድ ወይኑን ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው። ደቀመዛሙርቱም ወይኑን ለህዝቡ ሁሉ እንዲሰጡ ጠየቀ።

3 ኔፊ 18፥8–9

ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ተንበርክኮ ሲጸልይ

ኢየሱስም ንሰሃ የገባ እና የተጠመቀ ወይኑን መጠጣት እንዳለበት ተናገረ። ወይኑን የጠጣ ማንኛውም ሰው ደሙን ማሳታወስ እንደሚገባው ጠየቀ። ለእነርሱ በተሰቃየ እና በሞተ ጊዜ ደሙን እንደሰጠ አስታወሳቸው።

3 ኔፊ 18፥11

ኢየሱስ ክርስቶስ ለህዝቡ ይናገራል።

ኢየሱስ ዳቦውን መብላት እና ወይኑን መጠጣት ትእዛዝ መሆኑን ነገራቸው። ዳቦውን በመብላት እና ወይኑን በመጠጣት፣ ህዝቡም ለሰማይ አባት ትእዛዛቱን እንደሚጠብቁ እና ኢየሱስን እንደሚያስታውሱ አሳይተዋል። ኢየሱስም እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ከሆነ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚባረኩ ተናገረ።

3 ኔፊ 18፥7፣ 10–14፤

ኢየሱስ ክርስቶስ ለህዝቡ ይናገራል፣ እናም ወደ እርሱም ፈገግ ብለዋል

ህዝቡም ዳቦውን ከበሉና ወይኑንም ከጠጡ በኋላ፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። ከዚያም ህዝቡ ኢየሱስን አወደሱት።

3 Nephi 18፣4–5፣ 920፣9