Scripture Stories
የባሕር መሻገሪያ መርከብ


“የባሕር መሻገሪያ መርከብ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

“የባሕር መሻገሪያ መርከብ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች

1 ኔፊ 17–18

የባሕር መሻገሪያ መርከብ

ወደ ቃል ኪዳን ምድር ለመጓዥ መዘጋጀት

ምስል
ቤተሰቦች በባህር ላይ

ለጋስ በፍራፍሬ እና በማር የተሞላች ምድር ነበረች። ወብ የመኖሪያ ቦታ ነበረች። ሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ በባህር አጠገብ ይኖር ነበር እናም የሚያስፈልጓቸው ነገሮች ሁሉ ነበሯቸው።

1 ኔፊ 17፥5–6

ምስል
ኔፊ እየጸለየ

ከብዙ ቀናት በኋላ፣ ጌታ ለመጸለይ ወደ ተራራ እንዲሄድ ለኔፊ ነገረው። በዚያም፣ ቤተሰቡን ከባሩ ማዶ የሚያሻግርበት መርከብብ እንዲሰራ ጌታ ነገረው።

1 ኔፊ 17፥7–8

ምስል
ኔፊ ድንጋይ እያየ

ኔፊ መርከቡን እንዴት እንደሚሠራ ጌታ አሳየው። ነገር ግን ኔፊ መሳሪያዎችን ለመስራት ብረቶችን የት ማግኘት እንደሚችል አላወቀም ነበር። ጌታምብረቶችን ለማግኘት የት መሄድ እንዳለበት ለኔፊ አሳየው።

1 ኔፊ 17፥8–10

ምስል
ላማን እና ልሙኤል እየተነጋገሩ ኔፊ እየሰራ

በኋላም፣ ኔፊ መሣሪያዎችን ለመሥራት እሳት አቀጣጠለ። ላማን እና ልሙኤል ወንድማቸውን ኔፊን ተመለከቱ። መርከቡን በመገንባት ሊረዱት አልፈለጉም። ባህሩን ለማቋረጥ መሞከር መጥፎ ሀሳብ እንደሆነ አሰቡ።

1 ኔፊ 17፥11፣ 16–18

ምስል
ላማን እና ልሙኤል በኔፊ ተናደዱ

ላማን እና ልሙኤል፣ ኔፊ መርከብ እንዲሠራ ጌታ እንደነገረው አላመኑም። ለምን አሁንም በጌታ ላይ እምነት እንዳልነበራቸው ኔፊ ጠየቃቸው። ወንድሞቹ መልአክን እንዳዩ እና የጌታን ኃይል አውቀው እንደነበር አስታወሳቸው። ላማን እና ልሙኤል በጣም ስለተናደዱ ኔፊን ለመግደል ፈለጉ።

1 ኔፊ 17፥18–19፤ 45–48

ምስል
ላማን እና ልሙኤል በመሬት ላይ

ኔፊ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ተሞልቶ ነበር። ኔፊ፣ እንዳይነኩት ላማንን እና ልሙኤልን አስጠነቀቃቸው። ፈሩ እንዲሁም ለብዙ ቀናት ኔፊን ለመንካት አልደፈሩም ነበር። ከዚያም ጌታ፣ እጁን ወደ ወንድሞቹ እንዲዘረጋ ለኔፊ ነገረው። ኔፊ ወደ እነርሱ ለመድረስ ሲዘረጋ፣ በጌታ ኃይል እንደሚንቀጠቀጡ ተሰማቸው።

1 ኔፊ 17፥48፣ 52–55

ምስል
ሁሉም በመርከቡ ላይ እየሰሩ

ላማን እና ልሙኤል ጌታን አመለኩ እናም መርከቧን በመገንባት ረዱ። ኔፊ እርዳታ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ ጌታ ጸለየ። የኔፊ ቤተሰብ የገነቡት መርከብ ቆንጆ ነበር። ከብዙ ቀናት በኋላ፣ መርከቢቱ ተገንብታ አለቀች፣ እንዲሁም መልካም እንደ ሆነች አዩ። የኔፊ ቤተሰቦች ጌታ እንደረዳቸው አወቁ።

1 ኔፊ 18፥1–4

አትም