“በባህር ላይ የነበረ አውሎ ንፋስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
“በባህር ላይ የነበረ አውሎ ንፋስ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች
በባህር ላይ የነበረ አውሎ ንፋስ
በጌታ ሰላምን ማግኘት
ጌታ፣ ወደ መርከቧ የመግባት ጊዜ እንደደረሰ ለሌሂ ነገረው። ቤተሰቦቹ በሚጓዙበት ወቅት የሚበሉትን ብዙ ምግብ ሰነቁ። ከዚያም ሁሉም ወደ መርከቧ ገብተው ወደ ቃል ኪዳን ምድር ተጓዙ።
ለብዙ ቀናት በባህር ላይ ከተጓዙ በኋላ፣ አንዳንድ ሰዎች አክብሮት የጎደላቸው እና ባለጌ መሆን ጀመሩ። ጌታ እረድቷቸው እንደነበረ ረሱ።
ኔፊ እነርሱ ጌታን ሊያሳዝኑ ይችላሉ ሲል ተጨነቀ። ያለ ጌታ እርዳታ መርከባቸው ጥበቃ አያገኝም። ኔፊ፣ ወንድሞቹ እንዲያቆሙ ጠየቀ።
ላማን እና ልሙኤል በኔፊ ተናደዱ። አሰሩት እንዲሁም በእርሱ ላይ ጨካኞች ሆኑ። ጌታን ንየሚታዘዙ አልነበሩም፣ እናም ሊያሆናው መስራት አቆመ። ብዙም ሳይቆይ ትልቅ ማዕበል መጣ። ለሶስት ቀናት በማዕበል ውስጥ ከቆዩ በኋላ፣ ሁሉም እንደሚሰምጡ ፈርተው ነበር።
የኔፊ ቤተሰብ ኔፊን እንዲፈቱ ላማንን እና ልሙኤልን ለመኗቸው። ነገር ግን ላማን እና ልሙኤል አሁንም ማንም ኔፊን እንዲፈታ አልፈቀዱም። ሳርያ እና ሌሂ አዘኑ እንዲሁም በጣም ታመሙ። ማዕበሉም አልቆመም።
በአራተኛው ቀን ላማን እና ልሙኤል መርከቧ ልትሰምጥ እንደነበረ አወቁ። ንስሐ ገቡ ከዚያም ኔፊን ፈቱት። ኔፊ ሲጸልይ ማዕበሉ ቆመ። ሊያሆናው እንደገና ሰራ። ኔፊ መርከቧን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ለመምራት ተጠቀመበት።
ከብዙ ቀናት በኋላ ቤተሰቦቹ ወደ ቃል ኪዳን ምድር ደረሱ።