በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሞዛያ እና ዜኒፍ


“ሞዛያ እና ዜኒፍ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ኦምኒ 1ሞዛያ 9

ሞዛያ እና ዜኒፍ

በጌታ የተጠበቀ

ሞዛያ ሰዎችን እየመራ

ኔፋውያን እና ላማናውያን ብዙ ጦርነቶችን አድርገው ነበር። አንድ ቀን፣ ጌታ ሞዛያ ለሚባል ኔፊያዊ ጌታን ከሚከተል ከማንኛውም ሰው ጋር የኔፊን ምድር እንዲለቅ ነገረው።

ኦምኒ 1፥10፣ 12

ሞዛያ ከተማን እየተመለከተ

ብዙ ኔፋውያን ጌታን በመታዘዝ ከሞዛያ ጋር ሄዱ። እግዚአብሔርም ሰዎች ይኖሩበት ወደ ነበረ ምድር መራቸው። እነርሱም የዛራሔምላ ህዝብ ተብለው ይጠሩ ነበር።

ኦምኒ 1፥13–14

ሞዛያ ከሰዎች ጋር እያወራ

የዛራሔምላ ህዝብም ከኢየሩሳሌም የመጡት ከብዙ ጊዜ በፊት ነበር። ጌታ ኔፋውያንን ከናስ ሰሌዳዎች ጋር ስለላካቸው ደስተኞች ነበሩ። የሞዛያ ህዝብ ከዛራሔምላ ህዝብ ጋር ተቀላቀሉ። ህዝቡ ሁሉ ሞዛያን ንጉሳቸው አድርገው መረጡት። እርሱም ስለ ጌታ አስተማራቸው።

ኦምኒ 1፥14–19

ዜኒፍ ሰዎችን እየመራ

አንድ ትልቅ ቡድን ወደ ኔፊ ምድር ተመልሰው በሄዱበት ጊዜ ኔፋውያን በዛራሔምላ ለተወሰነ ጊዜ ይኖሩ ነበር። እነርሱም የሚመሩት ዜኒፍ በተባለ ኔፊያዊ ነበር።

ኦምኒ 1፥27–29ሞዛያ 9፥3–5

የላማናውያን ንጉሱ እየተናገረ

ላማናውያን አሁን በኔፊ ምድር ይኖሩ ነበር፣ ስለዚህ ዜነፍ ህዝቡ እዚያ መኖር ይችል እንደሆነ ንጉሣቸውን ጠየቀ። ንጉሱም ተስማማ።

ሞዛያ 9፥6–10

ላማናውያን እያጠቁ

ንጉሱ ዜኒፍን እና ህዝቡን አታለላቸው። የተወሰኑ ምግቦቻቸውን እና እንስሶቻቸውን በኋላ መውሰድ ይችል ዘንድ በኔፊ ምድር እንዲኖሩ ፈቀደላቸው። ዜኒፍ ህዝብ ለዓመታት በሰላም ኖሩ። ብዙ ምግብ አመረቱ፤ ብዙ እንስሳትም ነበሯቸው። ከዚያም ላማናውያን ጥቃት ሰነዘሩ እንዲሁም ምግባቸውን እና እንስሶቻቸውን ለመውሰድ ሞከሩ።

ሞዛያ 9፥10–14

የዜኒፍህዝብ ድል እያደረጉ

ዜኒፍ፣ ህዝቡ በጌታ እንዲያምኑ አስተምሯል። ላማናውያን ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት በመጡ ጊዜ፣ ዜኒፍ እና ህዝቡ ወደ ጌታ ጸለዩ። ጌታ ብርታት ሰጣቸው እንዲሁም ጥበቃ በመስጠት ረዳቸው። ላማናውያንን ማባረር ቻሉ። ጌታ ዜነፍ እና ህዝቡ ስላሳዩት እምነት ባረካቸው።

ሞዛያ 9፥15–18