“ወጣቱ አልማ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
“ወጣቱ አልማ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች
አልማ ወጣቱ
ትልቅ ለውጥ
ንጉስ ሞዛያ፣ አልማ በዛራሔምላ ያለችውን ቤተክርስቲያን እንዲመራ ሀይል ሰጠው። አልማ ህዝቡ ንስሀ እንዲገቡ እና በጌታ እምነት እንዲኖራቸው አስተማራቸው።
አልማ፣ ስሙ አልማ የተባለ ወንድ ልጅ ነበረው። ወጣቱ አልማ አባቱ ያስተምረው የነበረውን አያምንም ነበር።
ሞዛያ በጌታ የማያምኑ ወንድ ልጆችም ነበሩት። እነርሱም ከወጣቱ አልማ ጋር ጓደኞች ነበሩ። ሁሉም፣ ሰዎች ቤተክርስቲያኗን እንዲክዱ ይፈልጉ ነበር። አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚቃረኑ ነገሮችን ወደማድረግ መሯቸው።
አንድ ቀን፣ ጌታ እንዲያቆሙ የሚያደርጋቸው መልአክ ላከ። መልአኩ ቤተክርስቲያኗን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ሙከራ እንዲያቆሙ ነገራቸው። አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች በጣም ፈርተው ስለነበረ መሬትም ላይ ወደቁ።
አልማ ለሶስት ቀናት እና ለሶስት ምሽቶች መናገር እና መነቃነቅ አልቻለም ነበር። አድርጓቸውበነበሩት ትክክል ያልሆኑ ነገሮች የተነሳ መጥፎ ሥሜት ተሰምቶት ነበር። ደግሞም ብዙ ሰዎችን ጌታን ወደመካድ ስለመራቸው ተጨንቆ ነበር።
አልማ በኃጢያቱ ምክንያት ብዙ ተሰቃየ። ከዚያም አባቱ ስለ እግዚአብሔር ልጅ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ይናገር የነበረውን አስታወሰ።
አልማ፣ ኢየሱስ ይምረው ዘንድ ጸለየ። ከጸለየ በኋላ፣ ስቃዩን አያስታውስም ነበር። ጌታ ይቅር እንዳለው አወቀ። ከዚያ በኋላ ስለሃጢያቶቹ መጥፎ ሥሜት አልተሰማውም። በምትኩ፣ አልማ ደስተኛ ናበረ።
ሞዛያ 27፥24፣ 28–29፤ አልማ 36፥18–22
አልማ ጥንካሬውን አገኘ። እርሱ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች ንስሀ ለመግባት እና የተከሰቱትን ስቃዮች ሁሉ ለማስተካከል ወሰኑ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሌሎችም ንስሀ እንዲገቡ በመርዳት ጌታን አገለገሉ። ሞዛያ ያስተዳድረው በነበረው ምድር በሙሉ በመጓዝ ህዝብን ሰለኢየሱስ አስተማሩ።
ሞዛያ 27፥20–24፣ 32–37፤ አልማ 36፥23–26
አልማ እና የሞዛያ ወንድ ልጆች በህይወታቸው ውስጥ ደስታ ያመጣውን የኢየሱስ ትምህርት ለማካፈል ፈለጉ። ጌታን እና ሕዝቡን ለማገልገል ጠንክረው ሰሩ። የሞዛያ ወንድ ልጆች ካሉበት ለመሄድ እና ላማናውያንን ስለኢየሱስ ለማስተማር መረጡ። አልማ ባለበት ለመቆየት እና ኔፋውያንን በማስተማር ለመቀጠል መረጠ።