በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
አቢናዲ እና ንጉስ ኖህ


“አቢናዲ እና ንጉስ ኖህ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሞዛያ 11–17

አቢናዲ እና ንጉስ ኖህ

የነቢይ መልእክት

ሁለት ካህናት ከኋላው ቆመው ሳለ ንጉሥ ኖህ እየጠቆመ

ንጉስ ኖህ በኔፊ ምድር የሚኖሩ ኔፋውያን ገዢ ነበር። ኖህ ህዝቦቹ ብዙ ገንዘብ እንዲሰጡት ያደርግ ነበር፣ ከዚያም በገንዘቡ ለራሱ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ይገዛ ነበር። በመግዛት እንዲረዱት ትዕቢተኛ ካህናትን ሾመ። ኖህ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አልጠበቀም። ይልቁንም ብዙ መጥፎ ነገሮችን አደረገ።

ሞዛያ 11፥1–13

ንጉስ ኖህ

ኖህ ህዝቡም ክፉዎች እንዲሆኑ አደረገ። ጌታን አይከተሉም ነበር።

ሞዛያ 11፥7፣ 11፣ 14–15፣ 19

አቢናዲ ሰዎች መጥፎ ነገር ሲያደርጉ እየተመለከተ

አቢናዲ የሚባል የእግዚአብሔር ነቢይ በምድሪቱ ይኖር ነበር። ጌታ፣ ኖህና ህዝቡ ንስሃ እንዲገቡ እንዲነግራቸው አቢናዲን ላከ።

ሞዛያ 11፥20

አቢናዲ ለሰዎች እየተናገረ

አቢናዲ፣ ጌታ ሰዎቹ ንስሃ እንዲገቡ እንደሚፈልግ ነገራቸው። ንስሐ የማይገቡ ከሆነ ጌታ ጠላቶች ወደ አገራቸው መጥተው እንዲገዟቸው ያደርጋል። ጠላቶቻቸው ለኖህና ለህዝቡ ህይወትን እጅግ ከባድ ያደርጉባቸዋል።

ሞዛያ 11፥20–25

የተናደዱ ሰዎች

ህዝቡ አቢናዲ በተናገረው ነገር ተናደዱ። ሊገድሉትም ፈለጉ፣ ነገር ግን ጌታ አቢናዲን ጠበቀው፣ እንዲያመልጥም ረዳው።

ሞዛያ 11፥26

ንጉስ ኖህ እጆቹን ገጥሞ ካህናቱን እያናገረ

ኖህ አቢናዲንም ሊገድለው ፈለገ። ኖህ በጌታ አያምንም ነበር። እሱ እንዲሁም ህዝቡ ንስሐ አልገቡም።

ሞዛያ 11፥27–29

አቢናዲ ሰሌዳዎቹን ይዞ ለቤተሰብ እየተናገረ

ከሁለት አመት በኋላ፣ ጌታ ህዝቡን ለማስጠንቀቅ አቢናዲን እንደገና ላከ። አቢናዲ ንስሐ ስላልገቡ ጠላቶቻቸው መሬታቸውን እንደሚወርሱ ለህዝቡ ነገራቸው። ህዝቡ በአቢናዲ ተናደደ። ምንም ስህተት እንዳልሰሩ እና ንስሃ እንደማይገቡ ተናገሩ። አቢናዲን አስረውት ወደ ኖህ ወሰዱት።

ሞዛያ 12፥1–16

አቢናዲ ለንጉሥ ኖህ ጀርባውን በመስጠት ተንበርክኮ

ኖህና ካህናቱ አንድ እቅድ አወጡ። ካህናቱ አቢናዲን ብዙ ጥያቄዎች በመጠየቅ ሊያታልሉት ሞከሩ። ነገር ግን አቢናዲ በድፍረት መለሰላቸው። ካህናቱ በአቢናዲን መልሶች ተገረሙ። ሊያታልሉት አልቻሉም። አቢናዲ ትክክል የሆነውን ከማድረግ ይልቅ ለገንዘብ ይበልጥ እንደሚያስቡ ለካህናቱ ነገራቸው።

ሞዛያ 12፥17–37

አቢናዲ ቆሞ እያፀባረቀ

ኖህ ካህናቱ አቢናዲን እንዲገድሉት ነገራቸው። ነገር ግን አቢናዲ እንዳይነኩት አስጠነቀቃቸው። ፊቱ በእግዚአብሔር ኃይል አበራ። አቢናዲ፣ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ህግ እንዳላስተማሩ ተናገረ። አቢናዲ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወለድ፣ ለእኛ እንደሚሞት እና ከሞት እንደሚነሳ አስተማራቸው። ኢየሱስ ንስሐ ከገቡ ይቅር እንደሚላቸው ነገራቸው።

ሞዛያ 1316፥6–15

አቢናዲ ንጉስ ኖህን እየተመለከተ

አቢናዲ ጌታ እንዲያደርስ የላከውን መልእክት ጨረሰ። ኖህ አሁንም ተቆጥቶ ነበር። አቢናዲን ወስደው እንዲገድሉት ለካህናቱ ነገራቸው።

ሞዛያ 17፥1

አልማ እያሰበ እንዲሁም ሌሎች ካህናት ተናደው ሣሉ ንጉስ ኖህ አቢናዲን እየተመለከተ

አልማ የተባለ አንድ ካህን አቢናዲን አመነ። አልማ አቢናዲን ሊያድነው ሞከረ። ነገር ግን ኖህም በአልማ ተናዶ ነበር ስለዚህም እንዲሄድ አስገደደው።

ሞዛያ 17፥2–3

አልማ ከክፉ ካህናት እየተደበቀ

ካህናቱ አቢናዲ ያስተማረው ትምህርት እውነት እንዳልሆነ ከተናገረ በህይወት ሊያቆዩት እንደሚችል ነገሩት። አቢናዲ ግን እውነትን እንዳስተማረ ተናገረ። ኖህና ካህናቱ እንደገና ተናደዱ። አቢናዲን በእሳት አቃጥለው ገደሉት። የኖህ ጠባቂዎች አልማንም ለመግደል ሞክሩ። ነገር ግን አልማ ተደበቀ እናም የአቢናዲን ቃላት ሁሉ ጻፈ።

ሞዛያ 17፥3–13፣ 20