በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሴቶች በምድረበዳ ውስጥ


“ሴቶች በምድረበዳ ውስጥ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

1 ኔፊ 16–17

ሴቶች በምድረበዳ ውስጥ

ከጌታ ጋር መራመድ

ሴቶች እየሰሩ

የእስማኤል ሴት ልጆች ከቤተሰባቸው ጋር ወደ ምድረበዳ ተጉዘዋል። ጉዞው ከባድ ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሌሂን እና የሳርያን ወንድ ልጆች አገቡ።

1 ኔፊ 16፥717፥1

ሴት ልጆች በእስማኤል መቃብር አጠገብ አዝነው

አንድ ቀን እስማኤል ሞተ። ሴት ልጆቹ በጣም አዘኑ። አባታቸው ናፈቃቸው። ሴት ልጆቹ ደግሞም እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው በምድረበዳ ይሞታሉ ብለው ተጨነቁ። በሌሂ እና በኔፊ ተበሳጩ፣ እናም ወደ ቤታቸው ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈለጉ።

1 ኔፊ 16፥34–36

እህትማማቾቹ እርስ በርስ እየተፅናኑ

የእግዚአብሔር ድምፅ ለእስማኤል ሴት ልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው ተናገረ። ንስሀ ገቡ፣ እናም ጌታ ባረካቸው።

1 ኔፊ 16፥39

ሳርያ ከትናንሽ ልጆች ጋር

ሴቶቹ በምድረበዳ ሕፃናት ወለዱ። ሳርያም ያዕቆብ እና ዮሴፍ የተባሉ ሁለት ተጨማሪ ልጆች ወለደች።

1 ኔፊ 17፥118፥7

ቤተሰቦች እየተጓዙ

ጌታ ሴቶቹን በጉዞአቸው ረዳቸው። ለልጆቻቸው የሚሆን ብዙ ወተት እንዲኖራቸው ባረካቸው። ሴቶቹ በሚጓዙበት ጊዜ ጠንካራ እንዲሆኑ ረዳቸው።

1 ኔፊ 17፥1–3

እናቶች እና ልጆች በድንኳን ውስጥ

ጌታ ሴት ልጆችን እና ቤተሰቦቻቸውን ወደ ቃል ኪዳን ምድር እየመራ እንደሆነ ተናግሯል። ጌታ፣ ቤተሰቦቹ ሲጓዙ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እንደሚያገኙ ቃል ገብቷል። ያደኑትንም መብል ለመብላት መልካም እንዲሆን አድርጎላቸዋል፤ እንዲሁም መርቷቸዋል።

1 ኔፊ 17፥3፣ 5፣ 12–14

ቤተሰቦች በባህር ዳርቻ

ከስምንት ዓመታት የምድረበዳ ቆይታ በኋላ ቤተሰቦቹ ወደ ባህሩ ደረሱ። ሴቶቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደሰቱ። በባህሩ አጠገብ ያለው ምድር ውብ ነበር። በሚበሉ ፍራፍሬና ማር ሞልቶ ስለነበር፣ ለጋስ ብለው ጠሩት። ጌታ ሁሉንም አዘጋጅቶላቸው ነበር።

1 ኔፊ 17፥4–6