“አልማ እና አሙሌቅ በእስር ቤት፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
አልማ እና አሙሌቅ በእስር ቤት
በአስቸጋሪ ጊዜያት በጌታ መተማመን
አልማ እና አሙሌቅ በአሞኒሃ ከተማ ወንጌልን አስተማሩ። አንዳንድ ሰዎች በጌታ አመኑ እንዲሁም ንስሐ ገቡ። ነገር ግን ሌሎች ብዙ ሰዎች በአልማ እና በአሙሌቅ ተቆጥተው ሊያጠፏቸው ፈለጉ። የተቆጡ ሰዎች አልማን እና አሙሌቅን አስረው ወደ ከተማው ዋና ዳኛ ወሰዷቸው።
ዋናው ዳኛ ህዝቡ ንስሐ መግባት እንዳለበት አላመነም። ህዝቡ በአልማ እና በአሙሌቅ ተበሳጩ። አልማ እና አሙሌቅ ያስተማሩትን ያመኑ ሰዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አደረጉ። ከዚያም በጌታ ያመኑት ሴቶችና ህጻናትን በእሳት ውስጥ ጣሏቸው።
አሙሌቅ በህመም ላይ ያሉትን ሰዎች ባየ ጊዜ በጣም አዘነ። እነሱን ለማዳን የእግዚአብሔርን ኃይል እንዲጠቀም አልማን ጠየቀው። ነገር ግን አልማ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳልፈቀደለት ተናገረ። ሴቶቹ እና ልጆቹ ከጌታ ጋር እንደሚሆኑ ለአሙሌቅ ነገረው። ጌታ በገደሏቸው ሰዎችላይ ይፈርድባቸዋል።
ጌታ ሴቶቹን እና ህጻናቱን ስላላዳነ ዋናው ዳኛ በአልማ እና በአሙሌቅ ላይ ተሳለቀባቸው። አልማን እና አሙሌቅን ወደ እስር ቤት ሰደዳቸው።
ከሶስት ቀናት በኋላ ዋናው ዳኛ ከሀሰተኛ ካህናቱ ጋር ወደ እስር ቤት ሄደ። ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቁ። አልማ እና አሙሌቅ ግን አልመለሱላቸውም።
ዋናው ዳኛ እና ካህናቱ በአልማ እና በአሙሌቅ ላይ ክፉ ነገር አደረጉ። እንዲሁም ለአልማ እና አሙሌቅ ምንም አይነት ምግብ እና ውሃ አልሰጧቸውም ነበር። አልማ እና አሙሌቅ ባስተማሩትም ነገር ተሳለቁ።
አልማ እና አሙሌቅ ለብዙ ቀናት ተሠቃዩ ። ዋናው ዳኛ ከካህናቱ ጋር እንደገና መጣ። አልማ እና አሙሌቅ የእግዚአብሔር ኃይል ካላቸው፣ የታሰሩባቸውን ገመዶች መበጣጠስ እንዳለባቸው ነገራቸው። ከዚያም የዚያን ጊዜ ያምናቸዋል።
አልማ እና አሙሌቅ የእግዚአብሔር ኃይል ተሰማቸው። ተነሱ። አልማ በጌታ ላይ እምነት ነበረው እናም ገመዱን ለመበጣጠስ ኃይል እንዲሠጠው ጠየቀ።
አልማ እና አሙሌቅ ገመዶቹን በጠሱ። ዋናው ዳኛ እና ካህናቱ ፈሩ። ለማምለጥ ሞክረው ነበር ነገር ግን መሬቱ መንቀጥቀጥ ጀመረ።
የእስር ቤቱ ግንብ በዋናው ዳኛ እና በካህናቶቹ ላይ ወደቀ እነርሱም ሞቱ። ነገር ግን ጌታ አልማን እና አሙሌቅን ጠበቃቸው። ሰዎቹ ጩኸቱን በሰሙ ጊዜ የሆነውን ለማየት ሮጡ። አልማ እና አሙሌቅ ብቻ ከእስር ቤቱ ወጡ። ሰዎቹ አልማን እና አሙሌቅን በጣም ፈርተው ስለነበር ከፊታቸው ሸሹ።