ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፴፩


ምዕራፍ ፴፩

አልማ ኃይማኖታቸውን የካዱትን ዞራማውያን ለመመለስ ተልዕኮውን መራ—ዞራማውያን ክርስቶስን ካዱ፤ በውሸት የምርጫ ሀሳብ አመኑ፣ እናም በተወሰነ ፀሎት አመለኩ—አገልጋዮች በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ—ስቃያቸው በክርስቶስ ደስታ ተውጠዋል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ ቆሪሆር ከሞተ በኋላ፣ ዞራማውያን የጌታ ጎዳናን መበከላቸውን እናም መሪያቸው የነበረው ዞራም የሰዎችን ልብ ጣኦትን ለማምለክ እንዲያጎነብስ መምራቱን አልማ ወሬውን በመስማቱ ልቡ በህዝቡ ኃጢያት ምክንያት መታወክ ጀመረ።

በህዝቡ መካከል ያለውን ክፋት ማወቅ ለአልማ ታላቅ ሀዘን ነበር፤ ስለዚህ ልቡም ዞራማውያን ከኔፋውያን በመለየታቸው እጅግ አዘነ።

አሁን በዛራሔምላ በስተምስራቅ በባህሩ ዳርቻ፣ በኢየርሾን ምድር በስተደቡብ፣ ላማናውያን በሞሉበት በምድረበዳው በደቡብ ዳርቻ አንቲዮኑም ብለው በሚጠሩት ስፍራ ውስጥ ዞራማውያን እራሳቸውን በአንድ ላይ ሰበሰቡ።

አሁን ዞራማውያን ከላማናውያን ጋር የህብረት ስምምነት ያደርጋሉ፣ እናም ይህም ለኔፋውያን የታላቅ ጥፋት መንስኤ ይህናል በማለት ኔፋውያን እጅግ ፈሩ።

እናም አሁን፣ የቃሉ መሰበክ ህዝቡ ትክክለኛውን እንዲሰራ የሚመራ ታላቅ ዝንባሌ ስላለው—አዎን፣ ይህም ከጎራዴ፣ ወይም ከሚሆንባቸው ማንኛውም ነገር፣ የበለጠ በአዕምሮአቸው ላይ ውጤት ይኖረዋል—ስለዚህ አልማ ኃያል ውጤት ያለውን የእግዚአብሔር ቃል በጎነት መሞከራቸው አስፈላጊነቱን አሰበ።

ስለዚህ አሞንን፣ አሮንንና፣ ኦምነርን ወሰደ፤ እናም ሂሚኒን በዛራሔምላ ቤተክርስቲያን ተወው፤ ነገር ግን ቀዳሚዎቹ ሶስቱን ከእርሱ ጋር ወሰዳቸውና፣ ደግሞ በሜሌቅ የነበሩትን አሙሌቅንና፣ እና ዚኤዝሮምን፣ ደግሞም ሁለት ወንድ ልጆቹን ወሰደ።

እንግዲህ ሔለማን የሚባለውን ትልቁን ልጁን ከእርሱ ጋር አልወሰደውም፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር የወሰዳቸው ስማቸው ሺብሎንና፣ ቆሪያንቶን ይባላሉ፤ እናም ቃሉን በዞራማውያን መካከል ለመስበክ ከእርሱ ጋር የሄዱት ስማቸው እነዚህ ናቸው።

እናም ዞራማውያን ከኔፋውያን የተገነጠሉ ነበሩ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ተሰብኮላቸው ነበር።

ነገር ግን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እናም ስርዓቶቹ በሙሴ ህግ መሰረት ባለመጠበቃቸው በታላቅ ስህተት ውስጥ ወደቁ

ወደፈተናው እንዳይገቡ ዕለት ዕለትም እግዚአብሔርን በመለመን በፀሎታቸው የሚቀጥሉበትን የቤተክርስቲያኗን ስርዓት አላከበሩም።

፲፩ አዎን፣ በአጠቃላይ፣ የጌታን መንገድ በብዙ ሁኔታዎች አጣመዋል፤ ስለዚህ፣ ለዚህ ምክንያት አልማና ወንድሞቹ ለእነርሱ ቃሉን ለመስበክ ወደምድሪቱ ሄደዋል።

፲፪ እንግዲህ፣ ወደምድሪቱ በመጡ ጊዜ፣ እነሆ፣ ለመገረማቸው ዞራማውያን ምኩራብን ሠርተው አገኙአቸው፣ እናም የጌታ ቀን ብለው በሚጠሩት ቀንም በሳምንት አንድ ቀን በአንድ ላይ እራሳቸውን ይሰበስባሉ፤ እናም አልማና ወንድሞቹ አይተውት በማያውቁት ሁኔታ ያመልካሉ፤

፲፫ በምኩራባቸው ለመቆሚያነት ከጭንቅላት በላይ ከፍ ያለን ቦታ በመሀከሉ ሰርተው ነበር፤ እናም ጫፉም ላይ ለመግባት የሚያስችለው አንድን ሰው ብቻ ነበር።

፲፬ ስለዚህ፣ ማምለክ የፈለገ መሄድና በጫፉ ላይ መቆም አለበት፤ እናም ወደሰማይ እጁን በመዘርጋት፣ እናም በኃይል እንዲህ በማለት ይጮሃል፥

፲፭ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ አንተ አምላክ መሆንህን እናምናለን፣ ቅዱስ መሆንህንና፣ አንተ መንፈስ እንደነበርክ፣ መንፈስም እንደሆንክ፣ እናም ለዘለዓለም መንፈስ እንደምትሆን እናማንለን።

፲፮ ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ከወንድሞቻችን እንደለየኸን እናምናለን፤ እናም በአባቶቻቸው ሞኝነት የተሰጧቸውን የወንድሞቻችንን ወግ አናምንም፣ ነገር ግን አንተ እኛ ቅዱሳን ልጆችህ እንድንሆን እንደመረጥከን እናምናለን፣ እናም ደግሞ ክርስቶስ እንደሌለ እንድናውቅ አድርገኸናል።

፲፯ ነገር ግን አንተ ትናንትም፣ ዛሬም ለዘለዓለም አንድ ነህ፤ እናም በዙሪያችን ያሉ ሁሉ በቁጣህ ወደሲኦል እንዲጣሉ በተመረጡ ጊዜ፣ እኛ እንድንድን መርጠኸናል፤ ስለዚህም ስለቅድስናችን አቤቱ እግዚአብሔር እናመሰግንሀለን፣ እናም ደግሞ በክርስቶስ በማመን በሚያስተሳስራቸው፣ ልባቸውን ከአንተ ከሚያርቀው በወንድሞቻችን ከንቱ ወግ እንዳንመራ ስለመረጥኸን እናመሰግንሀለን።

፲፰ እናም አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፣ እኛ የተመረጥንና ቅዱስ ሰዎች በመሆናችን በድጋሚ እናመሰግንሀለን። አሜን።

፲፱ እንግዲህ እንዲህ ሆነ አልማና ወንድሞቹ፣ እናም ልጆቹ ይህንን ፀሎት ከሰሙ በኋላ ያለመጠን ተገረሙ።

እነሆም፣ ሁሉም ሰው ሄዶ ይህንኑ ፀሎት አቀረበ።

፳፩ እንግዲህ የስፍራው ስም ራሜዩምጵቶም ተብሎ ይጠራ ነበር፤ እርሱም ትርጓሜው ቅዱስ መቆሚያ ማለት ነው።

፳፪ እንግዲህ ከዚህ መቆሚያ እያንዳንዱ ሰው ይኸንኑ ፀሎት ያቀርባል፤ አምላካቸውን በእርሱ ስለተመረጡ፣ እናም እርሱም በወንድሞቻቸው ወግ እንዳይመሩ ስላደረገ፣ እናም ልባቸው ምንም ስለማያውቁት ስለሚመጡት ነገሮችም ስላልተወሰደ አምላካቸውን አመሰገኑት።

፳፫ አሁን፣ ህዝቡ በዚህ ሁኔታ ምስጋናውን ካቀረበ በኋላ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ በቅዱሱ መቆሚያ ተሰብስበው በድጋሚ በዚህ ሁኔታ ምስጋናን እስከሚያቀርቡ ድረስ ስለ አምላካቸውም በድጋሚ አልተናገሩም

፳፬ እንግዲህ አልማ ይህንን በተመለከተ ጊዜ ልቡ አዝኖ ነበር፤ እርሱ ኃጢአተኛና ብልሹ የሆኑትን ሰዎች መሆናቸውን ተመልክቷልና፤ አዎን ልባቸውንም በወርቅ፣ በብር፣ እናም በሚያምሩ ነገሮች ላይ ማድረጋቸውን ተመለከተ።

፳፭ አዎን እናም ደግሞ ልባቸው በኩራታቸው በፉከራ ሲነሳሳ ተመለከተ።

፳፮ እናም ድምፁን ወደሰማይ ከፍ አደረገና፣ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ አቤቱ ጌታ ሆይ አገልጋዮችህ በሰው ልጆች መካከል እንደዚህ ዓይነቱን ታላቅ ኃጢያት ሲሰሩ ለመመልከት እስከመቼ ከዚህ በታች በስጋ እንዲኖሩ ትፈቅዳለህ?

፳፯ እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ እነርሱ ወደአንተ ይጮኻሉ፣ እናም ይሁን እንጂ ልባቸው በኩራታቸው ተሞልቷል። እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ በዓለም ከንቱ ነገሮች እስከ ማበጥ ድረስ ሲኩራሩ በአንደበታቸው ግን ወደአንተ ይጮሃሉ።

፳፰ አምላኬ ሆይ፣ ውድ ልብሶቻቸውም፣ ቀለበቶቻቸውም፣ አምባሮቻቸውንም፣ የወርቅ ጌጣጌጦቻቸውንም፣ እናም የሚያጌጡባቸው የተከበሩ ነገሮቻቸው ሁሉ ተመልከት፤ እናም እነሆ ልባቸው በእነዚህ ላይ ነበር፣ ግን ወደ አንተ ይጮሀሉም እንዲህም ይላሉ—ሌሎች በሚጠፉበት ጊዜ እኛ በአንተ የተመረጥን ስለሆነ አምላክ ሆይ እናመሰግንሀለን።

፳፱ አዎን፣ እናም አንተ ክርስቶስ አለመኖሩን እንዳሳወቅሃቸውም ይናገራሉ።

ጌታ አምላክ ሆይ፣ እንደዚህ ዓይነት ክፋትን እና ታማኝ አለመሆንን በዚህ ህዝብ መካከል ለምን ያህል ጊዜ ትፈቅዳለህ? ጌታ ሆይ፣ በደካማነቴ እታገስ ዘንድ ብርታትን ትሰጠኛለህ። ምክንያቱም እኔ ደካማ ነኝና፣ እናም በእነዚህ ሰዎች መካከል እንደዚህ ዓይነት ክፋት ነፍሴን ያስጨንቃታል።

፴፩ አምላክ ሆይ፣ ልቤ እጅግ አዝኗል፤ በክርስቶስ ነፍሴን ታፅናናለህን። ይህንንም በእኔ ላይ በህዝቡ ክፋት የሚመጣውን ስቃይ በትዕግስት እታገሰው ዘንድ ጌታ ሆይ ብርታትን ትሰጠኛለህ።

፴፪ ጌታ ሆይ፣ ነፍሴን ታፅናናለህ፣ እናም ለእኔና፣ ደግሞ ከእኔ ጋር ለሚያገለግሉት ጓደኞቼ—አዎን፣ አሞንና፣ አሮንንም፣ ኦምነርንም፣ ደግሞ አሙሌቅንም፣ ዚኤዝሮምንም፣ እናም ደግሞ ሁለት ወንድ ልጆቼንም—መቃናትን ስጠን፤ አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እነኝህን ሁሉ ታፅናናለህ። አዎን በክርስቶስ ነፍሳቸውን ታፅናናለህ።

፴፫ በህዝቡ ክፋትም የተነሳ በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ስቃይ ይሸከሙ ዘንድ ብርታትን እንዲያገኙ ትሰጣቸዋለህ።

፴፬ ጌታ ሆይ፣ እኛም በድጋሚ እነርሱን ወደ ክርስቶስ በማምጣት ድልን እናገኝ ዘንድ ለእኛ ትፈቅድልናለህ

፴፭ እነሆ፣ ጌታ ሆይ፣ የእነርሱ ነፍስ ውድ ነው፣ እናም ብዙዎቹ ወንድሞቻችን ናቸው፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ፣ እነዚህን ወንድሞቻችንን በድጋሚ ወደአንተ እናመጣቸው ዘንድ ኃይልና ጥበብን ስጠን።

፴፮ እንግዲህ እንዲህ ሆነ አልማ እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር በነበሩት ላይ ሁሉ እጁን አጨበጨበ። እናም እነሆ፣ እጁን በእነርሱ ላይ ባጨበጨበ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።

፴፯ እናም ምን መመገብ እንዳለባቸውም ሆነ መጠጣት እንዳለባቸው እንዲሁም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሳያስቡ አንዳቸው ከሌላኛው እራሳቸውን ለዩ።

፴፰ እናም ጌታ እንዳይራቡ ወይም እንዳይጠሙ ሁሉን አቀረበላቸው፤ አዎን፣ እናም ደግሞ በክርስቶስ ፍቅር ከመዋጥ በስተቀር ምንም ስቃይ እንዳያገኛቸው ብርታትን ሰጣቸው። እንግዲህ ይህም በአልማ ፀሎት መሰረት የሆነ ነበር፤ እና ይህ ደግሞ እርሱ በእምነት በመፀለዩ ነበር።