“ጥር 8–14 ፦‘እሄዳለሁ እና አደርጋለሁ።’ 1 ኔፊ 1–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]
“ጥር 8–14 (እ.አ.አ)። 1 ኔፊ 1–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 8–14 ፦ “እሄዳለሁ … አደርጋለሁ”
1 ኔፊ 1–5
መፅሐፈ ሞርሞን የሚጀምረው እውነተኛ ችግር ባጋጠመው የእውነተኛ ቤተሰብ ታሪክ ነው። በ600 ዓ.ዓ የሆነ ነገር ቢሆንም በዚህ ታሪክ ውስጥ ያሉ ነገሮች ዛሬ ባለ ቤተሰብ ውስጥም የተለመዱ የሚመስሉ ነገሮች አሉ። ይህ ቤተሰብ በክፋት ዓለም ውስጥ ይኖር ነበር፣ ነገር ግን ጌታ የሚከተሉት ከሆነ ወደ ደህንነት እንደሚመራቸው ቃል ገባላቸው። በመንገዳቸው ላይ መልካም እና መጥፎ ወቅቶች አሳልፈዋል፣ ታላላቅ በረከቶች እና ተአምራቶች አይተዋል፣ ነገር ግን በመካከላቸው ክርክር እና ጭቅጭቅም ነበረ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወንጌልን ለመኖር የሚጥር እንደዚህ ዓይነት ጥልቅ የሆነ የቤተሰብ ታሪክ ብዙ ጊዜ የለም፦ ወላጆች እምነትን በቤተሰባቸው ውስጥ ለማነሳሳት ሲጥሩ እና ስለ ደህንነታቸው ሲጨነቁ፣ ልጆች ወላጆቻቸውን እንደሚያምኑ ሲወስኑ እና ወንድማማቾች ከምቀኝነት እና ከጭቅጭቅጋር ሲታገሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ እርስ በእርስ ይቅር ሲባባሉ እናያለን። በአጠቃላይ፣ በዚህ ፍጹም ባልሆነ ቤተሰብ የእምነት ምሳሌዎች ውስጥ ኃይል አለ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
የእግዚአብሔር ቃል ለኔ “ትልቅ ዋጋ [አለው]”።
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ አንዱ ጎልቶ የሚታይ መልዕክት የእግዚአብሔር ቃል “ትልቅ ዋጋ” ያለው መሆኑ ነው (1 ኔፊ 5፥21)። 1 ኔፊ 1–5ን ስታነቡ የእግዚአብሔር ቃል የሌሂን ቤተሰብ በቀጥታም ሆነ በተዛዋዋሪ የባረከበትን መንገዶች ፈልጉ (ለምሳሌ፣ 1፥11–15፤ 3፥19–20፤ 5፥10–22ን ይመልከቱ)። እነዚህ ምዕራፎች ስለ እግዚአብሔር ቃል ምን ያስተምሯችኋል? ቅዱሳት መጽሐፍትን ለመመርመር የሚያነሳሳችሁን ምን አገኛችሁ?
በተጨማሪም “ቅዱሳት መጽሐፍትን ስፈትሽ፣,” መዝሙር, ቁጥር. 277; “የቅዱሳት መጽሐፍት ቅርስ [Scriptures Legacy]” (ቪዲዮ), ወንጌል ላይብረሪ.
ወደ ጌታ ስመለከት ምስክርነቴን አገኛለሁ እንዲሁም አጠነክራለሁ።
ኔፊ በጌታ ባለው ኃያል እምነተ ይታወቃል፣ ነገር ግን ልክ እንደ ሁላችንም ምስክርነቱን ለማግኘት መስራት ነበረበት። በ1 ኔፊ 2 ውስጥ ኔፊ የአባቱ ቃል እውነት ስለመሆኑ ምስክርነት ለምን ማግኘት እንደቻለ የሚያሳይ ምን ታነባላችሁ? ላማን እና ልሙኤል ይህንን ምስክርነት ያላገኙት ለምንድን ነው ? (በተጨማሪም 1 ኔፊ 15፥2–11 ይመልከቱ)። ጌታ ልባችሁን ሲያራራ የተሰማችሁ መቼ ነው?
በተጨማሪም “ጌታ የሌሂ ቤተሰብ ኢየሩሳሌምን ለቆ እንዲሄድ አዘዘ [The Lord Commands Lehi’s Family to Leave Jerusalem]” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍትን ይመልከቱ።
እግዚአብሔር የእርሱን ፍቃድ እንዳደርግ መንገድን ያዘጋጅልኛል።
ጌታ የሌሂ ወንድ ልጆች የነሃስ ሰሌዳዎቹን እንዲያመጡ ሲያዝ፣ ይህን እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው የተለየ መመሪያን አልሰጠም። ይህ ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሔር ከምንቀበለው መመሪያ ጋር ይመሳሰላል እናም እርሱ ከእኛ “ከባድ ነገር” እንደፈለገ ሆኖ ሊሰማን ይችላል (1 ኔፊ 3፥5)። በ1 ኔፊ 3፥7፣ 15–16 ኔፊ ለጌታ ትዕዛዝ በሰጠው ምላሽ ውስጥ ምን ያነሳሳችኋል?
1 ኔፊ 3–4ን ስታነቡ ኔፊን ያጋጠሙትን የተለያዩ ችግሮች ፈልጉ። ጌታ “[ያዘዛቸውን] ትዕዛዛት እንዲያሟሉ” ለኔፊ “መንገድን ያዘጋጀው እንዴት ነው”? ጌታ ለኔፊ ያደረገውን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር ትዕዛዛቱን እንድንጠብቅ ያዘጋጀን አንዱ ኃይለኛ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛችን እንዲሆን በመላክ ነው። የፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስን “አዳኛችን ለእኛ ምን አደረገ? [What Has Our Savior Done for Us?]” መልዕክት ማንበብን አስቡ (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 75–77)። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን መንገድን ያዘጋጀው እንዴት ነው? እርሱ ለእናንተ ሁሉንም ነገሮች ማሸነፉን በማወቃችሁ፣ “ለመሄድ እና ለማድረግ” ምን መነሳሳት ይሰማችኋል?
በተጨማሪም “ኔፊ የናሱን ሰሌዳዎች ለማግኘት በመንፈስ ተመራ [Nephi Is Led by the Spirit to Obtain the Plates of Brass]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተ መፃሕፍት፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “መታዘዝ፣” የወንጌል ቤተ መፃሕፍት ውስጥ ይመልከቱ።
የእግዚአብሔርን ስራዎች ማስታወስ ትዕዛዛቶቹን ለመጠበቅ እምነት ሊሰጠኝ ይችላል።
ላማን እና ልሙኤል ሲያጉረመርሙ እና ሲያማርሩ ኔፊ እና ሌሂ አብዛኛውን ጊዜ ሊያነሳሷቸው እና ሊደግፏቸው ከጎናቸው ነበሩ። የማጉረምረም ስሜት ሲሰማችሁ የኔፊን እና የሌሂን ቃላት ማንበብ ሊረዳ ይችላል። ኔፊ እና ሌሂ ሌሎች በእግዚአብሔር ላይ እምነትን እንዲገነቡ ለመርዳት የሞከሩት እንዴት ነው? (1 ኔፊ 4፥1–3፤ 5፥1–8ይመልከቱ፤ በተጨማሪም 1 ኔፊ 7፥6–21 ይመልከቱ)። ለማጉረምረም እና ለማማረር ስትፈተኑ ሊረዳችሁ የሚችልን ነገር ምን ተማራችሁ?
“በመንፈስ ተመራሁ”
በ1 ኔፊ 4፥5–18 ውስጥ፣ ኔፊ ስለነበረው መንፈስን የመገንዘብ እና የመከተል ችሎታ ምን ያስደንቃችኋል? ከጌታ ራዕይን ስለመቀበል የበለጠ ለመማር የረስል ኤም. ኔልሰንን መልዕክት ልታጠኑ ትችላላችሁ፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ፣ ራዕይ ለህይወታችን፣” [ሊያሆና፣፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 93–96]።
ልጆችን ለማስተማ የሚረዱ ሀሳቦች
የራሴ ምስክርነት ሊኖረኝ ይችላል።
-
ኔፊ አባቱ ያስተማረው ነገር እውነት እንደሆነ እንዴት አወቀ? በ1 ኔፊ 2፥16፣ 19 ውስጥ ላለው ጥያቄ ልጆቻችሁ መልሶችን እንዲፈልጉ አግዙ። የኔፊን ድርጊቶች በጡቦች ላይ ወይም በሌሎች ቁሶች ላይ በመፃፍ እና ቁሶቹን በመጠቀም የሆነ ነገርን በመገንባት ሊደሰቱ ይችላሉ። እነዚህ ተግባራት ምስክርነትን እንድንገነባ እንዴት እንደሚያግዙን ወደሚደረግ ውይይት ሊመሩ ይችላሉ።
-
ልጆች ምስክርነትን ለማግኘት የሚሹበትን ነገሮች የሚወክሉ ፎቶዎችን ወይም ቁሶችን፣ ለምሳሌ የመጽሐፈ ሞርሞን ቅጂን ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ፣ የቤተ መቅደስ ወይም በሕይወት ያለ ነቢይ ፎቶን ለልጆቻችሁ ልታሳዩ ትችላላችሁ። አንዱን እንዲመርጡ እና በዚያ ላይ ምስክርነታቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። እናንተ ምስክርነታችሁን እንዴት እንዳገኛችሁ ለልጆቻችሁ ልትነግሩ ትችላላችሁ። የራሳችንን ምስክርነት ለምንድን ነው የምንፈልገው?
እግዚአብሔር ትዕዛዛቱን እንድጠብቅ ይረዳኛል።
-
እግዚአብሔር ኔፊ የነሃስ ሰሌዳዎቹን እንዲያገኝ እንዴት እንደረዳው ልጆቻችሁ እንዲናገሩ ለመርዳት እነዚህን አንድ ወይም ብዙ ግብዓቶችን መጠቀምን አስቡ፦ 1 ኔፊ 3–4፤ የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ፤ “የኔፊ ድፍረት [Nephi’s Courage]” (የልጆች የምዝሙር መጽሐፍ፣ 120–21)፤ እና “ምዕራፍ 4፦ የነሃስ ሰሌዳዎች” (በመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች ውስጥ፣ 8–12)።
-
እናንተ እና ቤተሰባችሁ 1 ኔፊ 3፥2–7ን በመተወን ልትደሰቱ ትችላላችሁ። ምናልባት ሌሂ እንደሆናችሁ በማስመሰል ልጆቻችሁ የነሃስ ሰሌዳዎቹን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። እንደ ላማን እና ልሙኤል ወይም ኔፊ በመሆን በእነርሱ ቃላት እንዲመልሱ ጋብዟቸው። እግዚአብሔር እንድናደርግ ያዘዘን የተወሰኑ ነገሮች ምንድን ናቸው? (ሃሳቦችን ለመግኘት ፎቶዎች 103–15 በወንጌል ጥበብ መጽሐፍ ወይም ሞዛያ 18፥8–10 ይመልከቱ)። እንደ ኔፊ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ቅዱሳት መጽሐፍት ታላቅ ጠቀሜታ አላቸው።
-
ቅዱሳት መጽሐፍት ለሌሂ ቤተስብ በጣም አስፈላጊ ነበሩ። ይህንን ለማስረዳት ኔፊ እና ወንድሞቹ የነሃስ ሰሌዳዎቹን ለማግኘት ያደረጉትን ነገር ልጆቻችሁ እንድትናገሩ ወይም እንድትተውኑ እንዲረዷችሁ መጋበዝ ትችላላችሁ፦ ረጅም ርቀትን ተጓዙ፣ ወርቅ እና ነሃሳቸውን አሳልፈው ሰጡ እና ሕይወታቸውን ለማትረፍ በዋሻ ውስጥ ተደበቁ። ከዚያም 1 ኔፊ 5፥21ን ልታነቡ እና ለሌሂ ቤተሰብ ቅዱሳት መጽሐፍት ለምን ዋጋ እንደነበራቸው ልትናገሩ ትችላላችሁ። ለእኛ ዋጋ ያላቸው ለምንድን ነው? ቅዱሳት መጽሐፍትን ጠቀሜታ እንዳላቸው ነገሮች የምንወስዳቸው እንዴት ነው?