አጠቃላይ ጉባኤ
አዳኛችን ለእኛ ምን አደረገ?
የሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


12:44

አዳኛችን ለእኛ ምን አደረገ?

በሰማይ አባታችን ዕቅድ ውስጥ ከምድራዊ ሕይወት ጉዞአችን እስከ ዕጣ ፈንታ ለተዘረዘረው የሚያስፈልገውን ሁሉንም ነገር ኢየሱስ ክርስቶስ አደረገ።

ከብዙ ዓመታት በፊት በካስማ ጉባኤ በቅዳሜ ምሽት ስብሰባ ውስጥ፣ ከብዙ ዓመታት መቅረት በኋላ ጓደኞቿ ወደ ቤተክርስቲያን እንድትመለስ እንደጋበዟት ነገር ግን ለምን መመለስ እንዳለባት አንድም ምክንያት ማሰብ እንዳልቻለች የነገረችኝን አንዲት ሴት አገኘው። እሷን ለማበረታታት እንዲህ አልኩኝ፣ “አዳኙ ያደረገልሽን ሁሉንም ነገሮች ስታስቢ፣ ተመልሰሽ እርሱን ለማምለክ እና ለማገልገል ብዙ ምክንያቶች አሉሽ።” “እርሱ ለእኔ ምን አደረገ?” ብላ ስትመል በጣም ተገረምኩኝ።

ዳግሞ ምፅዓት

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን ምን አደረገ? በሰማይ አባታችን ዕቅድ ውስጥ ከምድራዊ ሕይወት ጉዞአችን እስከ ዕጣ ፈንታ ለተዘረዘረው የሚያስፈልገውን ሁሉንም ነገር አደረገ። ስለዛ ዕቅድ አራት ዋና ገፅታዎች እናገራለሁ። በእነዚህ በእያንዳንዱ ውስጥ አንድያው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ማዕከላዊ አካል ነው። ይህን የሚያበረታታው “በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ሁሉ ራሱን በስፋት የሚያፈስ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ ስለዚህ ከሁሉ ነገሮች በላይ መልካም ነው” (1 ኛ ኔፊ 11፥22)።

1.

ከፋሲካ ሰንበት በፊት፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መጀመሪያ መናገር ወቅታዊ ነው። ከሞት መነሳት የእምነታችን መልሶ ማረጋገጫ የግል ምሰሶ ነው። ለትምህርታችን፣ ለባህሪያችን መነሳሳት እና ለወደፊታችን ተስፋ ትርጉም ይጨምራል።

የመጽሐፍ ቅዱስ እና የመጽሐፈ ሞርሞን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ግልፅ መግለጫዎችን ስለምናምን፣ በዚህ ምድር ላይ ለኖሩ ሁሉም ሟች ሰዎች ተመሳሳይ ትንሳኤ እንደሚመጣ የብዙ መጽሐፍ ቅዱሳት ትምህርቶችንም እንቀበላለን።1 ኢየሱስ እንዳስተማረው፣ “እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ” (ዮሐንስ 14፥19)። እና የእርሱ ሐዋርያ እንዲህ አስተማረ፣ “ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ” እናም “ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን [ይለብሳል]” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፥52፣ 54)።

ትንሳኤው

ነገር ግን ትንሳኤው ከዚህ ሟች አለመሆን ማረጋገጫ የበለጠ ነገር ይሰጠናል። ሟች ሕይወታችንን እንዴት እንደምንመለከት ይለውጣል።

ይህ ትንሳኤ እያንዳንዳችን እና የምንወደው ሰዎች የሚያጋጥመንን ምድራዊ ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችል እይታን እና ጥንካሬን ይሰጠናል። በውልደት ወይም በሟች ሕይወት ውስጥ ያገኘነውን አካላዊ፣ አዕምሮአዊ ወይም ስሜታዊ ጉድለቶችን ለመመልከት አዲስ መንገድን ይሰጠናል። ሃዘኖችን፣ ውደቀትን እና ብስጭቶችን ለመቋቋም ጥንካሬን ይሰጠናል። እያንዳንዳችን የተረጋገጠ ትንሳኤ ስላለን እነዚህ ሟች ጉድለቶች እና ተቃውሞዎች ጊዜያዊ ብቻ እንደሆኑ እናውቃለን።

ትንሳኤው በሟች ሕይወታችን ወቅት የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንድንጠብቅ ኃይለኛ ማበረታቻ ይሰጠናል። ከሞት ስንነሳ እና ወደ ተተነበየው የመጨረሻ ፍርድ ስንሄድ፣ ትንሳኤ ላደረጉት ሰዎች ቃል ለተገቡት የተመረጡ በረከቶች ብቁ መሆን እንፈልጋለን።2

እንደ ቤተሰቦች ለዘላለም መኖር እንችላለን።

በተጨማሪም፣ ትንሳኤው ከቤተሰብ አባሎቻችን—ማለትም ከባል፣ ከሚስት፣ ከልጆች፣ ከወላጆች እና ከትውልዶች—ጋር የመሆን እድልን ማጠቃለል የሚችለው ቃልኪዳን በሟች ሕይወት ውስጥ የቤተሰባችንን ሃላፊነቶች ለማሟላት ድንቅ ማበረታቻ ነው። በዚህ ሕይወት ውስጥ በጋራ በፍቅር ለመኖር ይረዳናል እናም የምንወዳቸው ሰዎች ሲሞቱ ያፅናናናል። እነዚህ ሟች መለያየቶች ጊዜያዊ ብቻ እንደሆኑ እናውቃለን እና የወደፊት አስደሳች መልሶ መገናኘትን እና ህብረትን እንጠብቃለን። ትንሳኤው ተስፋን እና ስንጠብቅ ታጋሽ እንድንሆን ጥንካሬን ይሰጠናል። የራሳችንን ሞት—ያለጊዜው የሚባለውን ሞትም ቢሆን እራሱ በብርታት እና በክብር እንድንገናኘው ያዘጋጅልናል።

እነዚህ ሁሉም የትንሳኤ ውጤቶች “ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን ምን አደረገ?” ለሚለው ጥያቄ የመጀመሪያ መልስ አካል ናቸው።

2.

ለብዙዎቻችን ከሃጢያቶቻችን ይቅር የመባል እድል የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ዋናው ትርጉም ነው። በአምልኮ በክብር እዲህ እንዘምራለን፦

ውዱን ደሙን በነፃ አፈሰሰ፤

ሕይወቱን በነፃ ሰጠ፣

ለጥፋተኛ ሃጢያት አልባ መስዋዕት፣

የሚሞትን ዓለም ለማዳን።3

ንስሃ ለሚገቡት ለሁሉም ሟቾች ሃጢያቶች መስዋዕት ለመሆን አዳኛችን እና ቤዛችን የማይገለፅ ስቃይን ተቋቋመ። ይህ የሃጢያት ክፍያ የመልካምነትን መጨረሻ ማለትም እንከን አልባውን ንፁህ ጠቦትለክፉው መጨረሻ መለኪያ ማለትም ለመላው ዓለም ሃጢያቶች ሰጠ። ወደ እግዚአብሔር መገኛ ወደ ዘላለም አባት በድጋሚ መግባት እንድንችል ከግላዊ ሃጢያታችን እንድንነፃ ለእያንዳንዳችን በርን ከፈተ። ይህ የተከፈተ በር ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች የቀረበ ነው። በአምልኮ እዲህ እንዘምራለን፦

ከመለኮታዊ ዙፋኑ ወደ ታች መውረዱ ያስገርመኛል

እንደ እኔ አይነት አመፀኛ እና ኩራተኛ ነብስን ለማዳን፣

እንደ እኔ ላለው ታላቅ ፍቅሩን ሊያካፍል።4

የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ታላቁ እና ሊገለፅ የማይችለው ውጤት የሚመሰረተው በእግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ባለው ፍቅር ላይ ነው። ይህ “የነፍስ ዋጋ”—እያንዳንዱ—“በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነው” የሚለውን የእርሱን አዋጅ ያረጋግጣል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እየሱስ ክርስቶስ በሰማይ አባታችን ፍቅር መልኩ ይህን ገለፀ፦ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ 3፥16)። በዘመናዊ ራዕይ ውስጥ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ እንዲህ አወጀ “ያመኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ አለምን በመውደድ እርሱ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠውን ስማ እናም አድምጥ፣ እንዲሁም ተመልከት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 34፥3)።

መጽሐፈ ሞርሞን “ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት”፣ “ፍፁም” እና “በክርስቶስ ፍፁም” ለመሆን እኛ “በሙሉ ኃይላችን፣ አዕምሮአችን እና ጉለበታችን እግዚአብሔርን መውደድ” በሚኖርብን ትምህርት መደምደሙ አያስገርምም (ሞሮኒ 10፥32–33)።ሞሮኒ 10፥32–33)። በፍቅር የተበረታታው የእርሱ እቅድ በፍቅር መቀበል ይኖርበታል።

3.

አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ምን አደረገልን? በነብያቶቹ ትምህርቶች እና በግል አገልግሎቱ አማካኝነት ኢየሱስ የደህንነትን ዕቅድ አስተማረን። ይህ ዕቅድ ፍጥረትን፣ የሕይወትን ዓላማ፣ የተቃውሞን አስፈላጊነት እና የምርጫን ስጦታ ያጠቃልላል። መታዘዝ ያለብንን ትዕዛዛት እና ቃልኪዳኖች እናም ወደ የሰማይ ወላጆቻችን የሚወስዱንን መለማመድ ያለብንን ስነስርዓቶች እንዲሁም አስተማረን።

የተራራ ስብከት

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእርሱን ትምህርት እንዲህ እናነባለን፦ “እኔ የአለም ብርሃን ነኝ፤ ለሚከተለኝ የህይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” (ዮሐንስ 8፥12)። በዘመናዊ ራዕይ ይህን እናነባለን፣ “እነሆ ጨለማም ሊጋርደው የማይችል ብርሃን… ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥9)። ትምህርቶቹን የምንከተል ከሆነ፣ በዚህ ሕይወት ውስጥ መንገዳችንን ያበራል እናም በሚቀጥለው ሕይወት ውስጥ ዕጣ ፈንታችንን ያረጋግጣል።

ስለሚወደን በዚህ ሟች ዓለም ነገሮች ላይ ሳይሆን በእርሱ ላይ እንድናተኩር ይጠይቀናል። በእርሱ ታላቅ የሰማይ እንጀራ ትምህርቱ፣ በዓለማዊ ነገሮች—ማለትም በምድር ላይ ሕይወትን የሚደግፉ ነገር ግን ለዘላለማዊ ሕይወት ምግብ በማይሰጡ ነገሮች የበለጠ ከሚሳቡ ሰዎች መካከል መሆን እንደሌለብን ኢየሱስ አስተማረ።5 ኢየሱስ ክርስቶስ “ተከተሉኝ” ብሎ በተደጋጋሚ እንደጋበዘን።6

4.

በመጨረሻም መጽሐፈ ሞርሞን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አካል እንዲህ ያስተምራል “እናም በመከራና በሁሉም ዓይነት ህመምና ፈተናዎች በመሰቃየት ይሄዳል፤ የህዝቡን ህመምና በሽታ በራሱ ላይ ይወስዳል የሚለውን ቃል ይፈፀም ዘንድ ይህ ይሆናል” (አልማ 7፥11)።

አዳኛችን እነዚህን ሟች ፈተናዎች ለምንድን ነው “በሁሉም ዓይነት” የተሰቃየው? አልማ እንዲህ ገለፀ፣ “አንጀቱ በምህረት ይሞላ ዘንድ፣ ድካማችንን በራሱ ላይ አደረገ እናም በስጋ ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ ያውቅ ዘንድ ይህንን ያደርጋል” (አልማ 7፥12)።

ክርስቶስ በጌተሰማኒ

አዳኛችን ፈተናዎቻችንን፣ ትግሎቻችንን፣ የልብ ህመሞቻችንን እና ስቃዮቻችንን ይሰማዋል እናም ያውቃል፣ ምክንያቱም እንደ የሃጢያት ክፍያው አካል ሁሉንም በፍቃደኝነት ስለተለማመዳቸው። ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳት ይህን ያረጋግጣሉ። አዲስ ኪዳን እንዲህ ያውጃል፣ “እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና” (ዕብራውያን 2፥18)። ኢሳይያስ እንዲህ አስተማረ፣ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ … አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ” (ኢሳይያስ 41፥10)። ማንኛውንም ዓይነት ሟች ድክመቶችን የሚሰቃዩ ሁሉ አዳኛችን ያን ዓይነት ህመም እንዳየ እናም በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት እንድንቋቋመው ለእያንዳንዳችን ጥንካሬን እንደሰጠን ማስታወስ አለባቸው።

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ይህን ሁሉ በሶስተኛው የእምነት አንቀፆቻችን እንዲህ አጠቃለለ የእምነት አንቀፆች 1፥3፦ “የወንጌሉን ህግጋትና ስነስርዓቶችን በማክበር፣ የሰው ዘሮች ሁሉ በክርስቶስ ኃጥያት ክፍያ በኩል መዳን እንደሚችሉ እናምናለን።”

“ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ምን አድርጎልኛል?” ብላ ያቺ እህት ጠየቀች። እያንዳንዳችን መለኮታዎ ዕጣ ፈንታችንን ለመሻት የሚያስችል ምድራዊ ልምድ እንዲኖረን በሰማይ አባታችን ዕቅድ መሰረት እርሱ “ሰማዮችን እና ምድርን ፈጠረ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥9)። እንደ የአብ ዕቅድ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ለእያንዳንዳችን አለመሞትን ሊያረጋግጥ ሞትን አሸነፈ። የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ለሃጢያቶቻችን ንስሃ ለመግባ እና ንፁህ ሆነን ወደ ሰማይ ቤታችን ለመመለስ ለእያንዳንዳችን እድልን ይሰጠናል። የእርሱ ትዕዛዛቶች እና ቃልኪዳኖች መንገዱን ያሳዩናል፣ እናም የእርሱ ክህነት ስነስርዓቶችን ለማከናወን ስልጣንን ይሰጣል። እናም አዳኛችን በመከራዎቻችን ውስጥ እንዴት እንደሚያጠነክረን ያውቅ ዘንድ በፍቃደኝነት ሁሉንም የሟች ህመሞች እና ድክመቶች ተለማመደ።

ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ሁሉ አደረግ ምክንያቱም ሁሉንም የእግዚአብሔርን ልጆች ስለሚወድ። ፍቅር ለሁሉም ነገር ማነሳሻ ነው እና ከመጀመሪያውም እንዲሁ ነበር። በዘመናዊ ራዕይ ውስጥ እግዚአብሔር እንዲህ ነግሮናል፣ “እርሱም … ወንድንና ሴትን በመልኩ እና በአምሳሉ ፈጠራቸው፣ … እናም እግዚአብሔርን እንዲወዱና እንዲያገለግሉ ትዕዛዛትን ሰጣቸው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥18–19)።

ስለዚህ ሁሉ እመሰክራለሁ እናም አዳኛችን ለእያንዳንዳችን ያደረገውን እንድናስታውስ እና ሁላችንም እንድንወደው እና እንድናገለግለው እፀልያለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።