አጠቃላይ ጉባኤ
ለምን የቃል ኪዳኑ መንገድ
የሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ለምን የቃል ኪዳኑ መንገድ

የቃል ኪዳኑ ጎዳና መለየት ልዩ እና ዘላለማዊ ትርጉም ያለው ነው።

በመላው አገልግሎታቸው ውስጥ፣ ፕሬዝዳንት ረስልኤም ኔልሰን እግዚአብሔር ከልጆቹ ጋር ስላለው ቃልኪዳኖች አጠኑ እንዲሁም አስተማሩ። እርሱ እራሱ የቃልኪዳኑን መንገዱ የሚጓዝ ብሩህ ምሳሌ ነው። እንደ ቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያው መልዕክታቸው ፕሬዝዳንት ኔልሰን እንዲህ አሉ፦

ቃል ኪዳኖችን ከእርሱ ጋር በመግባት እና ከዚያም እነዚህን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ አዳኝን ለመከተል በልብ የምትወስኑበት በሁሉም ቦታ ላሉት ወንዶች፣ ሴቶች፣እና ልጆች ለሚገኙት ለእያንዳንዱ መንፈሳዊ በረከቶች እና እድሎች በር ይከፍታል።

“… የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና በዚያ የምትገቡት ቃል ኪዳኖች ህይወታችሁን፣ ጋብቻችሁን፣ እና ቤተሰባችሁን፣ እናም የጠላትን ጥቃቶች ለመቋቋም ያላችሁን ችሎታ ለማጠናከር ዋና ቁልፎች ናቸው። በቤተመቅደስ ውስጥ በምታመልኩበት እና ለቅድመ ዘመዶቻችሁ የምታደርጉት አገልግሎት በተጨማሪ የግል ራዕይና ሰላም ይባርካችኋል እናም በቃል ኪዳን መንገድ ለመቆየት ያላችሁን የልብ ውሳኔ ያጠነክራል።”1

የቃልኪዳኑ መንገድ ምንድን ነው? ወደ ሰለስቲያል የእግዚአብሔር መንግስት የሚመራ አንዱ መንገድ ነው። በጥምቀት በር ላይ መንገዱን እንጀምራለን እናም ከዛ “ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖ[ረን] [ሁለቱ ታላቅ ትዕዛዞች] በክርስቶስ ባ[ለነን] ፅኑነት [እንቀጥላለን] … እስከመጨረሻው።”2 (በነገራችን ላይ ከሟች ሕይወት በላይ በሚዘልቀው) በቃልኪዳኑ መንገድ ውስጥ ለደህንነት እና ከፍ ለማለት አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም ስነስርዓቶችን እና ቃልኪኖችን እንቀበላለን።

የእኛ ሁሉንም የያዘ የቃልኪዳን ቁርጠኝነት የእግዚብሔርን ፍቃድ ማድረግ ነው እናም “እኛን ባዘዘን በሁሉም ነገር ለትዕዛዛቱ ታዛዥ መሆን” ነው።3 በእየቀኑ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን መርሆዎች እና ትዕዛዞች መከተል በሕይወት ውስጥ የሚያስደስት እና በጣም የሚያረካ ነው። በአንድ መልኩ፣ አንድ ሰው ትልቅ ብዙ ችግሮችን እና ፀፀቶችን ያስወግዳል። የእስፖርትን ምሳሌ ልጠቀም። በቴኒስ ጨዋታ ውስጥ ያልተገፋ ስህተት ተብሎ የሚጠራ ነገር አለ። እነዚህ ነገሮች መጫወት የሚቻልን ኳስ መረቡ ላይ መምታት እና ሲሰርቡ ሁለቴ መሳሳት ናቸው። ያልተገፉ ስህተቶች የተቀናቃኝ ችሎታ ሳይሆን የተጫዋቹ ስህተት ውጤት ተብለው ይወሰዳሉ።

ብዙ ጊዜ ችግሮቻችን ወይም ፈተናዎቻችን በራሳችን ምክንያት፣ በደካማ ምርጫዎች ውጤት ወይም “ባልተገፉ ስህተቶች” ውጤት የመጡ ናቸው ብለን ማለት እንችላለን። የቃልኪዳኑን መንገድ በታታሪነት ስንከተል ብዙ “ያልተገፉ ስህተቶችን” በተፈጥሮ እናስወግዳለን። የሱስን የተለያዩ መልኮች እናስወግዳለን። ሐቀኛ ያልሆነ ተግባር ገደል ውስጥ አንወድቅም። የክፋት እና የአለመታመን ገደልን እንሻገራለን። ታዋቂ ቢሆኑም እንኳን አካላዊ እና መንፈሳዊ ጤንነታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሰዎችን እና ነገሮችን እናልፋለን። ሌሎችን የሚጎዱ ወይም የሚያሰናክሉ ምርጫዎችን እናስወግዳለን እናም በተቃራኒው የግል ስነስርዓት እና አገልግሎት ልምዶችን እናገኛለን።4

ሽማግሌ ጄ.ጎልደን ኪምባል እንዲህ ብለዋል ይባላል፣ “ቀጥተኛውን እና ቀጭኑን መንገድ ሁሌም ላልጓዝ እችል ይሆናል፣ ነገር ግን በተቻለኝ ጊዜ ልሻገረው እጥራለሁ።”5 በጣም ወሳኝ በሆነ ወቅት፣ ወንድም ኪምባል በቃልኪዳን መንገድ ላይ መሻገር ብቻ ሳይሆን መቆየት የሚወገዱ መከራን በአንድ መልኩ ማስወገድ እና በሌላኛው ደግሞ የማይወገዱ የሕይወት ሀዘኖችን በውጤታማነት ማስተናገድ የእኛ ታላቅ ተስፋ እንደሆነ እንደሚስማማ እርግጠኛ ነኝ።

የተወሰኑት እንዲህ ሊሉ ይችላሉ፣ “በጥምቀት ወይም ካለጥምቀት ጥሩ ምርጫዎችን ማድረግ እችላለሁ፣ የተከበርኩኝ እና ውጤታማ ሰው ለመሆን ቃልኪዳኖችን አልፈልግም።” በእርግጥ፣ እራሳቸው በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ ሳይሆኑ በመንገዱ ላይ ያሉትን ሰዎች ምርጫዎች እና አስተዋፅኦ የሚያስመስሉ ብዙዎች አሉ። “የቃልኪዳን ዘላቂነት” መንገድ የመራመድ በረከቶችን ያጭዳሉ ማለት ትችላላችሁ። የቃልኪዳኑ መንገድ ልዩነት ታዲያ ምንድን ነው?

በእርግጥ ልዩነቱ በተለየ ሁኔታ እና ለዘላለም አስፈላጊ ነው። የመታዘዛችንን ተፈጥሮን፣ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ቁርጠኝነት ባህሪን፣ የምንቀበለው መለኮታዊ እርዳታን፣ እንደ የቃልኪዳን ህዝቦች ከመሰብሰብ ጋር የሚያያዙ በረከቶችን እና በጣም ጠቃሚ በሆነ መልኩ የእኛ የዘላለም ውርስን ያካትታል።

ቁርጠኛ መታዘዝ

መጀመሪያ ለእግዚአብሔር ያለን መታዘዝ ተፈጥሮ ነው። መልካም ምክንያትን ከመኖር በዘለለ ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው በሁሉም ቃል ለመኖር በክብር እንቆርጣለን። በዚህ ውስጥ በመጠመቅ፣ “በስጋ መሰረት ለሰው ልጆች በአብ ፊት እራሱን እንዳዋረደ ስላሳየ፣ እናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ለእርሱ ታዛዥ መሆኑን ለአባቱ ስለመሰከረ” የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ እንከተላለን።6

በቃልኪዳኖች፣ ስህተቶችን ከማስወገድ ወይም በውሳኔዎቻችን ብልህ ከመሆን የዘለለ ዓላማ አለን። ለምርጫዎቻችን እና ሕይወቶቻችን ለእግዚአብሔር ሃላፊነት ይሰማናል። በላያችን ላይ የክርስቶስን ስም እንወስዳለን። በኢየሱስ ምስክርነት ደፋር በመሆን እና ክርስቶስ መሰል ባህሪን በማዳበር—በክርስቶስ ላይ አተኩረናል።

በቃልኪዳኖች፣ ለወንጌል መርሆዎች መታዘዝ በነፍሳችን ውስጥ ስር የሰደደ ይሆናል። በትዳራቸው ጊዜ ሚስትዬዋ በቤተክርስቲያን ውስጥ የማትሳተፍ ስለነበረች እና ባልዬው ደግሞ የቤተክርስቲያን አባል ሆኖ ስለማያውቅ አንድን ጥንዶች አወቃለሁ። በትክክለኛ ስማቸው ሳይሆን ሜሪ እና ጆን ብዬ እጠራቸዋለሁ። ልጆች ወደ አላማቸው ውስጥ ሲገቡ፣ ሜሪ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው “በጌታ ምክርና በተግሳፅ” እነሱን የማሳደግ አስፈላጊነት አጥብቆ ተሰማት።7 ጆን ድጋፍ የሚሰጥ ነበር። ወንጌልን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስተማር ሜሪ ቤት ለመሆን የተወሰኑ መስዋዕቶችን አደረገች። ቤተሰቧ የቤተክርስቲያን አምልኮን እና እንቅስቃሴዎችን ሙሉ ጥቅም እንዲወስድ እሷ አረጋገጠች። ሜሪ እና ጆን የምሳሌ ወላጆች ሆኑ እናም ልጆቻቸው (ሁሉም ጠንካራ ወንድ ልጆች) በእምነት እና በወንጌል መርሆዎች እና አቋሞች አምልኮ አደጉ።

የጆን ወላጆች ማለትም የልጆቹ አያቶች በመላው የልጅ ልጆቻቸው ሕይወት እና ክንዋኔዎች ተደስተው ነበር፣ ነገር ግን ለቤተክርስቲያኗ ባላቸው ጥላቻ ምክንያት ይህንን ስኬት ለሜሪ እና ለጆን የወላጅነት ክህሎት ሊያመካኙት ፈለጉ። ጆን የቤተክርስቲያን አባል ባይሆንም እንኳን፣ ያ ፈተና ያለተቃውሞ እንዲያልፍ አልፈለገም። የወንጌል ትምህርቶችን ፍሬዎች—ማለትም ልጆቹ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያዩትን ነገሮች እንዲሁም በቤት ውስጥ እየሆነ የነበረውን እየመሰከሩ እንደሆነ አጥብቆ ተናገረ።

ጆን እራሱ በመንፈስ፣ በሚስቱ ፍቅር እና ምሳሌ እና በወንድ ልጆቹ ጉትጎታ ተፅዕኖ እየደረሰበት ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ በይበልጥ ለዋርድ አባሎች እና ጓደኞች ደስታ ሲል ተጠመቀ።

ለእነሱ እና ለወንድ ልጆቻቸው ሕይወት ከፈተናዎች ውጪ ባይሆንም፣ ሜሪ እና ጆን የበረከቶቻቸው ስር በእርግጥ የወንጌል ቃልኪዳን እንደሆነ በሙሉ ልብ አረጋገጡ። የእግዚአብሔር ለኤርምያስ ቃላት በልጆቻቸው እንዲሁም በራሳቸው ሕይወቶች ውስጥ ሲፈፀም አይተዋል፦ “ህጌንም በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።”8

ከእግዚአብሔር ጋር መታሰር

ሁለተኛው የቃልኪዳኑ መንገድ የተለየ ገፅታ የእኛ ከአማልክት ጋር ያለን ግንኙነት ነው። እግዚአብሔር ለልጆቹ የሚሰጠው ቃልኪዳኖች እኛን ከመምራት በላይ ናቸው። እኛን ከእርሱ ጋር ያስራሉ እናም ከእርሱ ጋር በመታሰር ሁሉኑም ነገሮች ማሸነፍ እችላለን።9

ትክክለኛ መረጃ ባሌለው አንድ የጋዜጣ ዘጋቢ የተፃፈን ዘገባ አነበብኩኝ እሱም ለሙታን የምንፈፅመው ጥምቀት የፎቶዎችን ጥቅል በውኃ ውስጥ በማጥለቅ እንደሆነ ገለፀ። ከዛ ፎቶግራፉ ላይ ስማቸው የሚገኘው ሰዎች በሙሉ እንደተጠመቁ ይቆጠራል። ያ መንገድ ውጤታማ ይሆን ነበር ነገር ግን የእያንዳንዱን ነፍስ ዘላለማዊ ዋጋ እና ከእግዚአብሔር ጋር የግላዊ ቃልኪዳን ጠቀሜታን ችላ ይላል።

“[ኢየሱስ] እንዲህ አለ … ፦ በጠባቡ ደጅ ግቡ፤ እናም ወደ ህይወት የሚወስደው ደጁ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ስለሆነ፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸውና”10 በምሳሌያዊ አነጋገር ይህ ደጁ በጣም ቀጭን በመሆኑ የተነሳ አንድን ሰው ብቻ ነው ለማስገባት የሚፈቅደው። እያንዳንዱ ለእግዚአብሔር ግላዊ ቁርጠኝነትን ያደርጋል በምላሹ በስም እሱ ወይም እሷ ሙሉ በሙሉ ለሰዓት እና ለዘላለም መመካት እንደሚችል/ምትችል ከእርሱ ግላዊ ቃልኪዳን ይቀበላሉ። በስነስርዓቶች እና በቃልኪዳኖች ነው “የአምላክነት ሀይል የሚገለፀው” በህይወታችን ውስጥ።11

መለኮታዊ እርዳታ

ይህ ሶስተኛው የተለዩ የቃልኪዳኑ መንገድ በረከቶችን እንድናስብ ይመራናል። እግዚአብሔር ቃልኪዳን ለሚገቡ ሰዎች ቃልኪዳን ጠባቂዎች እንዲሆኑ ለማገዝ ለመረዳት የማይቻልን ስጦታ፦ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይሰጣል። ይህ ስጦታ ቀጣይነት ላለው የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት፣ ጥበቃ እና ምሪት መብት ነው።12 እንዲሁም አፅናኙ ተብሎ የሚጠራው መንፈስ ቅዱስ “በተስፋ እናም በፍፁም ፍቅር ይሞላል።”13 እርሱ “ሁሉንም ነገሮች ያውቃል፣ እና ስለአብ እና ስለወልድ ይመሰክራል”14 የእርሱ ምስክሮች ለመሆን ቃል ስለምንገባው ክርስቶስ።15

በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ ከሃጢያት የይቅርታ እና የንፁ መሆን አስፈላጊ በረከቶችን እናገኛለን። በመንፈስ ቅዱስ የሚተዳደር በመለኮታዊ ፀጋ ብቻ መምጣት የሚችል ተስፋ ነው። ጌታ እንዲህ ይላል፣ “እንግዲህ ትዕዛዜ ይህች ናት፥ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ንሰሃ ግቡ፣ እናም መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ትቀደሱ ዘንድ፤ በመጨረሻው ቀን በፊቴ ያለእንከን ትቆሙ ዘንድ ወደ እኔ ኑ፣ እናም በስሜ ተጠመቁ።”16

ከቃልኪዳኑ ህዝቦች ጋር ሰብስቡ

አራተኛ፦ የቃልኪዳኑን መንገድ የሚከተሉት ሰዎች በብዙ መለኮታዊ ስብሰባዎች ውስጥ አስደናቂ በረከቶችን ያገኛሉ። ለረዝም ጊዜ የተበታተኑት የእስራኤል ጎሳዎች ወደ ውርስ ምድራቸው ስለ ትክክለኛው መሰብሰብ ትንቢቶች በመላው መጽሐፍ ቅዱሳት ውስጥ ይገኛሉ።17 የእነዛ ትንቢቶች እና ቃልኪዳኖች መሟላት የቃልኪዳኑ ህዝቦችን በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግስት ወደሆነው ወደ ቤተክርስቲያን መሰብሰቡ አሁን እየቀጠለ ነው። ፕሬዝዳንት ኔልሰን እንዲህ ገለፁ፣ “ስለ መሰብሰብ፣ ስናወራ እያልን ያለነው ይህን ቀላል እውነታ ነው፤ እያንዳንዱ የሰማይ አባት ልጆች፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የተመለሰው ወንጌል መልእክትን መስማት ይገባቸዋል።”18

ጌታ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትን እንዲህ ያዛል፣ “ለህዝቦች መመሪያ ትሆኑ ዘንድ ተነሱ እና አብሩ፤ … በፅዮን ምድርና በካስማዎቿ ላይ አብሮ መሰብሰቡ ከአውሎ ነፋስ፣ እና ቁጣም ሳይቀላቀል በምድር ሁሉ ላይ ከሚፈሰው መጠበቂያ እና መሸሸጊያ ይሆን ዘንድ ተነሱ እናም አብሩ።”19

በጌታ ቀን በጸሎት ቤት ውስጥ የቃልኪዳኑ ህዝቦች “ከዓለም ነገሮች [ራሳችንን] ነውር የሌለበት ለማድረግ” ሳምንታዊ ስብሰባ አለን።20 የኢየሱስ ክርስቶስን የሃጢያት ክፍያ ለማስታወስ የቅዱስ ቁርባን ዳቦን እና ውኃን የመቋደስ ስብሰባ ነው እናም “ለመፆም እናም ለመጸለይ እናም እያንዳንዳችን ለነፍ[ሳችን] ደህንነት እርስ በርሳችን የመነጋገሪያ” ጊዜ ነው።21 ወጣት ሳለሁ፣ በአጠቃላይ ትምህርት ቤት ክፍሌ ውስጥ እኔ ብቻ ነብርኩኝ የቤተክርስቲያኗ አባል የነበርኩት። በትምህርት ቤት ውስጥ በብዙ መልካም ጓደኞች ግንኙነት ተደስቻለሁ ነገር ግን በእያንዳንዱ ሳምንት በመንፈስ እንዲሁም በስጋ እራሴን ለማዝናናት እና ለማደስ በዚህ የሰንበት ስብሰባ ላይ በከፍተኛ ተመክቼ እራሴን አገኘው። በዚህ በወቅታዊው ወረርሽኝ ጊዜ የዚህን ተደጋጋሚ የቃልኪዳን ስብሰባን እንዴት እንደናፈቅን እና እንደበፊቱ በድጋሜ በአንድ ላይ የምንሰበሰብበትን ጊዜ እንዴት በጉጉት እንደምንጠብቅ።

የቃልኪዳኑ ህዝቦች ስነስርዓቶቹን፣ በረከቶቹን እና በተለየ መልኩ እዛ የሚገኘውን ራዕይ ለመቀበል ወደ ጌታ ቤት ወደ ቤተመቅደስ ይሰበሰባሉ። ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ አስተማረ፣ “በዓለም ዙሪያ በማንም የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን የእግዚአብሔር ህዝቦች … የመሰብሰቡ ዓላማ ምንድን ነበር? … ዋናው ዓላማ እርሱ ለህዝቡ የቤቱን ስርዓቶች እና የመንግስቱን ክብሮች ለህዝቡ ለመግለጽ የሚችልበት፣ እና ህዝብን የደህንነት መንገድን የሚያስተምርበት ቤት ለጌታ እንዲገነቡ ነው፤ ምክንያቱም አንዳንድ ስርዓቶች እና መሰረታዊ መርሆች፣ ሲማሩ እና ሲጠቀሙበት፣ ለዚህ አላማ በተሰሩ ቦታዎች ወይም ቤቶች ውስጥ መከናወን አለባቸው።”22

የቃልኪዳኑን ተስፋዎች ውረሱ

በመጨረሻ፣ የቃልኪዳኑን መንገድ በመከተል ብቻ ነው እግዚአብሔር ብቻ መስጠት የሚችለውን የአብርሐምን፣ የይሳቅን እና የያዕቆብን በረከቶች የመንወርሰው እነሱም የደህንነት እና ከፍ የማለት የመጨረሻ በረከቶች ናቸው።23

የመጽሐፍ ቅዱስ የቃልኪዳን ህዝቦች መግለጫ ብዙ ጊዜ የአብርሐም እውነተኛ ዘሮች ወይም “ቤተ እስራኤሎች” አድርጎ ይሰይማል። ነገር ግን የቃልኪዳኑ ህዝቦች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የሚቀበሉ ሁሉንም ሰዎች ያካትታል።24 ጳውሎስ እንዲህ ገለፀ፦

“የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። …

“እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሐም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።”25

ለቃልኪዳኖቻቸው ታማኝ የሚሆኑት ሰዎች “በጻድቃን ትንሳኤ የሚመጡት ናቸው።”26 እነሱ “የአዲስ ኪዳን አማላጅ በሆነው በኢየሱስ ፍፁም የሆኑ [ናቸው]። … እነዚህ ሰውነታቸው ሰለስቲያል የሆኑ ናቸው፣ ክብራቸውም እንደ ጸሀይ፣ እንዲሁም ከሁሉም በላይ በሆነ የእግዚአብሔር ክብር ነው።”27 “ስለዚህ፣ ሁሉም ነገሮች የእነርሱ ናቸው፣ በህይወትም ይሁን በሞት፣ ወይም አሁን ያሉ ነገሮች ወይም ወደፊት የሚመጡት ነገሮች፣ ሁሉም የእነርሱ ናቸውም እነርሱ የክርስቶስ ናቸው፣ እናም ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።”28

የነብዩን በቃልኪዳን መንገድ ላይ የመቆየት ጥሪን እንስማ። ኔፊ እኛን እና የእኛን ጊዜ ተመለከተ እናም እንዲህ ዘገበ፦ “እኔ ኔፊ በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃልኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ ኃይል ሲወርድ ተመለከትኩ፤ እነርሱም ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ።”29

በጌታ ቃልኪዳኖች ውስጥ ከኔፊ ጋር፣ “ነፍሴ ትደሰታለች።”30 በፋሲካ ሰንበት፣ ትንሳኤው ተስፋችን እና በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ እና በመጨረሻው ላይ ቃል ለተገባው ለሁሉም ነገሮች ማረጋገጫ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም