አጠቃላይ ጉባኤ
በመለኮታዊ የተነሳሳውን ህገ-መንግስት መከላከል
የሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በመለኮታዊ የተነሳሳውን ህገ-መንግስት መከላከል

በመለኮታዊ መነሳሳት ላይ ያለን እምነታችን ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የዩናይትድ ስቴትስን ህገ-መንግስት እና ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን እንድንደግፍ እና እንድንጠብቅ ልዩ ሃላፊነትን ይሰጣል።

በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ፣ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የተነሳሳ ህገ-መንግስት ለመናገር ተሰምቶኛል። ይህ ህገ-መንግስት በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለአባሎቻችን የተለየ ጠቀሜታ አለው ነገር ግን በዓለም ዙሪያ ላሉ ህገ-መንግስታት የጋራ ቅርስ ነው።

I.

ህገ-መንግስት የመንግስት መሰረት ነው። ለመንግስት ኃይሎች ልምምድ መዋቅርን እና ገደቦችን ይሰጣል። የዩናይትድስ ስቴትስ ህገ-መንግስት ዛሬ በተግባር ላይ ያለ የቆየ የተፃፈ ህገ-መንግስት ነው። ምንም እንኳን በመጀመሪያ ላይ ትንሽ ቁጥር ባላቸው ግዛቶች በስራ ላይ ቢውልም፣ በትንሽ ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙሪያ አርአያ ሆነ። ዛሬ እያንዳንዱ አገራት ሶስቱን ሳይጨምር የተፃፈን ህገ-መንግስት ይጠቀማሉ።1

በዚህ ንግግሮች ውስጥ ለማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ሌላ ቡድን አልናገርም። ከ60 ዓመታት በላይ ስላጠናሁት ስለ ዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት እናገራለሁ። ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድቤት ዋና ዳኛ እንደ የህግ ፀሀፊ በመሆን ከነበረኝ ልምድ እናገራለሁ። ለ15 ዓመታት እንደ ህግ መምህር እና ለሶስት ዓመት ተኩል በዩታ አጠቃላይ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደ ዳኛ በማገልገሌ እናገራለሁ። በጣም አስፈላጊ በሆነ መልኩ ለ37 ዓመታት የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ በመሆን ለእርሱ በዳግም ለተመለሰው ቤተክርስቲያን ስራ ተግባራዊ በሆነ መልኩ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት መለኮታዊ መነሳሳት ትርጉም ለማጥናት ባለኝ ሃላፊነት መሰረት እናገራለሁ።

የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት የተለየ ነው ምክንያቱም “ለሁሉም ስጋ ለባሽ መብት እና ጥበቃ”እንዲሆን እግዚአበሔር እራሱ እንደመሰረተው]” ስለገለጸ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥77፤ ደግሞም ቁጥር ቁጥር 80ይመልከቱ) ። ለዛ ነው ይህ ህገ-መንግስት ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙሪያ በተለየ ሁኔታ አሳሳቢ የሆነው። በዓለም ሌላ አገራት ውስጥ መርሆዎቹ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ወይም እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ መወሰን የራሳቸው ጉዳይ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስን ህገ-መንግስት በመመስረት የእግዚአብሔር ዓላማ ምንድን ነበር? በስነ ምግባር ነፃ ምርጫ ትምህርት ውስጥ እናያለን። በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን የመጀመሪያ አስርተ አመት ውስጥ አባላቷ በምዕራባዊ ድንበር ላይ በግል እና በጋራ መሰደድ ተሰቃይተው ነበር። በከፊል ይህ የሆነው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የነበረውን የሰውን ልጅ ባርነት በመቃወማቸው ነው። በእነዚህ አሳዛኝ ሁኔታዎች ውስጥ እግዚአብሔር በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ስለ ትምህርቱ የዘላለም እውነታዎችን ገለፀ።

እግዚአብሔር ለልጆቹ የስነ ምግባር ነፃ ምርጫን—የመወሰን እና የመተግበር ኃይልን ሰጠ። ለዚያ ወኪል አሠራር በጣም ተፈላጊ ሁኔታ ወንዶች እና ሴቶች እንደየግል ምርጫቸው የመንቀሳቀስ ከፍተኛው ነፃነት ነው። ከዚያም ራዕዩ እንዲህ ይገልፃል፣ “እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ሃጢያቶች በፍርድ ቀን ይጠየቅበ[ታል]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥78)። “ስለዚህ፣ ጌታ እንደዚህ ገለፀ፣ “ማንም ሰው ለሌላ በባሪያነት መተሳሰሩ ትክክል አይደለም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥79)። ይህ የሰው ባርነት በግልፅ ትክክል አይደለም ማለት ነው። እናም ተመሳሳይ በሆነ መርሆ ዜጎች መሪዎቻችውን ወይም ህጋቸውን ሚያረቁትን በመምረጥ ላይ ድምፅ አለማግኘት ትክክል አይደለም።

II.

የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት በመለኮታዊ የመነሳሳቱ እምነታችን፣ መለኮታዊ ራዕይ እያንዳንዱ ቃልን እና ሃረግን ፃፈ ማለት አይደለም፣ ለምሳሌ ከእያንዳንዱ ስቴት የተወካዮችን ቁጥር ወይም የእያንዳንዱን ዝቅተኛ እድሜ ድንጋጌዎችን አስመልክቶ።2 ህገ-መንግስቱ “ሙሉ በሙሉ የዳበረ ሰነድ” አልነበረም ፕሬዘዳንት ጄ ሩበን ክላርክ እንዳሉት። “በተቃራኒው፣” ብለው እንዲህ ገለፁ፣ “በእድገት ላይ ያለን ዓለም የሚቀያየር ፍላጎት ለማሟላት መዳበር እና ማደግ እንዳለበት እናምናለን።”3 ለምሳሌ፣ የተነሳሱት ማሻሻያዎች ባርነትን አስወገዱ እናም ለሴቶች የመምረጥ መብትን ሰጡ። ቢሆንም፣ ሕገ መንግስቱን በሚተረጎም እያንዳንዱ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ውስጥ መነሳሳት አላየንም።

የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግሥት ቢያንስ በአምስት በመለኮታዊ መንፈስ መሪነት መርሆዎችን ይይዛል ብዬ አምናለሁ።4

መጀመሪያ የመንግስት ኃይል ምንጭ ህዝብ የመሆኑ መርሆ ነው። ሉዓላዊ ኃይል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከነገሥታት መለኮታዊ መብት ወይም ከወታደራዊ ኃይል እንደሚመጣ በሚታመንበት ወቅት፣ ሉዓላዊ ኃይልን ለሕዝብ መስጠት ማለት አብዮታዊ ነበር። ፈላስፎች ስለዚህ ተሟግተው ነበር፣ ነገር ግን የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት ይህን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው ነበር። ሉዓላዊ ኃይልን በህዝቡ ማድረግ ማለት ወራሪዎች ወይም ሌላ የህዝብ ቡድኖች ለማስፈራራት ወይም የመንግስትን ተግባር ለመግፋት ጣልቃ መግባት ይችላሉ ማለት አይደለም ። ህገ-መንግስት ህዝቡ ኃይላቸውን በተመረጡ ተወካዮች የሚለማመዱበትን ህገ-መንግስታዊ የዲሞክራሲ ሪፐብሊክን መሰረተ።

ሁለተኛው የተነሳሳ መርሆ በአገር እና በንኡስ ክልሎቹ መካከል የውክልና የኃይል መከፋፈል ነው። በፌደራላዊ ስርዓታችን ውስጥ፣ ይህ ታይቶ የማይታወቅ መርሆ አንድ አንድ ጊዜ በተነሳሱ ማሻሻያዎች ተቀይሯል ለምሳሌ ከዚ በፊት እንደተጠቀሱት ባርነትን ባስወገዱት እና ለሴቶች የመምረጥ መብትን በሰጡት። ጠቃሚ በሆነ ሁኔታ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት ለብሔራዊ መንግስት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የሰጠውን የኃይሎች መለማመድ ይገድባል እናም ሌላ ሁሉንም የመንግስት ኃይሎች “ለስቴቶቹ በቅደም ተከተል ወይም ለህዝቡ” ይጠብቃል።5

ሌላኛው የተነሳሳ መርሆ የኃይሎች መለየት ነው። ከእኛ 1787 (እ.አ.አ) የህገ-መንግስታዊ ስብሰባ አንድ ክፍለ ዘመን በፊት፣ የእንግሊዙ ፓርላማ የተወሰኑ ኃይሎችን ከንጉሱ በመንጠቅ የህግ አውጪ እና የህግ አስፈፃሚ የስልጣን መለየትን መሰረተ። የአሜሪካው ስብሰባ መነሳሳት እራሱን የቻለ ህግ አስፈፃሚ፣ ህግ አውጪ እና ህግ አስከባሪ ኃይሎችን እርስ በእርሳቸው መቆጣጠርን እንዲለማመዱ መወከል ነበር።

አራተኛው የመነሳሳት መርሆ የግለሰብ መብቶች ጠቃሚ ማረጋገጫዎች ስብስብ ነው፣ እናም ህገ-መንግስቱ ተግባር ላይ ከዋለ ከሶስት ዓመት በኋላ ስራ ላይ በዋለው የመብቶች መጠየቂያ ህግ ውስጥ የመንግስት ስልጣንን ይገድባል። የመብቶች መጠየቂያ ህግ አዲስ አልነበረም። እዚህ መነሳሳቱ በማግና ካርታ በመጀመር በእንግሊዝ ውስጥ በተመሰረተው የመርሆዎች ትግበራ ላይ ነበር። የህገ-መንግስቱ ፀሐፊዎች እነዚህን ያውቁ ነበር ምክንያቱም የተወሰኑ የቅኝ ገዥ ሰነዶች እንደዚህ ዓይነት ማረጋገጫ ስለነበራቸው።

ካለ መብቶች መጠየቂያ ህግ፣ አሜሪካ ከሶስት አስርተ ዓመታት በኋላ ለሆነው ለተመለሰው ወንጌል እንደ አስተናጋጅ አገር ሆና አታገለግልም ነበር። በህዝብ ቢሮ ምንም ዓይነት የሐይማኖት ፈተና መኖር ባለመቻሉ በቀዳሚው ደንብ ውስጥ መለኮታዊ መነሳሳት ነበር፣6 ነገር ግን የሐይማኖት ነፃነት እና ኢድርጅታዊነት በመጀመሪያው ማሻሻያ ውስጥ መጨመር በጣም ጠቃሚ ነበር። በመጀመሪያው ማሻሻያ ውስጥ የመናገር እና የሚዲያ ነፃነቶች እና በሌላ ማሻሻያዎች ውስጥ ለምሳሌ እንደ የወንጀል ክስ ባለው የግል ጥበቃዎች መለኮታዊ መነሳሳትን እናያለን።

ምስል
እኛ ህዝቦች

አምስተኛው እና የመጨረሻው፣ በመላው ህገ-መንግስት ጠቃሚ ዓላማ ላይ መለኮታዊ መነሳሳትን አያለሁ። እኛ በግለሰቦች ሳይሆን በሕግልንመራ ይገባል ፣ እናም ታማኝነታችን ለህገ-መንግስቱ እና መርሆዎቹ እና አሠራሮቹ እንጂ ለማንም የቢሮ ባለቤትአይደለም። በዚህ መንገድ ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል መሆን አለባቸው። እነዚህ መርሆዎች በአንዳንድ አገሮች ዲሞክራሲን ያበላሸውን የራስ-ሰር ምኞት ያግዳሉ። ማንኛውም የሶስቱ የመንግስት ቅርንጫፍ ሌላውን መጫን የለበትም ወይም ሌላውን እርስ በእርስ ከመቆጣጠር ትክክለኛ የህገ-መንግስት ትግበራዎች ማቆም የለበትም ማለት ነው።

III.

የዩናይትድ ስቴትስ ሕገ መንግሥት በመለኮታዊ መንፈስ አነሳሽነት መርሆዎች ቢኖሩም፣ ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ሲተገበሩ የታሰቧቸው ውጤቶች ሁልጊዜ አልተሳኩም። የህግ ማውጣት ጠቃሚ ርዕሶች እንደ የቤተሰብ ግንኙነትን የሚገዙ ህጎች በፌደራላዊ መንግስት ከስቴቶች ተወስደዋል። የመጀመሪያው ማሻሻያ የሚያረጋግጠው የመናገር ነፃነት አንድ አንድ ጊዜ የማይወደድ ንግግርን በመሸፈን ተበክሏል። የኃይሎች መከፋፈል መርሆ የአንድን የመንግስት ቅርንጫፍ የውጣ ውረድ ልምምድ ወይም ለሌላው የተወከሉ ኃሎችን መግታት ሁሌም በግፊት ላይ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስን የተነሳሳ የህገ-መንግስት መርሆዎችን ዝቅ የሚያደርጉ ሌሎች ማስፈራሪያዎች አሉ። የህገ-መንግስት መቆም ለነፃነት እና እራስን ለመግዛት ዓላማ ሳይሆን ወቅታዊ ማህበራዊ ዝንባሌዎችን ለመመስረቱ ምክንያት በማድረግ በመተካት ሙከራዎች ቀንሷል። የህገ-መንግስት ስላጣን መርሆዎቹን ችላ በሚሉ እጩዎች ወይም ባለስልጣናት ቀለል ተደርጓል። የህገ-መንግስት ክብር እና ኃይል የስልጣን ምንጭ እና የመንግስትን ስልጣን ገዳቢ ከፍ ያለ ነገር አድርጎ ከመውሰድ ይልቅ እንደ የታማኝነት ፈተና ወይም የፖለቲካ መፈክር አድርገው በሚገልፁት ሰዎች ቀንሷል።

4.

በመለኮታዊ መነሳሳት ላይ ያለን እምነታችን ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የዩናይትድ ስቴትስን ህገ-መንግስት እና ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን በምንኖርበት ቦታ እንድንደግፍ እና እንድንጠብቅ ልዩ ሃላፊነትን ይሰጣል። በጌታ ማመን አለብን እናም ስለዚህ አገር ወደፊት አዎንታዊ መሆን አለብን።

ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሌላ ምን ማድረግ ያስፈልጋቸዋል? ሁሉንም አገራት እና መሪዎቻቸውን እንዲመራ እና እንዲባርክ ለጌታ መፀለይ አለብን። ይህ የእምነት አንቀፃችን አካል ነው። ለፕሬዘዳንቶች እና መሪዎች ተገዥ መሆን7 በእርግጥ ለተቃራኒ ግለሰብ ህጎች እና ፖሊሲዎች እንቅፋት አለመሆንን ይይዛል። በህገ-መንግስታችን እና ተግባራዊ በሚሆኑ ህጎች መዋቅር ስር ተፅኖአችንን በአግባቡ እና በሰላም እንድንለማመድም ያስፈልገናል። መስማማት በማይቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መጠነኛ እና አንድ ለማድረግ መሻት ይኖርብናል።

በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈውን ሕገ መንግሥት የማስከበር አካል የሆኑ ሌሎች ግዴታዎች አሉ። የተነሳሳውን የህገ-መንግስት መርሆዎች መማር እና መደገፍ አለብን። እነዛን መርሆዎች በተግባራቸው የሚደግፉትን ብልህ እና መልካም ሰዎችን መሻት እና መደገፍ አለብን።8 በየዜግነት ጉዳዮች ላይ ተፅኖአችን እንዲሰማ በማድረግ እውቀት ያለን ዜጎች እንሁን።

በዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ዲሞክራሲዎች ውስጥ የፖለቲካዊ ተፅዕኖ የሚደረገው (በምናበረታታው) ለቢሮ በመወዳደር፣ በምርጫ፣ በገንዘብ እርዳታ፣ በአባልነት እና በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በማገልገል እና ከባለስልጣናት፣ ከፓርቲዎች እና ከእጩዎች ጋር ቀጣይነት ባለው ንግግር ነው። በጥሩ ሁኔታ ለመስራት፣ አንድ ዲሞክራሲ እነዚሁን ሁሉ ይፈልጋል ነገር ግን ታታሪ ዜጋ ሁሉንም ነገር ማቅረብ የለበትም።

ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮች አሉ እና ማንም ፓርቲ፣ መድረክ እና የግለሰብ እጩ ሁሉንም የሰው ምርጫዎች ማርካት አይችልም። ስለዚህ እያንዳንዱ ዜጋ በማንኛውም ጊዜ ለእሱ ወይም ለእሷ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን መወሰን አለበት። እንግዲያውስ አባላት እንደየየራሳቸው ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ተፅእኖዎች እንዴት እንደሚተገበሩ መነሳሻ መፈለግ አለባቸው። ይህም ቀላል አይደለም። ከምርጫ ወደ ምርጫ እራሱ የፓርቲ ድጋፍ ወይም የእጩ ምርጫዎች መቀየርን ሊጠይቅ ይችላል።

እንደነዚህ አይነት የግል ስራዎች አንድ አንድ ጊዜ መራጮች መደገፍ የማይችሉትን ሌሎች አቋሞች ያላቸውን እጩዎችን ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወይም መድረኮችን መደገፍ ይጠይቃል።9 በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አባሎቻችንን እርስ በእርስ ከመፍረድ እንዲቆጠቡ የምናናበረታታበት አንዱ ምክንያት ያ ነው። አማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱስ ለሆነ ፓርቲ አባል መሆን አይችልም ወይም ለሆነ እጩ መምረጥ አይችልም ብለን መከራከር በፍፁ የለብንም። ትክክለኛ መርሆዎችን እናስተምራለን እናም ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ አባሎቻችን እነዛን መርሆዎች እንዴት እንደሚያስቀድሙ እና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እንዲመርጡ እንተዋቸዋለን። የአካባቢ መሪዎቻችንን የፖለቲካ ምርጫዎች እና ትስስር በማንኛውም የቤተክርቲያናችን ስብሰባዎች ላይ የማስተማር ወይም የክርክር ጉዳይ እንዳይሆኑ አጥበቀው እንዲጠይቁ አጥብቀን እንጠይቃለን።

በእርግጥ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከነፃ የቤተክርስቲያን የሐይማኖት ልምምድ ወይም ከጠቃሚ የቤተክርስቲያን ድርጅቶችላይ ተፅዕኖ አለው ብለን የምንወስደውን የተለየ የህግ አውጪ ሃሳቦች የማፅደቅ ወይም የመቃወም መብቷን ትለማመዳለች።

ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የህገ-መንግስት መለኮታዊ መነሳሳት እመሰክራለሁ እና ያነሳሳውን መለኮታዊ አካል የምንገነዘበው ሰዎች ታላቁን መርሆዎች ሁሌም እንድንደግፍ እና እንድንጠብቅ እፀልያለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. See Mark Tushnet, “Constitution,” in Michel Rosenfeld and András Sajó, eds., The Oxford Handbook of Comparative Constitutional Law (2012), 222. ሶስቱ አገራት በጽሑፍ ባልሰፈረ ህገ-መንግስት የሚተዳደሩት ዩናይትድ መንግስት፣ ኒውዚላንድ እና እስራኤል ናቸው። እነዚህ እያንዳንዱ የህገ-መንግስታዊነት ጠንካራ ባህሎች አላቸው ምንም እንኳን የገዢው ድንጋጌዎች በአንድ ሰነድ ባይጠቃለልም።

  2. United States Constitution, article 1, section 2 [የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት፣ አንቀፅ 1፣ ክፍል 2] ተመልከቱ።

  3. J. Reuben Clark Jr., “Constitutional Government: Our Birthright Threatened,” Vital Speeches of the Day, Jan. 1, 1939, 177, quoted in Martin B. Hickman, “J. Reuben Clark, Jr.: The Constitution and the Great Fundamentals,” in Ray C. Hillam, ed., By the Hands of Wise Men: Essays on the U.S. Constitution (1979), 53. ብሬጌም ያንግ ተመሳሳይ የህገ-ምንግስት የእድገት እይታን ያዘ፣ ገበሬዎች “ለሚመጡ ትውልዶች በመዋቅሩ ላይ እንዲገነቡ መሰረትን ጣሉ” አስተማረ (Discourses of Brigham Young፣ ሴል ጆን ኤ ዊድፆ [1954 (እ.አ.አ)]፣ 359።

  4. እነዚህ አምስቱ ተመሳሳይ ናቸው ነገር ግን በጄ ሩበን ክላርክ ውስጥ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ ቢሆኑም አንድ አይደሉም፦ J. Reuben Clark Jr., Stand Fast by Our Constitution (1973), 7; Ezra Taft Benson, “Our Divine Constitution,” Ensign, Nov. 1987, 4–7; and Ezra Taft Benson, “The Constitution—A Glorious Standard,” Ensign, Sept. 1987, 6–11. በአጠቃላይ፣ ኖወልቢ ሬይኖለድስ፣ “The Doctrine of an Inspired Constitution፣” በ By the Hands of Wise Men፣ 1–28 ይመልከቱ።

  5. የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት፣ ማሻሻያ 10።

  6. የዩናይትድ ስቴትስ ህገ-መንግስት፣ አንቀፅ 6።

  7. የእምነት አንቀፆች 1፥12፣ ይመልከቱ።

  8. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥10ይመልከቱ።

  9. ዴቪድ ቢ ማገልባይ፣ “The Necessity of Political Parties and the Importance of Compromise፣” BYU Studies፣ ይዘት 54፣ ቁጥር 4 (2015 እ.አ.አ)፣ 7–23 ይመልከቱ።

አትም