አጠቃላይ ጉባኤ
እስራኤልን መሰብሰብ ትችላላችሁ!
የሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:53

እስራኤልን መሰብሰብ ትችላላችሁ!

ይህንበማንነታችሁ ናውስጣችሁ ካለው ታላቅ ሃይል የተነሳ ይህን ማድረግ እንደምትችሉ በበፍጹም እርግጠኛ ነኝ።

ከሶስት አመት በፊት ገደማ ፕሬዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የኋላኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ወጣቶች በሙሉ በሁለቱም መጋረጃ በኩል ያለውን “እስራኤል በመሰብሰብ እንዲያግዙ በጌታ ወጣት ጦረኞች ውስጥ እንዲመለመሉ” ጋብዞ ነበር። “ያ መሰብሰብ አሁን በምድር ላይ እየሆኑ ካሉ ነገሮች ሁሉ እጅግ አስፈላጊው ነገር ነው” ብሎ ነበር።1 ይህን (1) በማንነታችሁ እና (2) ውስጣችሁ ካለው ታላቅ ሃይል የተነሳ ማድረግ እንደምትችሉ በጥሩ ሁኔታም እንደምትፈጽሙት ፍጹም እርግጠኛ ነኝ።

ወንድም ኮርቢት እና እህት ኮርቢት

ከአርባ አንድ አመታት በፊት ሁለት የቤተክርስትያናችን ሚስዮናውያን ወደ ኒው ጀርሲ (አሜሪካ) ወደሚገኝ አንድ ቤት እንደተመሩ ተሰማቸው። ከጊዜም በኋላ ሁለቱም ወላጆች እና አስር ልጆቻቸው በሙሉ በተአምራዊ ሁኔታ ተጠመቁ። በነብዩ ቃላት እነርሱ በህይወታቸው “እግዚአብሄር እንዲያሸንፍ” ፈቀዱ።2 “በህይወታችን” ማለት አለብኝ። ሶስተኛ ልጅ ነበርኩ። ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ቋሚ ቃልኪዳን ስገባ የ17 አመት ልጅ ነበርኩ። ነገር ግን ሌላ ምን እንደወሰንኩ ገምቱ? የሙሉ ጊዜ ምስዮናዊ አገልግሎት ላለማገልገል ነበር። ያ ከልክ በላይ ነበር። እናም ደግሞ ይህ ከኔ ሊጠበቅ አይችልም አይደል? እኔ አዲስ የቤተክርስትያን አባል ነበርኩ። ገንዘብ አልነበረኝም። በተጨማሪም ምንም እንኳን በምዕራብ ፊላደልፊያ እጅግ ከባድ ከሚባል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብመረቅም እና አንዳንድ አደገኛ ተግዳሮቶች ቢገጥሙኝም ለሁለት አመታት ከቤት መውጣት በድብቅ አፈራ ነበር።

የኮርቢት ቤተሰብ

እውነተኛ ማንነታችሁ

ነገር ግን እኔ እና የሰው ዘር በሙሉ እንደ መንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች ከመወለዳችን በፊት ከሰማይ አባታችን ጋር እንደኖርን ተምሬ ነበር። ልክ እኔ እንዳወኩት የሰማይ አባታችን ከሁሉም ልጆቹ ጋር ለዘላለም ለመኖር እንደሚናፍቅ ሌሎችም ማወቅ ነበረባቸው። ስለዚህ ማንም ምድር ላይ ከመኖሩ በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የመዳን እና የደስታ ፍጹም እቅድ አዘጋጀ። በአሳዛኝ ሁኔታ ሰይጣን የእግዚአብሄርን እቅድ ተቃወመ።3 በራዕይ መጽሃፍ መሰረት “በሰማይ ሰልፍ ሆነ።”!4 ሰይጣን አንድ ሶስተኛ የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆችን በእግዚአብሄር ፈንታ እሱ እንዲያሸንፍ በብልጠት አሳተ።5 ነገር ግን እናንተን አይደለም። ሀዋርያው ጳውሎስ “ከምስክራችሁ ቃል የተነሣ” ሰይጣንን ድል እንደነሳችሁት አይቷል።

በፓትርያርክ በረከቴ በመታገዝ እውነተኛ ማንነቴን ማወቄ የፕሬዝደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦልን እስራኤልን የመሰብሰብ ግብዣ እንድቀበል ድፍረት እና እምነት ሰጠኝ7። ለናንተም ተመሳሳይ ነገር ይሆናል፣ ውድ ወዳጆቼ። ከዚህ በፊት በምስክርነታችሁ ቃል ሰይጣንን ማሸነፋችሁን ማወቃችሁ ዛሬ እና ሁልጊዜም በእግዚአብሄር ልጆች ላይ ያ ተመሳሳይ ሰልፍ ሲታወጅ ሌሎችን እንድትወዱ፣ እንድታካፍሉ እና እንድትጋብዙ8 —ሌሎች እንዲመጡ እና እንዲያዩ፣ እንዲረዱ፣ እና አባል እዲሆኑ ይረዳል።

ሽማግሌ ኮርቢት

በእናንተ ውስጥ ያለው ሃያል እምነት

በእናንተ ውስጥ ያለው ግዙፉ ሃይልስ? ይህን አስቡ፤ ሁሉም አካላዊ እና መንፈሳዊ ሞት ወደሚሞቱበት የወደቀች አለም ለመምጣት በደስታ እልል9 ብላቹ ነበር። በራሳችን የትኛውንም ማሸነፍ አንችልም ነበር። በራሳችን ሃጥያት ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሃጥያት እንሰቃያለን። የሰው ልጅም ሊታሰብ የሚችለውን ሁሉ መሰበር እና ሃዘን ይገጥመው ነበር10—እናም በአዕምሯችን ላይ ካለው የመርሳት ግርዶሽ ጋር፣ የአለም ዋናው ክፉ ጠላት አነጣጥሮብንመፈተኑም ይቀጥል ነበር። ሁሉም ከሞት ለመነሳት እና ንጹህ ሆኖ ወደ እግዚአብሄር መገኘት የመመለስ ተስፋው ቃል ኪዳኑን በመጠበቅ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።11

ወደፊት ለመጓዝ ምን ሃይልን የሰጣቹ ምንድነው? ፕሬዝደንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ “በምድራዊ ህይወት ሊያጋጥመን ስለሚችለው ፈተና ያለን እውቀት ውስን ቢሆንም እንኳን የደስታን እቅድ ለመደገፍ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት እና የእርሱን ድርሻ ማወቅ እምነት ይጠይቃል” ብሎ አስተምሯል።12 ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚች ምድር እንደሚመጣ እና እኛን ለመሰብሰብ13 እና ለማዳን ህይወቱን እንደሚሰጥ ቃል ዝም ብላቹ አላመናችሁም ነበር። እናንተ “ክቡር መናፍስት”14 “እጅግ ታላቅ እምነት” ስለነበራችሁ ቃልኪዳኑ በእርግጥ እንደሚሆን ተመለከታችሁ።15 እርሱ ሊዋሽ አይችልም ስለሆነም ገና ከመወለዱ በፊት ደሙን ለናንተ እንዳፈሰሰ አድርጋችሁ አያችሁ።16

በዮሃንስ ምልክታዊ ቃላት እናንተ “ ከበጉ ደም የተነሣ [ሰይጣንን] ድል ነሳችሁ።17 ፕሬዝዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ በዚያ አለም “[እናንተ] መጨረሻውን ከመጀመርያም ተመልክታችኋል” ብሎ አስተምሯል።18

ለምሳሌ አንድ ቀን ትምህርት ቤት ከመሄዳችሁ በፊት ከወላጆቻችሁ አንዱ ወደቤት ስትመለሱ የምትወዱትን ምግብ እንደሚሰሩላችሁ እውነተኛ ቃል ገቡላችሁ እንበል! እናንተ ደስ ብሏችኋል! ትምህርት ቤት ሆናችሁ ያን ምግብ ስትበሉ እና ስትቀምሱ ታስባላችሁ። ዝም ብላችሁ መልካም ዜናችሁን ለሌሎች ታካፍላላችሁ። ወደ ቤት መሄድ ስለሚያስደስት ትጓጓላችሁ ስለዚህ ፈተናዎች እና የትምህርት ቤት ችግሮች ይቀሏችኋል። የተገባላችሁ ቃል የተረጋገጠ ስለሆነ ምንም ነገር ደስታችሁን ሊወስድባችሁ ወይም እንድትጠራጠሩ ሊያደርጋችሁ አይችልም። በተመሳሳይ መልኩ እናንተ የተከበራችሁ መናፍስት ከመወለዳችሁ በፊት የክርስቶስን ቃልኪዳኖች በእርግጠኝነት ለመመልከት ተምራችኋል እንዲሁም የእርሱን ማዳን19 ቀምሳችኋል። እምነታችሁ የበለጠ ባንቀሳቀሳችሁ ቁጥር እየጠነከሩ እና እየተለቁ እንደሚሄዱ ጡንቻዎች ናቸው ነገር ግን አስቀድመው በናንተ ውስጥ ናቸው።

እንዴት ነው በክርስቶስ ያላችሁን ትልቅ እምነት በማንቃት አሁን ላይ እስራኤልን ለመሰብሰብ እና ሰይጣንን ዳግም ማሸነፍ የምንችለው? ወደፊት ለማየት እና ለመመልከት ዛሬ እስራኤልን ለመሰብሰብ እና ለማዳን በጌታ ቃልኪዳን በተመሳሳይ እርግጠኝነት እንደገና በመማር ነው። እርሱ መፅሐፈ ሞርሞንን እና ነቢያቶቹን በመጠቀም እንዴት የሚለውን ያስተምረናል። ከክርስቶስ መምጣት ረዥም ጊዜ በፊት ኔፋውያን “ነቢያት እና …ካህናት…እና መምህራን … ህዝቦችን … ወደ መሲሁ ወደፊት እንዲመለከቱ እና እርሱ እንደመጣም አይነት እንደሚመጣ እንዲያምኑ በመምከር በትጋት አገለገሉ።20 ነብዩ አቢናዲ እንዲህ አስተማረ፣ “እናም፣ ስለነገሮች መምጣት እንደመጡ በመናገር፣ እንግዲህ ክርስቶስ ወደ ዓለም ባይመጣ ኖሮ ቤዛ ሊሆን አይችልም ነበር።”21 በአልማ ቃላት አቢናዲ “ወደፊት በእምነት አይን [እየተመለከተ]”22 የእግዚአብሄርን የማዳን ቃልኪዳን እንደተፈጸመ አድርጎ አየ። ክርስቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ልክ እንደናንተ “በበጉ ደም እና በምስክርነቱ ቃል ሰይጣንን ድል ነስቷል።” እናም ጌታ ለነዚህ ታማኝ አገልጋዮች እስራኤልን በመጋበዝ እንዲሰበስቡ ሃይል ሰጣቸው። በእምነት ወደፊት ስትመለከቱ በአለማቀፍ ደረጃ እንዲሁም በራሳችሁ “ዙሪያ” እስራኤል ተሰብስባ ስታዩ፣ እና ሁሉንም ስትጋብዙ ተመሳሳይ ነገር ለናንተም ያደርጋል።23

በመቶዎች የሚቆጠሩ ምስዮናውያን ያገኟቸውን እና ያስተማሯቸውን የጥምቀት እና የቤተመቅደስ ልብስ ለብሰው በምናባቸው በመሳል በክርስቶስ የነበራቸው የቅድመ አለም እምነት ላይ ይገነባሉ። “መጨረሻውን በማሰብ ጀምሩ”24 በሚል ርእስ ባደረጉት ንግግር ፕሬዝደንት ኔልሰን ይህን የማድረግ ግላዊ ምሳሌ እና የታዘዙ የምስዮን መሪዎች ይህንን ምስዮኖች እንዲያደርጉ እንዲያስተምሯቸው አዘዋል። ይህን በቅድመ ምድራዊ አለም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን ታላቅ እምነት ማወቅ ውድ ምስዮኖቻችን “እርሱን እንዲሰሙት”25 እናም ጌታ ቃል እንደገባው እስራኤልን ለመሰብሰብ ታላቁን እምነታቸውን እንዲያነቁ ረድቷቸዋል።

በርግጥ ውሸትን ማሰላሰል እምነትን ይጎዳል።26 ጓደኞቼ፣ ከማንነታችሁ ጋር የሚጋጩ በተለይም አግባብ ያልሆኑ ምስሎችን፣ ሆን ብሎ ማየት ወይም መመልከት በክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት ያዳክማል እናም ያለ ንስሃ ሊያጠፋችሁ ይችላል። እባካችሁን ምናባችሁን በክርስቶስ ላይ እምነት ለመጨመር እንጂ ለማበላሸት አትጠቀሙ።

የልጆች እና ወጣቶች ፕሮግራም

የልጆች እና ወጣቶች ፕሮግራም ለታላቅ እምነታችሁ ሃይል የሚሰጥ ትንቢታዊ መሳርያ ነው። ፕሬዝደንት ኦክስ እንዲህ አስተማሩ፣ “ያ ፕሮግራም የተዘጋጀው በአራት ነገሮች እንደ አዳኛችን እንድንሆን ለመርዳት ነው፤ እነሱም በመንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ አካላዊ እና አዕምሯዊ ናቸው።”27 እናንተ ወጣቶች ወንጌልን በመኖር፣ ሌሎችን በመንከባከብ፣ ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ በመጋበዝ፣ ቤተሰቦችን ለዘላለም በማዋሃድ፣ እና አዝናኝ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ስትመሩ፣28 በቅድመ ምድር የነበረው በክርስቶስ ላይ ያለው እምነታችሁ ይመለሳል እናም በዚህ ህይወት የጌታን ስራ እንድትሰሩ ያበቃችኋል!

በተጨማሪም የግል ግቦች “በተለይም የአጭር ጊዜ ግቦች”29 ኃይለኛ እምነታችሁን እንድታቀጣጥሉ ይረዳችኋል። መልካም ግብ ስታስቀምጡ የሰማይ አባት እናንተ ወይም ሌሎች እንዲሆኑ የሚፈልገውን በማየት ከዚህ ቀደም እንዳደረጋችሁት ወደፊት ትመለከታላችሁ።30 ከዚያም እንዲሳካ ታቅዳላችሁ እንዲሁም ጠንክራችሁ ትሰራላችሁ። ሽማግሌ ኩዊንተን ኤል.ኩክ “ በእምነት አይን የማቀድ፣ ግብ የማስቀመጥ … እና ፟[ ሌሎችን የመጋበዝ] አስፈላጊነትን ዝቅ አድርጋችሁ አትመልከቱ” በማለት አስተምሯል። 31

ምርጫው የእናንተ ነው! ጌታ “[የመምረጥ] ሃይል በእነርሱ ውስጥ ነውና” ብሎ ተናግሯል።32 ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን “እምነታችሁ የሚያድገው በአጋጣሚ ሳይሆን በምርጫ ነው”33በማለት አብራርቷል። በተጨማሪም “ማንኛውም ትክክለኛ ጥያቄያችሁ … በትዕግስት እና በእምነት አይን ይመለሳል” ብሏል።34

እመሰክራለሁ (1) እውነተኛ ማንነታችሁ እና (2) በእናንተ ውስጥ ያለው በክርስቶስ ላይ ያለ ታላቅ የእምነት ሃይል “ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በመጋበዝ የሃጥያት ክፍያው በረከቶችን እንዲቀበሉ በማስቻል አለምን ለአዳኙ ዳግም መምጣት ያዘጋጃል።“35 የመጽሃፈ ሞርሞንን እርግጥ የሆነ ቃልኪዳን ደስታ ሁላችንም እንድንካፈል እመኛለሁ።

“የነቢያትን ቃል የሚሰሙ እናም… ፣ የተሰጠውን ምልክት በመጠባበቅ በእምነት ፀንተው ክርስቶስን ወደ ፊት የሚመለከቱ ጻድቃኖች—እነሆ፣ እነርሱም የማይጠፉት ናቸው።

“ነገር ግን [ክርስቶስ] … ይፈውሳቸዋል … በእርሱ ሰላም ይኖራቸዋል።”36

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።