ታላቁ እቅድ
እኛ የእግዚአብሔርን እቅድ የምናውቀው እና ለመሳተፍ ቃል የገባነው እነዚህን እውነቶች የማስተማር ግልፅ ሀላፊነት አለብን።
በልዩ ፈተናዎች እና ችግሮች መካከል ቢሆንም እንኳን በእውነት የተባረክን ነን! ይህ አጠቃላይ ጉባኤ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስን ሀብት እና የደስታ ፍሰትን ሰጥቶናል። ዳግም መመለስን በጀመረው በአብ እና በወልድ ራዕይ ሐሴት አድርገናል። ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ትምህርቱ መመስከር ዋናው እቅዱ ስለሆነው፣ ስለመፅሐፈ ሞርሞን ተአምራዊ መምጣትም አንድናስታውስ ተደርገናን። ለነቢያት እና ለግል ስለሚሰጡት ራዕያት እውነታም በማወቅ በደስታ ታድሰናል። ስለኢየሱስ ክርስቶስ የማያልቀው የኃጢያት ክፍያ እና ስለ አካላዊው ትንሣኤው ውድ የሆኑ ምስክሮችን ሰምተናል። እናም እግዚአብሔር አብ አዲስ ለተጠራው ነቢይ ጆሴፍ ስሚዝ የተገለጠውን ሌሎች የወንጌሉ ሙላት እውነቶች “ይህ የምወደው ልጄ ነው” አድምጠው! ብሎ ካወጀ በኋላ ተምረናል።” (ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥17)
ስለክህነት እና ቁልፎቹ ዳግም መመለስ በተመለከተ ባለው እውቀት ማረጋገጫ አግኝተናል። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሚባለው በትክክለኛው ስሟ የጌታ ዳግም የተመለሰች ቤተክርስቲያን እንድትታወቅ ለማድረግ ባለን ቁርጠኝነት ታድሰናል። እናም የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የአሁኑን እና የወደፊቱን ተፅእኖ ለመቀነስ በጾምና በጸሎት እንድንሳተፍ ተጋብዘናል። በዚህ ጠዋት የጌታ ህያው ነቢይ የዳግም መመለስን ታሪካዊ አዋጅ ባቀረቡበት ተነሳስተናል። እንዲህ የሚለውንም አዋጅን እናረጋግጣለን “የዳግም መመለስ መልዕክትን በጸሎት የሚያጠኑ እና በእምነት የሚጸኑ ሰዎች ስለዚያ መለኮታዊነት እና አለምን ተስፋ ለተገባው ለጌታችን እና ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት ስላለው እቅድ የራሳቸውን ምስክርነት በማግኘት ይባረካሉ።”1
እቅዱ
ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ከፍ እንዲሉ እና እንደ እርሱ እንዲሆኑ የማስቻል ዓላማው የሆነው የመለኮታዊ ዕቅድ አካል ነው። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንደ “ታላቁ የደስታ እቅድ፣” “የቤዛነት እቅድ፣” እና “የደህንነት እቅድ” (አልማ 42፥8፣ 11፣ 5) ተብሎ የሚጠራው፣ በዳግም መመለስ ውስጥ የተገለጸው፣ ያም እቅድ የተጀመረው በሰማይ ሸንጎ ነበር። እንደ መንፈሶች፣ እኛም የሰማይ ወላጆቻችን ይደሰቱበት የነበረውን ዘለአለማዊ ህይወት ለማግኘት ፈለግን። በዚያን ጊዜ ያለ ሥጋዊ አካል የሟች ተሞክሮ እስከቻልነው ድረስ እድገት አድርገናል፡፡ ያንንም ተሞክሮ ለመስጠት፣ እግዚአብሔር አብ ይህችን ምድር ለመፍጠር አቀደ። በታቀደው ሟች ህይወት ውስጥ፣ ለመንፈሳዊ እድገታችን አስፈላጊ የሆነውን ተቃውሞ ሲያጋጥመን በኃጢያት እንቆሽሻለን። ለምድራዊ ሞትም ተገዢ እንሆናለን። ከሞት እና ከኃጢያት እኛን መልሶ ለማውጣትም፣ የሰማይ አባታችን እቅድ አዳኝን ያቀርባል። የእርሱ ትንሳኤ ሁሉንም ከሞት ያድናል፣ እናም የእርሱ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕትም እድገታችንን ለማሳደግ በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ከኃጢአት ለማንጻት አስፈላጊ የሆነውን ዋጋ ይከፍላል። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ለአብ እቅድ ዋና ክፍል ነው።
በሰማይ ሸንጎ ውስጥ፣ የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ሁሉ የአብ እቅድ፣ እንዲሁም የዚህ ዘለአለማዊ ውጤቱ እና ፈተናዎች፣ የሰማይ እርዳታዎቹ፣ እና የዚህ ግርማዊ እጣ ፈንታ እንዲያውቁት ተደረገ። መጨረሻውን ከመጀመሪያው ተመለከትን። በዚህ ምድር ላይ የተወለዱት ብዙ ሺህ ሰዎች ሁሉ የአብ ዕቅድን መረጡ እናም ያንንም ተከትሎ በመጣው ፉክክር በሰማይ ጦርነትም ተዋጉ፡፡ ብዙዎች በሟችነት ምን እንደሚያደርጉ ከአብ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ። ገና ባለተገለጹ መንገዶችም፣ በመንፈስ አለም የነበሩን ስራዎቻችን በዚህ ሟች ህይወት ያሉንን ሁኔታዎች ላይ ተፅዕኖ አደረጉ።
ሟችነት እና የመንፈስ አለም
በስጋዊ ጉዞዎቻችን እና ተከትሎት በሚመጣው የመንፈስ አለም ውስጥ ተጽዕኖ ስለሚፈጥሩብን የአብ እቅድ አንዳንድ ዋነኛ ነገሮች በማጠቃለያነት እናገራለሁ።
የሟች ሕይወት እና ከህይወት በኋላ የሚቀጥለው እድገት ዓላማ የእግዚአብሔር ልጆች ልክ እንደ እርሱ እንዲሆኑ ነው። ይህም የሰማይ አባት ለልጆቹ ሁሉ ያለው ፍላጎት ነው። ይህን አስደሳች እጣ ፈንታ ለማሟላት፣ በአባት እና በወልድ ፊት ለመኖር እና ከፍ ከፍ ያለውን በረከቶች ለመደሰት በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት የነጹ ሰዎች መሆን እንዳለብን ዘለአለማዊ ህግጋት ግድ ይላሉ። መፅሐፈ ሞርሞን እንደሚያስተምረው፣ “እርሱም ከቸርነቱ ይካፈሉ ዘንድ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል፤ እናም ወደ እርሱ የሚመጡትን ማንንም፣ ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውንና ነፃውን፤ ሴትና ወንድን አይክድም፤ እምነተቢሶችንም ያስታውሳል፤ እናም ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው“ (2 ኔፊ 26፥33፤ ደግሞም አልማ 5፥49ይመልከቱ)።
እኛ እንሆን ዘንድ እጣ ፈንታችን የሆነውን ለመሆን የተሰራው መለኮታዊ እቅድ ሟች የሆኑ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ትእዛዛት እና እቅዱ ጋር የሚጻረር ድርጊት እንዲፈፅሙ የሚያደርጋቸውን መጥፎ ተቃራኒ በመቃወም ምርጫ እንድናደርግ ይፈልጋል። እንዲሁም እንደ ኃጢያቶች ወይም እንደ አንዳንድ የውልደት ጉድለቶች እይነት ላሉ ሌሎች የምድራዊ ህይወት ተቃውሞዎች እንድንጋለጥ ይፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልገን እድገታችን ከምቾትና ከመረጋጋት ይልቅ በመከራ እና በፈተና ጊዜ በተሻለ ይከናወናል። እናም መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የሟችነትን አስከፊ ውጤቶች በሙሉ ካልረዳን በስተቀር፣ ከእነዚህ ሟች ተቃውሞዎች ማንኛውም ዘለአለማዊ ዓላማውን ማሳካት አይችልም።
ዕቅዱ በዘለአለም እጣ ፈንታችንን፣ በሟችነት ጊዜአችን የምንጓዝበትን አላማ እና ሁኔታ፣ እና የምንቀበላቸውን ሰማያዊ እገዛዎችን ያሳያል። የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ወደ አደገኛ ሁኔታዎች እንዳንገባ ያስጠነቅቁናል። በመንፈስ የተነሳሱመሪዎች ትምህርቶች መንገዳችንን የሚመሩ እና ዘለአለማዊ ጉዞአችንን የሚያበረታቱ ማረጋገጫዎች ይሰጣሉ።
የሟችነት መንገዳችንን ለማገዝ የእግዚአብሔር እቅድ አራት ታላላቅ ማረጋገጫዎችን ይሰጠናል። ሁሉም የእቅዱ ማእከል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል የተሰጡን ናቸው። የመጀመሪያውም ንስሐ ለገባንባቸው ኃጢአቶች፣ በመከራው ከእነዚያ ኃጢያቶች መንጻት እንደምንችል ያረጋግጥልናል። ከዚያ መሐሪው የመጨረሻው ዳኛ “ከእንግዲህ አያስታውሳቸውም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42)።
ሁለተኛ፣ እንደ አዳኛችን የኃጢያት ክፍያ አካል በራሱ ላይ ሁሉንም ሌሎች የስጋዊ ህይወት ህመሞችን ወሰደ። ይህ እንደ ጦርነት እና ቸነፈር ያሉ የማይቀሩ ምድራዊ የግል እና አጠቃላይ፣ ሸክሞችን እንድንሸከም መለኮታዊ እርዳታ እና ብርታት እንድንቀበል ያስችለናል። መፅሐፈ ሞርሞን ስለኃጢያት ክፍያ ሃይል አስፈላጊና ግልጽ የቅዱሳት መጻህፍት መግለጫችንን ያቀርባል። አዳኝ “የሕዝቡን ሥቃይ እና ህመም [እና ድክመት]” ወሰደው። … አንጀቱ በምህረት ይሞላ ዘንድ፣ ድካማችንን በራሱ ላይ አደረገ እናም በስጋ ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ ያውቅ ዘንድ ይህንን ያደርጋል” (አልማ 7፥11–12)።
ሶስተኛ፣ አዳኙ፣ በማይገደበው የኃጢያት ክፍያው አማካኝነት፣ የሞትን መጨረሻነት ይሰርዛል እናም ሁላችንም ከሞት እንደምንነሳ አስደሳች ማረጋገጫ ይሰጠናል። መፅሐፈ ሞርሞን እንዲህ ያስተምራል፣ “ይህም ዳግም መመለስ ለሁሉም ይሆናል፣ ለሽማግሌዎች እና ለወጣቶች፣ ለታሰሩ እና ነፃ ለሆኑትም፣ ለሴትና ለወንድ፣ ለኃጢያተኛ እና ለፃድቃን፣ እናም እንዲሁም የራስ ፀጉራቸው እንኳን አይጠፋም፤ ነገር ግን ሁሉም ነገር በፍጹም መልክ ይመለሳል” (አልማ 11፥44)።
በዚህ የፋሲካ ወቅት የትንሳኤን እውነተኛነት እናከብራለን። ይህ በእያንዳንዳችን እና በምንወደው ሰው ፊት ሲወለድ የምናገኛቸውን አካላዊ፣ አዕምሯዊ፣ ወይም ስሜታዊ ጉድለቶች ወይም በምንወለድበት ጊዜ ወይም በሟች ህይወታችን ጊዜ ያገኘናቸውን ስሜታዊ ጉድለቶችን ለመቋቋም የሚያስችል እይታ እና ጥንካሬ ይሰጠናል። በትንሳኤ ምክንያት፣ እነዚህ ሟች ጉድለቶች ጊዜያዊ ብቻ እንደሆኑ እናውቃለን።
በዳግም የተመለሰው ወንጌል በትንሳኤ ከቤተሰባችን አባላት ማለትም ከባል፣ ሚስት፣ ልጆች፣ እና ወላጆች ጋር የመሆን እድልን ሊያካትት እንደሚችል ያረጋግጥልናል። ይህ የቤተሰብ ሀላፊነታችንን በሟችነት ለመወጣት የሚያስችለን ለእኛ ትልቅ ማበረታቻ ነው። በሚቀጥለው አስደሳች ግንኙነቶች እና ማህበራት በመጠባበቅ በዚህ ህይወት በፍቅር አብረን እንድንኖር ይረዳናል።
አራተኛ እና በመጨረሻም፣ የዘመናችን ራዕይ እድገታችን በሟችነት ማብቃት እንደሌለበት ያስተምረናል። ስለዚህ አስፈላጊ ማረጋገጫ ጥቂት መገለጥ ነው የተሰጠው። ይህ ሕይወት እግዚአብሔርን ለመገናኘት የምንዘጋጅበት ጊዜ መሆኑን እና ንስሃችንን ማዘግየት እንደሌለብን ተነግሮናል ( አልማ 34፥32–33ይመልከቱ)። አሁንም፣ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ወንጌል “ለክፉዎች እና ለማይታዘዙ አመፀኞች” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥29) እንኳን እንደተሰበከ እና እዚያ የሚማሩትም እነዚያ ደግሞ ከመጨረሻው ፍርድ በፊት ንስሓ መግባት እንደሚችሉ ተምረናል። ( ቁጥሮች 31–34፣ 57–59ይመልከቱ)።
የሰማይ አባታችን ዕቅድ ሌሎች አንዳንድ መሰረታዊ ነገሮች እነሆ።
በዳግም የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ስለ ንጹህነት፣ ጋብቻ እና የልጆች መውለድ ጉዳዮች ላይ ልዩ እይታ ይሰጠናል። ጋብቻ የእግዚአብሔር እቅድ ዓላማውን ለማሳካት፣ ለስጋዊ ህይወት መወለድ መለኮታዊ ሁኔታን ለማቅረብ፣ እና የቤተሰብ አባላትን ለዘለአለም ለማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ያስተምራል። “ጋብቻ በእግዚአብሔር ለሰው የተሰጠ ነው” አለ ጌታ፣ “…ምድር የተፈጠረችበትን አላማ ታሟላ ዘንድ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 49፥15–16)። በዚህ ውስጥ፣ የእሱ እቅድ፣ ከሕግና ከበባህላዊ አንጻር ከአንዳንድ ጠንካራ ዓለማዊ ኃይሎች ጋር ይጋጫል።
ነፍስን የመፍጠር ሀይል እግዚአብሔር ለልጆቹ ከሰጠው ስጦታውች የበለጠ ከፍተኛው ሀይል አለው። አጠቃቀሙ በአንደኛው ትእዛዝ ውስጥ የተሰጠ መብት ነው፣ ግን አላግባብ መጠቀሙን ለመከልከል ሌላ አስፈላጊ ትእዛዝ ተሰጥቷል። ከጋብቻ ማሰሪያ ውጭ፣ ሁሉም የመውለድ ኃይል አጠቃቀሞች በተወሰነ ደረጃ ወይም በሌላ የወንዶች እና የሴቶች መለኮታዊ ባህርያትን የሚያዋርድ እና የሚያበላሹ ናቸው። ዳግም የተመለሰው የወንጌል በዚህ የንፅህና ህግ ላይ ትኩረት የሚያደርገው በእግዚአብሔር እቅድ አፈፃፀም ውስጥ የመባዛት ኃይላችን ባለው አላማ ምክንያት ነው።
ቀጥሎስ ምን አለ?
በዚህ 200ኛው የመጀመርያው ራእይ፣ ተሃድሶን ያነሳሳውን፣ መታሰቢያ በሚከበርበት ወቅት፣ የጌታን ዕቅድ እናውቃለን እና በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያኗ አማካይነት በረከቶቹን ለሁለት ምዕተ ዓመታት በመደሰታችንም እንበረታታለን። በዚህ በ2020 (እ.አ.አ) ዓመት ውስጥ ላለፉት ሁኔታዎች የ20/20 እይታ የሚሉት ታዋቂ አባባል አለን።
የወደፊቱን ስንመለከት፣ እይታችን እርግጠኝነቱ ከዚህ በጣም ያነሰ ነው። ከዳግም መመለስ በኋላ ባሉት ሁለት ምዕተ ዓመታት፣ የመንፈስ ዓለም በአሁኑ ጊዜ የሚከናወነውን የስብከት ሥራ ለማከናወን ብዙ ምድራዊ ተሞክሮ ያላቸው ብዙ ሰዎችን እንደሚያካትት እናውቃለን። ደግሞም ንስሐ የገቡ እና የጌታን ወንጌል በሚቀበሉበት በሞት መጋረጃ ሁለቱም ወገኖች በኩል የጌታን ወንጌል ለሚቀበሉ ሰዎች የዘለአለም ስርዓቶችን ለማከናወን ብዙ ቤተመቅደሶች እንዳለን እናውቃለን። እነዚህ ሁሉ የሰማይ አባታችንን እቅድ ወደፊት ይገፋሉ። የእግዚአብሔር ፍቅር እጅግ ታላቅ በመሆኑሆን ብለው የጥፋት ልጆች ከሚሆኑት ጥቂቶች በስተቀር፣ ለሁሉም ልጆቹ የክብር ዕድል ፈንታ አዘጋጅቶላችዋል ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥43)።
አዳኙ በዳግም እንደሚመጣ እና የእግዚአብሔርን ምድራዊ የሆነውን አካል ለማጠቃለል ሺህ ዓመት የሚሆን የሰላም ንግስና እንደሚኖር እናውቃለን። እኛ ደግሞ ለእያንዳንዱ ሰው የመጨረሻው ፍርድ የእሱን ወይም የእሷን ትንሣኤ ተከትሎ በሚመጣበት ጊዜ የተለያዩ፣ የጻድቃንና እና የሃጥኢያተኞች ትንሳኤዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በድርጊቶቻችን፣ በልቦቻችን መሻቶች፣ እናም እንደሆነው የሰው አይነት መሰረት እንደሚፈረድብን እናውቃለን። ይህ ፍርድ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በመታዘዛቸው ለእነርሱ ብቁ ለሚሆኑበት እና ምቾት የሚያገኙበትን የክብር መንግሥት እንዲወሰዱ ያደርጋቸዋል። የዚህ ሁሉ ዳኛ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ( ዮሃንስ 5፥22፤ 2ኛ ኔፊ 9፥41ይመልከቱ)፡፡ ሁሉን አዋቂነቱ ንስሀ ያልገቡት ወይም ያልተቀየሩት እንዲሁም ንስሐ የገቡ ወይም ጻድቃንን ስለድርጊታችን እና ስለምኞታችን ሁሉ ፍጹም እውቀት ይሰጠዋል። ስለዚህ ከፍርዱ በኋላ “ፍርዱ ትክክል ነው” በማለት ሁላችንም እንመሰክራለን (ሞዛያ 16፥1)።
በመጨረሻም፣ ከስም መወገድ ወይም ከክህደት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ የመመለስን ብዙ የደብዳቤ ጥያቄዎችን በመገምገም እና ወደ እኔ የመጡትን ጥያቀዎች ስመልከት ወደ እኔ የመጣውን መገለጥ አካፍላለሁ። ብዙ አባሎቻችን ስለትምህርቱ እና በዳግም ስለተመለሰው ቤተክርስቲያን በመንፈስ የተነሳሱ ህግጋት ብዙ ጥያቄዎችን የሚመልስንን ይህን የደህንነት እቅድ አይረዱም። የእግዚአብሔርን እቅድ የምናውቀው እና ለመሳተፍ ቃል ኪዳን የገባነውም፣ እነዚህን እውነቶች የማስተማር እና በምድራዊ ጉዳያችን ሌሎችን እና እራሳችንን ወደፊት ለመግፋት የምንችላቸውን ሁሉ ለማድረግ ግልፅ ሀላፊነት አለብን። ስለኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዳኛችን፣ ሁሉንም እንዲቻል ስላደረገው የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።