አጠቃላይ ጉባኤ
የሆሳዕና ጩኸት
የሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።


2:3

የሆሳዕና ጩኸት

አሁን፣ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አብ እና ወልድን ያየበትን የጆሴፍ ስሚዝን የመጀመሪያ ራዕይ ስናከብር፣ በሆሳዕና ጩኸት በመሳተፍ አብረን መደሰታችን ትክክለኛ እንደሆነ ተሰምቶናል።

ይህም ቅዱስ ጩኸት በዚህ የዘመን ፍጻሜ የተሰጠው በሚያዝያ 27፣ 1836 (እ.አ.አ) የከርትላንድ ቤተመቅደስ በተቀደሰበት ነበር። አሁንም ይህ የሚደረገው በእያንዳንዱ የቤተመቅደስ ቅዳሴ ላይ ነው። ይህም አዳኝ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም በገባበት ጊዜ የብዙዎችን ምላሽ የሚያሳይ፣ ለአብ እና ለወልድ የሚሰጥ የተቀደሰ መታሰቢያ ነው። ይህም በተጨማሪ ወጣቱ ጆሴፍ በዚያ ቀን በቅዱስ ደን ውስጥ ያጋጠሙትን፣ ማለትም አብ እና ወልድ የምናመልካቸው እና የምናሞግሳቸው ሁለት የተከበሩ አካላት መሆናቸውን ያረጋግጣል።

አሁን የሆዕሳና ጩኸት እንዴት እንደሚሰጥ አሳያለሁ። ይህንንም ሳደርግ፣ በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ ያሉ የሥራ ባልደረቦቻችን ይህንን እጅግ ቅዱስ ሥነ-ሥርዓት በክብርና በአክብሮት እንዲይዙ እጋብዛለሁ።

እያንዳንዱ ተሳታፊ ንፁህ ነጭ መሀረብ ወስዶ በአንዱ ጥግ በመያዝ፣ እና በአንድ ላይ “ሆሳዕና ፣ ሆሳዕና፣ ሆሳዕና ለእግዚአብሔር እና ለበጉ” እያሉ መሃረቡን በማውለብለብ ሶስት ጊዜ ይደጋግሙ፣ ይህንንም ተከትሎ “አሜን፣ አሜን፣ እና አሜን” ይባላል። ነጭ መሀረብ ከሌላችሁም፣ እጃችሁን ማወዛወዝ ትችላላችሁ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ በሆሳዕና ጩኸት ለመሳተፍ እንድትቆሙ እንጋብዛችኋለን፣ ያንንም ተከትሎ “የሆሳዕና ዝማሬ” እና “የእግዚአብሔር መንፈስ”1 ይዘመራሉ።

የመሪውን ምልክት በመከተል፣ እባካችሁ “የእግዚአብሔር መንፈስ” መዝሙርን ዘምሩ።

ሆሳዕና፣ ሆሳዕና፣ ሆሳዕና ለእግዚአብሔር እና ለበጉ።

ሆሳዕና፣ ሆሳዕና፣ ሆሳዕና ለእግዚአብሔር እና ለበጉ።

ሆሳዕና፣ ሆሳዕና፣ ሆሳዕና ለእግዚአብሔር እና ለበጉ።

አሜን፣ አሜን፣ እናም አሜን።

ማስታወሻ

  1. መዝሙር፣ ቁጥር 2።