ኑ እና በዚህ ሁኑ
በዓለም ላይ ያሉትን ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ታላቅ ጥረት ውስጥ እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን፡፡
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ በየሳምንቱ፤ በዓለም ዙሪያ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ተወዳጁን የሰማይ አባታችንን ፣ የዓለምን አምላክ እና ንጉስ እና የተወደደ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ያመልካሉ። በሕይወት ከኖሩት ሁሉ ብቸኛ ኃጢአት የሌለበት ነፍስ፣ እንከን የሌለው የእግዚአብሔር በግ የሆነውን ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት እና ትምህርቶች እናሰላስላለን። የእርሱን መስዋዕትነት ለማስታወስ ቅዱስ ቁርባንን እንካፈላለን እናም እርሱ በሕይወታችን ውስጥ ማእከል መሆኑን እንገነዘባለን።
እንወደዋለን እና እናከብረዋለን በጥልቅ እና ዘላለማዊ ፍቅሩ ምክንያት፣ እሱ ለእኔ እና ለእናንተ ተሠቃየ እናም ሞተ፡፡ እሱ የሞትን በሮች ከፈተ፣ ጓደኛማቾችን እና የሚወደዱትን የሚለያዩ መሰናክሎችን አፈረሰ፣1 እንዲሁም ተስፋ ላጡ ተስፋ፤ ለታመሙ ፈወስን እንዲሁም ለምርኮኞች ነጻነትን አመጣ፡፡2
ልባችንን፣ ህይወታችንን እና የዕለት ተዕለት ኑሯችንን ለእርሱ እናውላለን፡፡ በዚህ ምክንያት ፣ “ስለ ክርስቶስ እንናገራለን፣ እኛ በክርስቶስ እንደሰታለን ፣ እናም ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን… ልጆቻችን የኃጢያታቸውን ስርየት ከየት እንደሚፈልጉ ያውቁ ዘንድ ፡፡”3
ደቀ መዝሙርነትን መለማመድ
ሆኖም የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ስለ ክርስቶስ ከመናገር እና ከመስበክ የበለጠ ነገርን ይጠይቃል። ይበልጥ እንደ እርሱ እንድንሆን መንገዱ ላይ እኛን ለመርዳት አዳኛችን ራሱ ቤተክርስቲያኑን መልሷል። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተዋቀረው የደቀመዝሙርነት መሰረታዊ ነገሮችን ለመለማመድ እድሎችን ለማቅረብ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ በምናደርገው ተሳትፎ የመንፈስ ቅዱስን መነሳሳት ማወቅ እና ተግባራዊ ማድረግን እንማራለን፡፡ ለሌሎች በርህራሄ እና በደግነት ደራሽ የመሆን ልምድን እናዳብራለን።
ይህ የህይወት ዘመን ጥረት ነው፣ እናም ልምምድ ይጠይቃል።
ስኬታማ አትሌቶች የስፖርታቸውን መሰረታዊ ነገሮች በመለማመድ ስፍር ቁጥር የሌለው ሰዓታትን ያሳልፋሉ፡፡ ነርሶች፣ ኮምፒውተር ሰራተኞች፣ ኑክለር ኢንጂነሮች እና እኔ እራሱ በሃሪየት ኩሽና ውስጥ ተወዳዳሪ ምግብ አብሳይ የሆንኩት ስራችንን በብርታት ስንከታተል ቻይ እና ክህሎታማ እንሆናን።
የአውሮፕላን ካፒቴን እንደመሆኔ መጠን ብዙውን ጊዜ የአውሮፕላን አብራሪዎችን የበረራ ልምድ የሚሰጠውን ውስብስብ ማሽን በመጠቀም አሠለጥናቸዋለሁ። የመለማመጃ የበረራ ማሽኑ አውሮፕላን አብራሪዎች የበረራ መሰረታዊ ነገሮችን እንዲማሩ ብቻ አይደለም፤ እንዲሁም እውነተኛውን አውሮፕላን ሲነዱ ሊያጋጥሟዋቸው የሚችሉ ያልተጠበቁ ክስተቶችን እንዲለማመዱ እና ምላሽ እንዲሰጡም ያስችላቸዋል፡፡
ለኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቶችም ይሄ ተመሳሳይ ይሰራል፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እና በታላቅ ልዩ ልዩ ዕድሎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ መሆን በሕይወት ለሚለዋወጡ ምንም አይነት ሁኔታዎች የተሻለ እንድንዘጋጅ ይረዳናል። እንደ የቤተክርስቲያን አባል፣ በጥንት እና በዘመናዊ ነቢያቶች በኩል እራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማጥለቅ እንድንችል እንበረታታለን። ለሰማይ አባታችን በቅንነት እና ትሁት ጸሎት፣ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ ለመለየት እንማራለን። ለመርዳት፣ ለማስተማር፣ ለማቀድ፣ ለማገልገል እና ለማስተዳደር ጥሪዎችን እንቀበላለን። እነዚህ አጋጣሚዎች በመንፈስ፣ በአዕምሮ እና በባህርይ ውስጥ እንድናድግ ያስችሉናል፡፡
በዚህ ህይወት እና በመጪው ሕይወት የሚባርከን ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለማድረግ እና ለመጠበቅ እንድንዘጋጅ ይረዱናል።
ኑ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ!
በዓለም ላይ ያሉትን ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ታላቅ ጥረት ውስጥ እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን፡፡ ኑ እና ተመልከቱ በዚህ ከባድ የኮሮና ቫይረስ ወቅት እንኳን በቀጥታ ስርጭት (በኦንላይን) እንገናኝ፡፡ ከሚስዮናዊያኖቻችን ጋር በቀጥታ ስርጭት (በኦንላይን) ተገናኙ። ይህ ቤተክርስቲያን ምን ማለት እንደሆነ ለራሳችሁ ፈልጉ! ይህ አስቸጋሪ ጊዜ ሲያልፍ በቤታችን እና በአምልኮ ስፍራዎቻችን ውስጥ ከእኛ ጋር ይገናኙ!
እንድትመጡ እና እንድትረዱ እንጋብዛችኃለን! ኑ እና አብራችሁ አገልግሉ የአዳኙን ፈለግ በመከተል እና ይህን ዓለም የተሻለ ስፍራ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ልጆች እናገልግል።
ኑ እና በዚህ ሁኑ ይበልጥ ታጠነክሩናላችሁ፡፡ ደግሞም የተሻላችሁ፣ ደግ እና ደስተኛ ትሆናላችሁ፡፡ እምነታችሁ ጥልቀት ያለው እና ይበልጥ ጠንካራ ይሆናል—በሕይወታችሁ ውስጥ የሚከሰቱትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች እና ያልተጠበቁ የህይወት ፈተናዎች የመቋቋም ችሎታችሁ ይበልጥ አቅም ያለው ይሆናል፡፡
እና እንዴት ነው የምንጀምረው? ብዙ ሊያስኬዱ የሚችሉ መንገዶች አሉ።
መፅሐፈ ሞርሞንን እንዲያነቡ እንጋብዛችኋለን፡፡ ቅጂ ከሌላችሁ በ ChurchofJesusChrist.org ላይ ሊያነቡ ይችላሉ4 ወይም መፅሐፈ ሞርሞን አፕሊኬሽንን ያውርዱ። መፅሐፈ ሞርሞን ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ነው እናም የብሉይ እና የአዲስ ኪዳን ተጓዳኝ ነው። ሁሉንም ቅዱሳት መጽሐፍት እንወዳቸዋለን እናም ከእነሱ እንማራለን።
የቤተክርስቲያን አባላት የሚያስተምሯቸውን እና የሚያምኑትን ለማወቅ በ ComeuntoChrist.org ላይ ጊዜያችሁን እንድታሳልፉ እንጋብዛችኋለን።
በሚቻልበት ቦታ ሁሉ በቀጥታ ስርጭት ወይም በቤታችሁ በግል እንዲጎበኟችሁ ሚስዮናውያንን ይጋብዙ—እነሱ የተስፋ እና የመፈወስ መልእክት አላቸው። እነዚህ ሚስዮኖች በራሳቸው ገንዘብ እና ጊዜ በዓለም ዙሪያ በብዙ ቦታዎች የሚያገለግሉ ውድ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችን ናቸው።
በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ቤተሰብ ታገኛላችሁ፡፡ ራሳችሁን የተሻለ ለማድረግ በምትጥሩበት ጊዜ የእናንተን እርዳታ የሚፈልጉ እና እናንተን—ሊረዱአችሁ የሚፈልጉ ሰዎችን ታገኛላችሁ፡፡
የአዳኝ እቅፍ ለሁሉም ተዘርግቶአል
ምናልባት እንዲህ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል “በሕይወቴ ውስጥ ስህተቶችን ሰርቻለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሆኩ ሊሰማኝ እንደሚችል እርግጠኛ አይደለሁም፣ እግዚአብሔር እንደ እኔ ዓይነት ሰው አይፈልግም ”
ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ “የነገሥታት ንጉሥ፣”5 መሲህ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም6 ስለ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ በጥልቀት ያስባል። የግለሰቡ አቋም ምንም ይሁን ምን—ምን ያህል ድሃ ወይም ሀብታም፣ ምን ያህል ፍፁምና የጎደለው ወይም የተመሰከረለት ሰው ቢሆንም ያሳስበዋል፡፡ በምድራዊው ህይወቱ ጊዜ አዳኛችን ሁሉንም አገልግሏል፤ ለደስተኞች እና ለተሳካላቸው፣ ለተሰበሩ እና ለጠፉ እና ተስፋ ለሌላቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ያገለገላቸው ሰዎች ታዋቂ፣ ውብ ወይም ሀብታም ግለሰቦች አይደሉም። ብዙውን ጊዜ፣ ከፍ ያደረጋቸው ሰዎች በምላሹ የሚያቀርቧቸው ጥቂት ነገር ነበርአቸው፣ ምስጋና፣ ትሑት ልብ እና እምነት እንዲኖራቸው ፍላጎት ነበራቸው።
ኢየሱስ በምድራዊ ህይወቱ “ለእነዚህ ላነሱት” በማገልገል ካሳለፈ7 ዛሬ እነሱን አይወዳቸውም? ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ቦታ የለምን? ብቁ እንዳልሆኑ፣ እንደተረሱ፣ ወይም ብቸኛ አንደሆኑ ለሚሰማቸው እንኳን?
ለእግዚአብሔር ጸጋ ብቁ ለመሆን ልትደርሱበትበት የሚገባ የፍጹምነት ደረጃ የለም፡፡ ጸሎቶቻችሁ ወደ ሰማይ ለመድረስ ከፍ ባለ ድምጽ ወይም አንደበተ ርቱእ በሆኑ ቃላት መናገር ወይም ትክክል የሆነ ስዋሰው የተከተሉ መሆን የለባቸውም።
እውነቱ፣ እግዚአብሔር አያዳላም8—አለም ዋጋ የሚሰጣቸው ነገሮች ለእርሱ ትርጉም የላቸውም፡፡ እሱ ልባችሁን ያውቃል፣ እናም የእናንተን ማእርግ፣ ጠቅላላ ሃብት ወይም የኢንስተግራም ተከታዮችዎ ቁጥር ምንም ይሁኑ ምን ይወዳችኋል።
ልባችንን ወደ ሰማዩ አባታችን ስንዘረጋ እና ወደ እርሱ ስንቀርብ ፣ እሱ ወደ እኛ ሲቀርብ ይሰማናል።9
ሁላችንም ተወዳጅ ልጆቹ ነን።
እሱን የማይቀበሉም እንኳ፡፡
እነዛ እንደ ኃይለኛ፣ የማይታዘዝ ልጅ፣ በእግዚአብሄር እና በቤተክርስቲያኑ ላይ የተናደዱ፣ በምሳሌያዊ ሁኔታ ሻንጣዎቻቸውን ጠቅልለው የሚሸሹ እና መቼም እንደማይመለሱ በሩን አጋጨተው ዘግተው የሚወጡትም እንኳ፡፡
ልጅ ከቤት ሸሽቶ በሚሂድበት ጊዜ፣ ወላጆቹ በመስኮት በኩል ወደ ውጪ እንደሚመለከቱት አያስተውልም፡፡ በሚራራ ልብ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጃቸው ሲሄድ ይመለከታሉ፤ ውድ ልጃቸው ከዚህ አሳዛኝ ተሞክሮ አንድ ነገር እንዲማሩ እናም ምናልባት በአዲስ እይታ ሕይወትን እንዲመለከቱ፣ እና በመጨረሻም ወደ ቤት እንዲመለሱ ተስፋ በማድረግ፡፡
አፍቃሪው የሰማይ አባታችን እንዲሁ ነው። መመለሻችንን እየተጠባበቀ ነው።
አዳኛችሁ፣ በፍቅር እና በርህራሄ እንባ በሞሉ ዓይኖቹ፤ መመለሳችሁን ይጠብቃል። ከእግዚአብሄር ሩቅ እንደ ሆናችሁ በተሰማችሁ ጊዜም እንኳን እሱ ያያችኋል፡፡ እርሱ ይራራላችኋል እናም እናንተን ለማቀፍ ይሮጣል።10
ኑ እና በዚህ ሁኑ
ከስህተታችን እንድንማር እግዚአብሔር ይፈቅድልናል
እኛ ትርጉም ለማግኘት እና የመጨረሻውን እውነት ለመፈለግ በምድራዊ ህይወት መንገድ ላይ የምንጓዝ ተጓዦች ነን ፡፡ ብዙውን ጊዜ ፣ የምናየው ቀጥተኛ መንገዱን ነው—በመንገዱ ላይ ያሉት መገንጠያዎች ወዴት እንደሚመሩ ማየት አንችልም ፡፡ የሚወድን የሰማይ አባታችን ሁሉንም መልስ አልሰጠንም። ብዙ ነገሮችን ራሳችን እንድንመረምር ይጠብቅብናል፡፡ እንዲህ ማድረግ ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳን፤ እንድናምን ይጠብቅብናል፡፡
ትከሻችንን ቀና እንድናደርግ እና ትንሽ መፍትሄ እንድንፈልግ፤ ትንሽ የጀርባ አጥንት ፤ እና ሌላ እርምጃ ወደፊት እንድንራመድ ይጠብቅብናል፡፡
እኛ የምንማረው እና የምናድገው እንደዚያ ነው።
ሁሉም ዝርዝሮች በቅደም ተከተል እንዲገለጡ በታማኝነት ትፈልጋላችሁ? እያንዳንዱ ጥያቄ እንዲመለስ በታማኝነት ትፈልጋላችሁ? እያንዳንዱ መድረሻ እንዲጠቆም ትፈልጋላችሁ?
ብዙዎቻችን በእንደዚህ ዓይነት የሰማይ ጥቃቅን አስተዳደሮች በፍጥነት እንደሚሰለቸን አምናለሁ፡፡ የህይወትን አስፈላጊ ትምህርቶች በሙከራ እንማራለን፡፡ ከጥፋቶቻችን በመማር። ንስሐ በመግባት እና “ክፋት በጭራሽ ደስታ አለመሆኑን” ለራሳችን በመገንዘብ።11
የእኛ ስህተቶች እንዳይኮንኑን እና እድገታችንን ለዘላለም እንዳይገቱት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ፡፡ በእርሱ ምክንያት፣ ንስሐ መግባት እንችላለን፣ እናም ስሕተቶቻችን ወደ የላቀ ክብር መሸጋገሪያ ድንጋዮች ሊሆኑ ይችላሉ።
ይህንን መንገድ ብቻችሁን መጓዝ የለባችሁም። የሰማይ አባታችን በጨለማ እንድንባዝን አልተወንም።
ለዚህም ነው በ1820(እ.ኤ.አ) በፀደይ ወቅት፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ የታየው።
ለአፍታ ስለዚያ አስቡ፡፡ የጠፈር አምላክ ለሰው ልጅ ታየ!
ጆሴፍ ከእግዚአብሔር እና ከሌሎች ሰማያዊ ፍጥረታት ጋር ካደረጋቸው ብዙ ግንኙነቶች ይህ የመጀመሪያ ነበር፡፡ እነዚህ መለኮታዊ ፍጥረታት የተናገሯቸው ብዙ ቃላት በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቀዱሳን መጽሐፍት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነሱ በቀላሉ ተደራሽ ናቸው፡፡ ማንም ሊያነባቸው እና በእኛ ዘመን እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን መልእክት ራሳቸው መማር ይችላሉ፡፡
እነሱን ራሳችሁ እንድታጠኑ እንጋብዝችኋለን፡፡
ጆሴፍ ስሚዝ እነዚህን መገለጦች ሲቀበል በጣም ወጣት ነበር። አብዛኛዎቹ ሲመጡ 30 ዓመት አልሞላወም ነበር።12 ልምድ አልነበረውም፣ እና ለአንዳንድ ሰዎች፣ ምናልባት የጌታ ነቢይ የመሆን ብቃት ያለው አልመሰላቸውም ነበር፡፡
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የምናገኛቸውን የተለመዱ አካሄዶች እንደ ምሳሌ በመከተል ጌታ ግን እንዲሁም ጠራው።
ወንጌልን ዳግም ለመመለስ እግዚአብሔር ፍጹም ሰው እስኪያገኝ አልጠበቀም፡፡
እሱ እንዲያ ቢያርግ ኖሮ እስከ አሁን ይጠብቅ ነበር።
ጆሴፍ በብዙ እንደ እኔ እና እናንተ ነበር፡፡ እሱ ስህተት ቢሠራም፣ እግዚአብሔር ታላቅ ዓላማዎቹን ዳር ለማድረስ ተጠቅሞበታል፡፡
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ.ሞንሰን “ጌታ የሚጠራውን ጌታ ብቁ ያደርገዋል የሚሉትን የምክር ቃላት ይደጋግሙት ነበር።”13
ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ ከነበሩ ቅዱሳን ጋር ሲወያይ ወንድሞች፣ እህቶች ሆይ፣ ጥሪዎቻችሁን ተመልከቱ። ብዙዎቻችሁ በሰዎች መስፈርት ጠቢባን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁ ኃያል አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁ ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱችሁ አልነበራችሁም።”14
እግዚአብሄር ዓላማውን ለማስፈፀም ደካሞችን እና ቀላል ሰዎችን ይጠቀማል፡፡ ይህ እውነት በምድር ላይ ሥራውን የሚያከናውን የእግዚአብሔር ኃይል እንጂ የሰው ኃይል እንዳልሆነ ምስክር ነው፡፡15
እሱን ስሙት፣ ተከተሉት
እግዚአብሔር ለጆሴፍ ስሚዝ ሲገለጥ፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን አስተዋወቀ እና “እሱን ስማው” አለ፡፡16
ጆሴፍ ቀሪ ሕይወቱን እሱን በመስማት እና በመከተል አሳለፈ።
እንደ ጆሴፍ ሁሉ የእኛ የደቀ መዝሙርነት አዳኙን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመስማት በምንወስነው ውሳኔ ይጀምራል።
እሱን ለመከተል ከፈለጋችሁ እምነታችሁን ሰብስቡ እና መስቀሉን በላያችሁ ላይ ውሰዱ፡፡
የደቀመዝሙርነት እና የደስታን ታላቅነት ለመቀላቀል የምትችሏቸውን የተድላ እና መልካም የሆነ ስፍራ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ስትሆኑ ታገኛላችሁ።
በዚህ የመጀመሪያው ራዕይ ሁለት መቶኛ አመት ክብረ በዓል ወቅት፤ በዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ መልሶ መቋቋም እድልን ስናሰላስል እና ስንማር፣ ታሪካዊ ክስተት ብቻ እንዳልሆነ እንደምንገነዘብ ተስፋዬ ነው። በዚህ ታላቅ እና ቀጣይነት ባለው ታሪክ ውስጥ እኔ እና እናንተ ወሳኝ ሚና እንጫወታለን፡፡
የእኔ እና የእናንተ ደርሻ ምንድን ነው?
ከኢየሱስ ክርስቶስ መማር ነው። ቃሉን ለማጥናት፡፡ በዚህ ታላቅ ሥራ በትጋት በመሳተፍ እሱን ለመከተል፡፡ እንድትመጡ እና በዚህ እንድትሆኑ እጋብዛችኋለሁ!
ፍጹም መሆን አይጠበቅባችሁም። እምነታችሁን ለማዳበር እና በየቀኑ ወደ እርሱ ለመቅረብ ፍላጎት እንዲኖራችሁ ብቻ ነው።
የእኛ ድርሻ እግዚአብሔርን መውደድ እና ማገልገል እንዲሁም የእግዚአብሔርን ልጆች መውደድ እና ማገልገል ነው፡፡
ይህን በምታደርጉበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በዚህ ሕይወት ውስጥ በጣም ከባድ እና ከዚያ በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ብትሆኑም በፍቅር፣ በደስታ እና በተረጋገጠ መመሪያ ይከባችኋል፡፡
ስለዚህ እመሰክራለሁ እናም በረከቶቼን በጥልቅ ምስጋና እና ፍቅር ለእያንዳንዳችሁ እተውላችኋለሁ፣ በተቀደሰው በአዳኙ አና በአለቃችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።